ሚክያስ 7:1-20

  • የእስራኤል ብልሹ ሥነ ምግባር (1-6)

    • “የሰው ጠላቶቹ ቤተሰቦቹ ናቸው” (6)

  • “በትዕግሥት እጠብቃለሁ” (7)

  • በአምላክ ሕዝብ ላይ የተሰነዘረው ነቀፋ ይወገዳል (8-13)

  • ሚክያስ ለአምላክ ያቀረበው ጸሎትና ውዳሴ (14-20)

    • ይሖዋ የሰጠው መልስ (15-17)

    • ‘እንደ ይሖዋ ያለ አምላክ ማን ነው?’ (18)

7  ወዮልኝ! የበጋ ፍሬ* ከተሰበሰበናወይን የሚሰበሰብበት ጊዜ አብቅቶቃርሚያ ከተለቀመ በኋላየሚበላ የወይን ዘለላ እንደማያገኝ ሰው ሆኛለሁ፤በጣም የምመኘውን፣* በመጀመሪያው ወቅት የሚደርሰውን በለስም አላገኘሁም።   ታማኝ ሰው ከምድሪቱ ጠፍቷል፤*ከሰው ልጆችም መካከል ቅን የሆነ የለም።+ ሁሉም ደም ለማፍሰስ ያደባሉ።+ እያንዳንዱም የገዛ ወንድሙን በመረብ ያጠምዳል።   እጆቻቸው መጥፎ ነገር በማድረግ የተካኑ ናቸው፤+ገዢው የሆነ ነገር እንዲደረግለት ይጠይቃል፤ፈራጁ ክፍያ ይጠይቃል፤+ታዋቂ የሆነው ሰው የራሱን ፍላጎት ይገልጻል፤*+እነሱም አንድ ላይ ሆነው ያሴራሉ።*   ከእነሱ መካከል የተሻለ የተባለው እንደ እሾህ ነው፤እጅግ ቅን የተባለው ደግሞ ከእሾህ ቁጥቋጦ የከፋ ነው። ጠባቂዎችህ የተናገሩለት፣ አንተ የምትጎበኝበት ቀን ይመጣል።+ እነሱ አሁን ይሸበራሉ።+   ባልንጀራህን አትመን፤ወይም በቅርብ ወዳጅህ አትታመን።+ በእቅፍህ ለምትተኛው ስለምትናገረው ነገር ተጠንቀቅ።   ወንድ ልጅ አባቱን ይንቃልና፤ሴት ልጅ በእናቷ ላይ ትነሳለች፤+ምራት ደግሞ በአማቷ ላይ ትነሳለች፤+የሰው ጠላቶቹ ቤተሰቦቹ ናቸው።+   እኔ ግን ይሖዋን በጉጉት እጠባበቃለሁ።+ የሚያድነኝን አምላክ በትዕግሥት እጠብቃለሁ።*+ አምላኬ ይሰማኛል።+   ጠላቴ ሆይ፣ በእኔ ላይ በደረሰው ነገር ሐሴት አታድርጊ። ብወድቅም እንኳ እነሳለሁ፤በጨለማ ውስጥ ብቀመጥም ይሖዋ ብርሃን ይሆንልኛል።   በእሱ ላይ ኃጢአት ስለሠራሁ+ለእኔ እስኪሟገትልኝና ፍትሕ እንዳገኝ እስከሚያደርግ ድረስየይሖዋን ቁጣ ችዬ እኖራለሁ። እሱ ወደ ብርሃን ያወጣኛል፤እኔም የእሱን ጽድቅ አያለሁ። 10  “አምላክህ ይሖዋ የት አለ?”ስትለኝ የነበረችው ጠላቴም ታያለች፤ ኀፍረትም ትከናነባለች።+ ዓይኖቼም ያዩአታል። በዚያን ጊዜ በጎዳና ላይ እንዳለ ጭቃ የምትረገጥ ቦታ ትሆናለች። 11  የድንጋይ ቅጥሮችሽ የሚገነቡበት ቀን ይሆናል፤በዚያ ቀን ድንበሩ ይሰፋል።* 12  በዚያ ቀን ከአሦርና ከግብፅ ከተሞች፣ከግብፅ አንስቶ እስከ ወንዙ* ድረስ፣ከባሕር እስከ ባሕር፣ ከተራራም እስከ ተራራ ድረስ ያሉ ሰዎችወደ አንቺ ይመጣሉ።+ 13  ምድሪቱም ከነዋሪዎቿና ከሠሩት ነገር* የተነሳባድማ ትሆናለች። 14  ሕዝብህን ይኸውም በጫካ ውስጥ በፍራፍሬ እርሻ መካከል ብቻውን ያለውን፣የርስትህን መንጋ እንደ እረኛ በበትር ጠብቅ።+ እንደ ድሮው ዘመን በባሳንና በጊልያድ ይሰማሩ።+ 15  “ከግብፅ ምድር በወጣችሁበት ዘመን እንደነበረውድንቅ ሥራዎችን አሳያችኋለሁ።+ 16  ብሔራትም ያያሉ፤ ታላቅ ኃይል ቢኖራቸውም ያፍራሉ።+ እጃቸውን በአፋቸው ላይ ይጭናሉ፤ጆሯቸው ይደነቁራል። 17  እንደ እባብ አፈር ይልሳሉ፤+በምድር ላይ እንደሚሳቡ እንስሳት እየተንቀጠቀጡ ከምሽጎቻቸው ይወጣሉ። በፍርሃት ተውጠው ወደ አምላካችን ወደ ይሖዋ ይመጣሉ፤አንተንም ይፈሩሃል።”+ 18  የርስቱን ቀሪዎች+ ኃጢአት ይቅር የሚል፣ በደላቸውንም የሚያልፍእንደ አንተ ያለ አምላክ ማን ነው?+ እሱ ለዘላለም አይቆጣም፤ታማኝ ፍቅር በማሳየት ደስ ይሰኛልና።+ 19  ዳግመኛ ምሕረት ያሳየናል፤+ በደላችንን በቁጥጥሩ ሥር ያደርጋል።* ኃጢአታቸውን ሁሉ ወደ ጥልቅ ባሕር ትጥላለህ።+ 20  በጥንት ዘመን ለአባቶቻችን በማልክላቸው መሠረትለያዕቆብ ታማኝነትን፣ለአብርሃም ደግሞ ታማኝ ፍቅርን ታሳያለህ።+

የግርጌ ማስታወሻ

የበጋ ፍሬ በዋነኝነት የሚያመለክተው “በለስን” ሲሆን “ቴምርንም” ሊጨምር ይችላል።
ወይም “ነፍሴ በጣም የምትመኘውን።”
ወይም “ደብዛው ጠፍቷል።”
ወይም “የነፍሱን ምኞት ይገልጻል።”
ቃል በቃል “ይጎነጉናሉ።”
ወይም “በትዕግሥት የመጠበቅ ዝንባሌ አሳያለሁ።”
“ድንጋጌው ይርቃል” ማለትም ሊሆን ይችላል።
ኤፍራጥስን ያመለክታል።
ቃል በቃል “ከሥራቸው ፍሬ።”
ወይም “ይረግጣል፤ ያሸንፋል።”