ሚክያስ 3:1-12
3 እንዲህ አልኩ፦ “እናንተ የያዕቆብ መሪዎችናየእስራኤል ቤት ገዢዎች፣ እባካችሁ ስሙ።+
ትክክል የሆነውን ነገር ማወቅ አይገባችሁም?
2 ሆኖም እናንተ መልካም የሆነውን ትጠላላችሁ፤+ ክፉ የሆነውን ደግሞ ትወዳላችሁ፤+የሕዝቤን ቆዳ ትገፍፋላችሁ፤ ሥጋቸውንም ከአጥንቶቻቸው ትለያላችሁ።+
3 የሕዝቤንም ሥጋ ትበላላችሁ፤+ቆዳቸውንም ትገፍፋላችሁ፤አጥንቶቻቸውንም ትሰባብራላችሁ፤+በድስት ውስጥ እንዳለ አጥንትና በአፍላል* ውስጥ እንዳለ ሥጋ ትቆራርጧቸዋላችሁ።
4 በዚያን ጊዜ እርዳታ ለማግኘት ወደ ይሖዋ ይጮኻሉ፤እሱ ግን አይመልስላቸውም።
ክፉ ድርጊት በመፈጸማቸው፣+በዚያን ጊዜ ፊቱን ይሰውርባቸዋል።+
5 ሕዝቤ እንዲባዝን በሚያደርጉ፣+በጥርሳቸው ሲነክሱ*+ ‘ሰላም!’ እያሉ በሚያውጁ፣+አፋቸው ላይ የሚያደርጉት ነገር በማይሰጣቸው ሰው ሁሉ ላይ ግን ጦርነት በሚያውጁ* ነቢያት ላይ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦
6 ‘ሌሊት ይመጣባችኋል፤+ ራእይም አታዩም፤+ጨለማ ብቻ ይሆንባችኋል፤ ሟርትም አታሟርቱም።
ፀሐይ በነቢያቱ ላይ ትጠልቅባቸዋለች፤ቀኑም ወደ ጨለማ ይለወጥባቸዋል።+
7 ባለ ራእዮች ኀፍረት ይከናነባሉ፤+ሟርተኞችም ይዋረዳሉ።
ከአምላክ ዘንድ መልስ ስለማይኖርሁሉም አፋቸውን* ይሸፍናሉ።’”
8 እኔ በበኩሌ ለያዕቆብ ዓመፁን፣ ለእስራኤልም ኃጢአቱን እንድነግርበይሖዋ መንፈስ ኃይልን፣ፍትሕንና ብርታትን ተሞልቻለሁ።
9 ፍትሕን የምትጸየፉና ቀና የሆነውን ነገር ሁሉ የምታጣምሙ፣+እናንተ የያዕቆብ ቤት መሪዎች፣የእስራኤልም ቤት ገዢዎች፣ እባካችሁ ይህን ስሙ፤+
10 ጽዮንን ደም በማፍሰስ፣ ኢየሩሳሌምንም በዓመፅ የምትገነቡ፣ ስሙ።+
11 መሪዎቿ* በጉቦ ይፈርዳሉ፤+ካህናቷ በክፍያ ያስተምራሉ፤+ነቢያቷም በገንዘብ* ያሟርታሉ።+
ያም ሆኖ “ይሖዋ ከእኛ ጋር አይደለም?+
ምንም ዓይነት ጥፋት አይደርስብንም”+
እያሉ በይሖዋ ይመካሉ።*
12 ስለዚህ በእናንተ የተነሳጽዮን እንደ እርሻ ትታረሳለች፤ኢየሩሳሌም የፍርስራሽ ክምር ትሆናለች፤+የቤቱም* ተራራ፣ በጫካ እንዳሉ ከፍ ያሉ ቦታዎች* ይሆናል።+