መዝሙር 91:1-16
91 በልዑል አምላክ ሚስጥራዊ ቦታ የሚኖር ሰው+ሁሉን ቻይ በሆነው አምላክ ጥላ ሥር ይቀመጣል።+
2 ይሖዋን “አንተ መጠጊያዬና ምሽጌ፣+የምታመንብህም አምላኬ ነህ”+ እለዋለሁ።
3 እሱ ከወፍ አዳኙ ወጥመድ፣ከአውዳሚ ቸነፈርም ይታደግሃልና።
4 በላባዎቹ ይከልልሃል፤*በክንፎቹም ሥር መጠጊያ ታገኛለህ።+
ታማኝነቱ+ ትልቅ ጋሻና+ መከላከያ ቅጥር* ይሆንልሃል።
5 በሌሊት የሚያሸብሩ ነገሮችን፣በቀንም የሚወነጨፍ ፍላጻን አትፈራም፤+
6 በጨለማ የሚያደባ ቸነፈርም ሆነበቀትር የሚረፈርፍ ጥፋት አያስፈራህም።
7 በአጠገብህ ሺህ፣በቀኝህም አሥር ሺህ ይወድቃሉ፤ወደ አንተ ግን አይደርስም።+
8 በክፉዎች ላይ የሚደርሰውን ቅጣት* ትመለከታለህ፤በዓይንህ ብቻ ታየዋለህ።
9 ምክንያቱም “ይሖዋ መጠጊያዬ ነው” ብለሃል፤
ልዑሉን አምላክ መኖሪያህ* አድርገኸዋል፤+
10 ምንም ዓይነት አደጋ አይደርስብህም፤+አንዳችም መቅሰፍት ወደ ድንኳንህ አይጠጋም።
11 በመንገድህ ሁሉ እንዲጠብቁህ+መላእክቱን ስለ አንተ ያዛልና።+
12 እግርህን እንቅፋት እንዳይመታው+በእጃቸው ያነሱሃል።+
13 የአንበሳውን ግልገልና ጉበናውን* ትረግጣለህ፤ደቦል አንበሳውንና ትልቁን እባብ ከእግርህ ሥር ትጨፈልቃለህ።+
14 አምላክ እንዲህ ብሏል፦ “ስለወደደኝ፣* እታደገዋለሁ።+
ስሜን ስለሚያውቅ* እጠብቀዋለሁ።+
15 ይጠራኛል፤ እኔም እመልስለታለሁ።+
በተጨነቀ ጊዜ ከእሱ ጋር እሆናለሁ።+
እታደገዋለሁ እንዲሁም አከብረዋለሁ።
16 ረጅም ዕድሜን አጠግበዋለሁ፤+የማዳን ሥራዎቼንም እንዲያይ* አደርገዋለሁ።”+