መዝሙር 96:1-13

  • “ለይሖዋ አዲስ መዝሙር ዘምሩ”

    • ይሖዋ እጅግ ሊወደስ ይገባዋል (4)

    • የሌሎች ሕዝቦች አማልክት ከንቱ ናቸው (5)

    • ያጌጠ የቅድስና ልብስ ለብሳችሁ ይሖዋን አምልኩ (9)

96  ለይሖዋ አዲስ መዝሙር ዘምሩ።+ መላዋ ምድር ለይሖዋ ትዘምር!+   ለይሖዋ ዘምሩ፤ ስሙንም አወድሱ። የማዳኑን ምሥራች በየቀኑ አውጁ።+   ክብሩን በብሔራት፣አስደናቂ ሥራዎቹንም በሕዝቦች ሁሉ መካከል አስታውቁ።+   ይሖዋ ታላቅ ነው፤ ደግሞም እጅግ ሊወደስ ይገባዋል። ከሌሎች አማልክት ሁሉ በላይ እጅግ የሚፈራ ነው።   የሌሎች ሕዝቦች አማልክት ሁሉ ከንቱ ናቸው፤+ይሖዋ ግን ሰማያትን የሠራ አምላክ ነው።+   ሞገስና* ግርማ በፊቱ ናቸው፤+ብርታትና ውበት በመቅደሱ ውስጥ አሉ።+   እናንተ የሕዝብ ነገዶች፣ ለይሖዋ የሚገባውን ስጡ፤ከክብሩና ከብርታቱ የተነሳ ለይሖዋ የሚገባውን ስጡ።+   ለስሙ የሚገባውን ክብር ለይሖዋ ስጡ፤+ስጦታ ይዛችሁ ወደ ቅጥር ግቢዎቹ ግቡ።   ያጌጠ የቅድስና ልብስ ለብሳችሁ* ለይሖዋ ስገዱ፤*ምድር ሁሉ በፊቱ ተንቀጥቀጪ! 10  በብሔራት መካከል እንዲህ ብላችሁ አስታውቁ፦ “ይሖዋ ነገሠ!+ ምድር* በጽኑ ተመሥርታለች፤ ከቦታዋ ልትንቀሳቀስ አትችልም።* እሱ ለሕዝቦች በትክክል ይፈርዳል።”*+ 11  ሰማያት ሐሴት ያድርጉ፤ ምድርም ደስ ይበላት፤ባሕሩና በውስጡ ያለው ነገር ሁሉ የነጎድጓድ ድምፅ ያሰማ፤+ 12  መስኩና በላዩ ላይ ያለው ሁሉ ሐሴት ያድርግ።+ የዱር ዛፎችም ሁሉ በይሖዋ ፊት እልል ይበሉ።+ 13  እሱ እየመጣ ነውና፤*በምድር ላይ ለመፍረድ እየመጣ ነው። በዓለም* ላይ በጽድቅ፣በሕዝቦችም ላይ በታማኝነት ይፈርዳል።+

የግርጌ ማስታወሻ

ወይም “ክብርና።”
“ከቅድስናው ግርማ የተነሳ” ማለትም ሊሆን ይችላል።
ወይም “ይሖዋን አምልኩ።”
ወይም “ፍሬያማ የሆነችው ምድር።”
ወይም “ልትናወጥ አትችልም።”
ወይም “ይሟገታል።”
ወይም “መጥቷልና።”
ወይም “ፍሬያማ በሆነችው ምድር።”