መዝሙር 89:1-52

  • ስለ ይሖዋ ታማኝ ፍቅር መዘመር

    • ከዳዊት ጋር የተደረገ ቃል ኪዳን (3)

    • የዳዊት ዘር ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል (4)

    • አምላክ የቀባው ንጉሥ እሱን “አባቴ” ብሎ ይጠራዋል (26)

    • የዳዊት ቃል ኪዳን የጸና ነው (34-37)

    • ሰው ከመቃብር ሊያመልጥ አይችልም (48)

የዛራዊው የኤታን+ ማስኪል።* 89  የይሖዋ ታማኝ ፍቅር ስለተገለጠባቸው መንገዶች ለዘላለም እዘምራለሁ። ታማኝነትህን ለትውልዶች በሙሉ በአፌ አስታውቃለሁ።   እንዲህ በማለት ተናግሬአለሁና፦ “ታማኝ ፍቅር ለዘላለም ይገነባል፤*+ታማኝነትህንም በሰማያት አጽንተህ መሥርተሃል።”   አንተም እንዲህ ብለሃል፦ “ከመረጥኩት ጋር ቃል ኪዳን ገብቻለሁ፤+ለአገልጋዬ ለዳዊት ምያለሁ፦+   ‘ዘርህ ለዘላለም ጸንቶ እንዲኖር አደርጋለሁ፤+ዙፋንህንም ከትውልድ እስከ ትውልድ አጸናለሁ።’”+ (ሴላ)   ይሖዋ ሆይ፣ ሰማያት ድንቅ ሥራህን፣አዎ፣ በቅዱሳን ጉባኤ ታማኝነትህን ያወድሳሉ።   በሰማያት ከይሖዋ ጋር ማን ሊወዳደር ይችላል?+ ከአምላክ ልጆች*+ መካከል እንደ ይሖዋ ያለ ማን ነው?   አምላክ በቅዱሳን ጉባኤ መካከል እጅግ የተፈራ ነው፤+በዙሪያው ባሉት ሁሉ መካከል ታላቅና እጅግ የሚከበር ነው።+   የሠራዊት አምላክ ይሖዋ ሆይ፣ አንተ ኃያል ነህ፤ያህ ሆይ፣ እንደ አንተ ያለ ማን ነው?+ አንተ በሁሉም ነገር ታማኝ መሆንህን ታሳያለህ።+   የባሕሩን ሞገድ ትቆጣጠራለህ፤+ማዕበሉም ሲነሳ አንተ ራስህ ጸጥ ታሰኘዋለህ።+ 10  አንተ ረዓብን*+ እንደተገደለ ሰው አደቀቅከው።+ በብርቱ ክንድህ ጠላቶችህን በታተንካቸው።+ 11  ሰማያት የአንተ ናቸው፤ ምድርም የአንተ ናት፤+ፍሬያማ የሆነችውን ምድርና በውስጧ ያለውን ነገር ሁሉ የሠራኸው አንተ ነህ።+ 12  ሰሜንንና ደቡብን የፈጠርክ አንተ ነህ፤ታቦርና+ ሄርሞን+ ስምህን በደስታ ያወድሳሉ። 13  ክንድህ ኃያል ነው፤+እጅህ ብርቱ ነው፤+ቀኝ እጅህም ከፍ ከፍ ያለ ነው።+ 14  ጽድቅና ፍትሕ የዙፋንህ መሠረት ናቸው፤+ታማኝ ፍቅርና ታማኝነት በፊትህ ናቸው።+ 15  እልልታ የሚያውቁ ሰዎች ደስተኞች ናቸው።+ ይሖዋ ሆይ፣ እንዲህ ያሉ ሰዎች በፊትህ ብርሃን ይመላለሳሉ። 16  በስምህ ቀኑን ሙሉ ሐሴት ያደርጋሉ፤በጽድቅህም ከፍ ከፍ ይላሉ። 17  አንተ የብርታታቸው ክብር ነህና፤+በሞገስህም ብርታታችን* ከፍ ከፍ ብሏል።+ 18  ጋሻችን ከይሖዋ ነውና፤ንጉሣችን ከእስራኤል ቅዱስ ነው።+ 19  በዚያን ጊዜ ለታማኝ አገልጋዮችህ በራእይ ተናገርክ፤ እንዲህም አልክ፦ “ለኃያል ሰው ብርታት ሰጠሁ፤+ከሕዝቡም መካከል የተመረጠውን ከፍ ከፍ አደረግኩ።+ 20  አገልጋዬን ዳዊትን አገኘሁት፤+በተቀደሰ ዘይቴም ቀባሁት።+ 21  እጄ ይደግፈዋል፤+ክንዴም ያበረታዋል። 22  ማንኛውም ጠላት አያስገብረውም፤የትኛውም ክፉ ሰው አይጨቁነውም።+ 23  ባላጋራዎቹን ከፊቱ አደቃቸዋለሁ፤+የሚጠሉትንም እመታቸዋለሁ።+ 24  ታማኝነቴና ታማኝ ፍቅሬ ከእሱ ጋር ናቸው፤+በስሜም ኃይሉ* ከፍ ከፍ ይላል። 25  እጁን* በባሕሩ ላይ፣ቀኝ እጁንም በወንዞቹ ላይ አደርጋለሁ።+ 26  እሱም ‘አንተ አባቴ ነህ፤አምላኬና አዳኝ ዓለቴ ነህ’+ ብሎ ይጠራኛል። 27  እኔም በኩር እንዲሆን አደርገዋለሁ፤+ከምድር ነገሥታትም ሁሉ በላይ አስቀምጠዋለሁ።+ 28  ታማኝ ፍቅሬን ለዘላለም አሳየዋለሁ፤+ከእሱ ጋር የገባሁት ቃል ኪዳንም ጸንቶ ይኖራል።+ 29  ዘሩን ለዘላለም አጸናለሁ፤ዙፋኑም የሰማያትን ዕድሜ ያህል ጸንቶ እንዲኖር አደርጋለሁ።+ 30  ልጆቹ ሕጌን ቢተዉ፣ድንጋጌዎቼንም* አክብረው ባይመላለሱ፣ 31  ደንቦቼን ቢጥሱናትእዛዛቴን ባይጠብቁ፣ 32  ባለመታዘዛቸው* በበትር እቀጣቸዋለሁ፤+በደል በመፈጸማቸውም እገርፋቸዋለሁ። 33  ሆኖም ለእሱ ታማኝ ፍቅር ማሳየቴን አልተውም፤+የገባሁትንም ቃል አላጥፍም።* 34  ቃል ኪዳኔን አላፈርስም፤+ከአንደበቴ የወጣውንም ቃል አለውጥም።+ 35  ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በቅድስናዬ ምያለሁ፤ዳዊትን አልዋሸውም።+ 36  ዘሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል፤+ዙፋኑ በፊቴ እንዳለችው ፀሐይ ይጸናል።+ 37  በሰማያት ታማኝ ምሥክር ሆና እንደምትኖረው እንደ ጨረቃ፣ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል።” (ሴላ) 38  ሆኖም አንተ ራስህ ጣልከው፤ ደግሞም ገሸሽ አደረግከው፤+በተቀባው አገልጋይህ ላይ እጅግ ተቆጣህ። 39  ከአገልጋይህ ጋር የገባኸውን ቃል ኪዳን ወደ ጎን ገሸሽ አደረግክ፤አክሊሉን* መሬት ላይ በመጣል አረከስከው። 40  በድንጋይ የተገነቡትን ቅጥሮቹን* ሁሉ አፈረስክ፤ምሽጎቹን የፍርስራሽ ክምር አደረግክ። 41  በዚያ የሚያልፉ ሁሉ ዘረፉት፤የጎረቤቶቹም መሳለቂያ ሆነ።+ 42  ባላጋራዎቹ ድል እንዲጎናጸፉ አድርገሃል፤*+ጠላቶቹ ሁሉ ደስ እንዲላቸው አደረግክ። 43  በተጨማሪም ሰይፉን መልሰህበታል፤በጦርነትም እንዲሸነፍ አደረግክ። 44  ግርማ ሞገሱ እንዲጠፋ አደረግክ፤ዙፋኑንም መሬት ላይ ጣልከው። 45  የወጣትነት ዕድሜውን አሳጠርክበት፤ኀፍረትም አከናነብከው። (ሴላ) 46  ይሖዋ ሆይ፣ ራስህን የምትሰውረው እስከ መቼ ነው? ለዘላለም?+ ቁጣህስ እንደ እሳት ሲነድ ይኖራል? 47  ዕድሜዬ ምን ያህል አጭር እንደሆነ አስብ!+ ሰዎችን ሁሉ የፈጠርከው እንዲያው ለከንቱ ነው? 48  ሞትን ጨርሶ ሳያይ በሕይወት ሊኖር የሚችል ሰው ማን ነው?+ ራሱን* ከመቃብር* እጅ ማዳን ይችላል? (ሴላ) 49  ይሖዋ ሆይ፣ በታማኝነትህ ለዳዊት የማልክለት፣በቀደሙት ዘመናት ያሳየኸው ታማኝ ፍቅር የት አለ?*+ 50  ይሖዋ ሆይ፣ በአገልጋዮችህ ላይ የተሰነዘረውን ዘለፋ አስታውስ፤ሰዎች ሁሉ የሰነዘሩብኝን ዘለፋ እንዴት እንደተሸከምኩ* አስብ፤ 51  ይሖዋ ሆይ፣ ጠላቶችህ ምን ያህል እንደተሳደቡ አስታውስ፤የቀባኸውን ሰው እርምጃ ሁሉ እንዴት እንደነቀፉ አስብ። 52  ይሖዋ ለዘላለም ይወደስ። አሜን፣ አሜን።+

የግርጌ ማስታወሻ

ወይም “ጸንቶ ይኖራል።”
ወይም “ከመላእክት።”
ግብፅን ወይም የግብፅን ፈርዖን የሚያመለክት ሊሆን ይችላል።
ቃል በቃል “ቀንዳችን።”
ቃል በቃል “ቀንዱ።”
ወይም “ሥልጣኑን።”
ወይም “ፍርዶቼንም።”
ወይም “በማመፃቸው።”
ቃል በቃል “ታማኝነቴም የውሸት አይሆንም።”
ወይም “ዘውዱን።”
ወይም “የድንጋይ መጠለያዎቹን።”
ቃል በቃል “የባላጋራዎቹን ቀኝ እጅ ከፍ ከፍ አድርገሃል።”
ወይም “ነፍሱን።”
ወይም “ከሲኦል።” የሰው ልጆችን ሁሉ መቃብር ያመለክታል። የቃላት መፍቻውን ተመልከት።
ወይም “ያከናወንካቸው የታማኝ ፍቅር መግለጫዎች የት አሉ?”
ቃል በቃል “በእቅፌ እንደተሸከምኩ።”