የማቴዎስ ወንጌል 1:1-25

  • የኢየሱስ ክርስቶስ የትውልድ ሐረግ (1-17)

  • ኢየሱስ ክርስቶስ የተወለደበት ሁኔታ (18-25)

1  የዳዊት ልጅ፣+ የአብርሃም ልጅ+ የሆነውን የኢየሱስ ክርስቶስን* ታሪክ* የያዘ መጽሐፍ፦   አብርሃም ይስሐቅን ወለደ፤+ይስሐቅ ያዕቆብን ወለደ፤+ያዕቆብ ይሁዳንና+ ወንድሞቹን ወለደ፤   ይሁዳ ከትዕማር ፋሬስንና ዛራን+ ወለደ፤ፋሬስ ኤስሮንን ወለደ፤+ኤስሮን ራምን ወለደ፤+   ራም አሚናዳብን ወለደ፤አሚናዳብ ነአሶንን ወለደ፤+ነአሶን ሰልሞንን ወለደ፤   ሰልሞን ከረዓብ+ ቦዔዝን ወለደ፤ቦዔዝ ከሩት ኢዮቤድን ወለደ፤+ኢዮቤድ እሴይን ወለደ፤+   እሴይ ንጉሥ ዳዊትን ወለደ።+ ዳዊት ከኦርዮ ሚስት ሰለሞንን ወለደ፤+   ሰለሞን ሮብዓምን ወለደ፤+ሮብዓም አቢያህን ወለደ፤አቢያህ አሳን ወለደ፤+   አሳ ኢዮሳፍጥን ወለደ፤+ኢዮሳፍጥ ኢዮራምን ወለደ፤+ኢዮራም ዖዝያን ወለደ፤   ዖዝያ ኢዮዓታምን ወለደ፤+ኢዮዓታም አካዝን ወለደ፤+አካዝ ሕዝቅያስን ወለደ፤+ 10  ሕዝቅያስ ምናሴን ወለደ፤+ምናሴ አምዖንን ወለደ፤+አምዖን ኢዮስያስን ወለደ፤+ 11  ኢዮስያስ+ አይሁዳውያን ወደ ባቢሎን በተጋዙበት ዘመን+ ኢኮንያንን+ እና ወንድሞቹን ወለደ። 12  ወደ ባቢሎን ከተጋዙ በኋላ ኢኮንያን ሰላትያልን ወለደ፤ሰላትያል ዘሩባቤልን ወለደ፤+ 13  ዘሩባቤል አብዩድን ወለደ፤አብዩድ ኤልያቄምን ወለደ፤ኤልያቄም አዞርን ወለደ፤ 14  አዞር ሳዶቅን ወለደ፤ሳዶቅ አኪምን ወለደ፤አኪም ኤልዩድን ወለደ፤ 15  ኤልዩድ አልዓዛርን ወለደ፤አልዓዛር ማታንን ወለደ፤ማታን ያዕቆብን ወለደ፤ 16  ያዕቆብ ዮሴፍን ወለደ፤ ዮሴፍም ክርስቶስ የተባለውን ኢየሱስን የወለደችው የማርያም ባል ነበር።+ 17  ስለዚህ ጠቅላላው ትውልድ፣ ከአብርሃም እስከ ዳዊት 14 ትውልድ፣ ከዳዊት አንስቶ አይሁዳውያን ወደ ባቢሎን እስከተጋዙበት ጊዜ ድረስ 14 ትውልድ እንዲሁም ወደ ባቢሎን ከተጋዙበት ዘመን እስከ ክርስቶስ ድረስ 14 ትውልድ ነው። 18  ይሁንና ኢየሱስ ክርስቶስ የተወለደበት ሁኔታ እንደሚከተለው ነው፦ እናቱ ማርያም ለዮሴፍ ታጭታ በነበረበት ጊዜ፣ አብረው መኖር ከመጀመራቸው በፊት በመንፈስ ቅዱስ* ፀንሳ ተገኘች።+ 19  ይሁን እንጂ ባሏ* ዮሴፍ ጻድቅ ስለሆነና በይፋ ሊያጋልጣት ስላልፈለገ በስውር ሊፈታት አሰበ።+ 20  ሆኖም ይህን ለማድረግ አስቦ ሳለ የይሖዋ* መልአክ በሕልም ተገልጦለት እንዲህ አለው፦ “የዳዊት ልጅ ዮሴፍ ሆይ፣ ሚስትህ ማርያም የፀነሰችው በመንፈስ ቅዱስ ስለሆነ+ እሷን ወደ ቤት ለመውሰድ አትፍራ። 21  ወንድ ልጅ ትወልዳለች፤ እሱንም ኢየሱስ* ብለህ ትጠራዋለህ፤+ ሕዝቡን ከኃጢአታቸው ያድናቸዋልና።”+ 22  ይህ ሁሉ የሆነው ይሖዋ* በነቢዩ በኩል እንዲህ ሲል የተናገረው ይፈጸም ዘንድ ነው፦ 23  “እነሆ! ድንግል ትፀንሳለች፤ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፤ ስሙንም አማኑኤል+ ይሉታል”፤ ትርጉሙም “አምላክ ከእኛ ጋር ነው”+ ማለት ነው። 24  ከዚያም ዮሴፍ ከእንቅልፉ ነቃ፤ የይሖዋ* መልአክ ባዘዘውም መሠረት ሚስቱን ወደ ቤቱ ወሰዳት። 25  ሆኖም ልጁን እስክትወልድ ድረስ ከእሷ ጋር የፆታ ግንኙነት አልፈጸመም፤+ ልጁንም ኢየሱስ ብሎ ጠራው።+

የግርጌ ማስታወሻ

ወይም “የትውልድ ሐረግ።”
“ቅቡዕ፤ መሲሕ” የሚል ትርጉም አለው።
በሥራ ላይ ያለን ኃይል ያመለክታል።
በአይሁዳውያን ባሕል መሠረት የተጫጩ ሰዎች እንደተጋቡ ይቆጠራል።
በዚህ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም፣ በክርስቲያን ግሪክኛ ቅዱሳን መጻሕፍት ላይ “ይሖዋ” የሚለው መለኮታዊ ስም ከሚገኝባቸው 237 ቦታዎች ውስጥ ይህ የመጀመሪያው ነው።ከተጨማሪው መረጃ ላይ ከተጨማሪው መረጃ ላይ ሀ5ን ተመልከት።
የሹዋ ወይም ኢያሱ ከተባለው የዕብራይስጥ ስም ጋር ተመሳሳይ ሲሆን “ይሖዋ አዳኝ ነው” የሚል ትርጉም አለው።
ከተጨማሪው መረጃ ላይ ሀ5ን ተመልከት።
ከተጨማሪው መረጃ ላይ ሀ5ን ተመልከት።