የማርቆስ ወንጌል 16:1-8

  • ኢየሱስ ከሞት ተነሳ (1-8)

16  ሰንበት+ ካለፈ በኋላም መግደላዊቷ ማርያም፣ የያዕቆብ እናት ማርያምና+ ሰሎሜ ሄደው አስከሬኑን ሊቀቡ ጥሩ መዓዛ ያላቸው ቅመሞች ገዙ።+  ከዚያም በሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን በማለዳ ፀሐይ ስትወጣ ወደ መቃብሩ መጡ።+  እርስ በርሳቸውም “በመቃብሩ ደጃፍ ላይ ያለውን ድንጋይ ማን ያንከባልልልናል?” ይባባሉ ነበር።  ቀና ብለው ሲመለከቱ ግን በጣም ትልቅ የነበረው ድንጋይ ከቦታው ተንከባሎ አዩ።+  ወደ መቃብሩ ሲገቡ ነጭ ልብስ የለበሰ አንድ ወጣት በቀኝ በኩል ተቀምጦ አዩና ደነገጡ።  እሱም እንዲህ አላቸው፦ “አትደንግጡ።+ በእንጨት ላይ የተሰቀለውን የናዝሬቱን ኢየሱስን እየፈለጋችሁ እንደሆነ አውቃለሁ። እሱ ተነስቷል።+ እዚህ የለም። ተመልከቱ፣ እሱን ያኖሩበት ስፍራ ይኸውና።+  ይልቁንስ ሄዳችሁ ለደቀ መዛሙርቱና ለጴጥሮስ ‘ቀድሟችሁ ወደ ገሊላ ይሄዳል።+ እንደነገራችሁም እዚያ ታዩታላችሁ’ በሏቸው።”+  እነሱም ከመቃብሩ ከወጡ በኋላ በአድናቆት ተውጠው በፍርሃት እየተንቀጠቀጡ ሸሽተው ሄዱ። ከፍርሃታቸውም የተነሳ ለማንም ምንም ነገር አልተናገሩም።*+

የግርጌ ማስታወሻ

ከፍተኛ ተአማኒነት ያላቸው በእጅ የተጻፉ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥንታዊ ቅጂዎች እንደሚያመለክቱት የማርቆስ ወንጌል የሚያበቃው ቁጥር 8 ላይ ነው። ከተጨማሪው መረጃ ላይ ሀ3ን ተመልከት።