በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የምሳሌ መጽሐፍ

ምዕራፎች

የመጽሐፉ ይዘት

  • 1

    • የምሳሌዎቹ ዓላማ (1-7)

    • መጥፎ ጓደኝነት የሚያስከትለው መዘዝ (8-19)

    • እውነተኛ ጥበብ በአደባባይ ትጮኻለች (20-33)

  • 2

    • ጥበብ ያላት የላቀ ዋጋ (1-22)

      • ጥበብን እንደተሸሸገ ሀብት አጥብቆ መሻት (4)

      • የማመዛዘን ችሎታ ይጠብቅሃል (11)

      • የሥነ ምግባር ብልግና ለውድቀት ይዳርጋል (16-19)

  • 3

    • ጥበበኛ ሁን፤ በይሖዋ ታመን (1-12)

      • ባሉህ ውድ ነገሮች ይሖዋን አክብር (9)

    • ጥበብ ደስታ ታስገኛለች (13-18)

    • ጥበብ ጥበቃ ታስገኛለች (19-26)

    • ሌሎችን በአግባቡ መያዝ (27-35)

      • ‘ለሌሎች መልካም ነገር ከማድረግ ወደኋላ አትበል’ (27)

  • 4

    • ጥበብ ያዘለ አባታዊ ምክር (1-27)

      • ከምንም በላይ ጥበብን አግኝ (7)

      • ከክፉ ጎዳና ራቅ (14, 15)

      • የጻድቃን መንገድ እየደመቀ ይሄዳል (18)

      • “ልብህን ጠብቅ” (23)

  • 5

    • ሥነ ምግባር ከጎደላት ሴት ራቅ (1-14)

    • ከሚስትህ ጋር ደስ ይበልህ (15-23)

  • 6

    • ዋስ መሆን ችግር ሊያስከትል ይችላል (1-5)

    • “አንተ ሰነፍ፣ ወደ ጉንዳን ሂድ” (6-11)

    • የማይረባና ክፉ ሰው (12-15)

    • ይሖዋ የሚጠላቸው ሰባት ነገሮች (16-19)

    • ከክፉ ሴት ራስህን ጠብቅ (20-35)

  • 7

    • የአምላክን ትእዛዛት ጠብቅ፤ በሕይወትም ትኖራለህ (1-5)

    • አንድ ሞኝ ወጣት ተታለለ (6-27)

      • “ለእርድ እንደሚነዳ በሬ” (22)

  • 8

    • ጥበብ በሰው ተመስላ ተናገረች (1-36)

      • ‘አምላክ ከሥራዎቹ ቀዳሚ አደረገኝ’ (22)

      • ‘የተዋጣለት ሠራተኛ ሆኜ ከአምላክ ጎን ነበርኩ’ (30)

      • “በሰው ልጆች እጅግ እደሰት ነበር” (31)

  • 9

    • እውነተኛ ጥበብ ትጣራለች (1-12)

      • “በእኔ ምክንያት ዘመንህ ይረዝማል” (11)

    • ማስተዋል የጎደላት ሴት ትጣራለች (13-18)

      • “የተሰረቀ ውኃ ይጣፍጣል” (17)

  • የሰለሞን ምሳሌዎች (10:1–24:34)

    • 10

      • ጥበበኛ ልጅ አባቱን ደስ ያሰኛል (1)

      • ‘ትጉ እጆች ብልጽግና ያስገኛሉ’ (4)

      • “ከቃላት ብዛት ስህተት አይታጣም” (19)

      • “የይሖዋ በረከት ባለጸጋ ታደርጋለች” (22)

      • “ይሖዋን መፍራት ዕድሜን ያስረዝማል” (27)

    • 11

      • ‘ልካቸውን በሚያውቁ ዘንድ ጥበብ ትገኛለች’ (2)

      • ከሃዲ ሰው ሌሎችን ለጥፋት ይዳርጋል (9)

      • ‘ብዙ አማካሪዎች ባሉበት ስኬት ይገኛል’ (14)

      • “ለጋስ ሰው ይበለጽጋል” (25)

      • “በሀብቱ የሚታመን ሰው ይወድቃል” (28)

    • 12

      • ‘ወቀሳን የሚጠላ የማመዛዘን ችሎታ ይጎድለዋል’ (1)

      • “ሳይታሰብበት የሚነገር ቃል እንደ ሰይፍ ይወጋል” (18)

      • ‘ሰላምን የሚያራምዱ ደስታ አላቸው’ (20)

      • “ይሖዋ ውሸታም ከንፈሮችን ይጸየፋል” (22)

      • ጭንቀት ልብን ያዝላል (25)

    • 13

      • ምክር የሚሹ ጥበበኞች ናቸው (10)

      • “የዘገየ ተስፋ ልብን ያሳምማል” (12)

      • ‘ታማኝ መልእክተኛ ፈውስ ያመጣል’ (17)

      • “ከጥበበኞች ጋር የሚሄድ ጥበበኛ ይሆናል” (20)

      • ተግሣጽ የፍቅር መግለጫ ነው (24)

    • 14

      • “ልብ የራሱን ምሬት ያውቃል” (10)

      • ትክክል መስሎ የሚታይ መንገድ ወደ ሞት ሊመራ ይችላል (12)

      • “ተላላ ቃልን ሁሉ ያምናል” (15)

      • ‘የባለጸጋ ወዳጆች ብዙ ናቸው’ (20)

      • “የሰከነ ልብ ለሰውነት ሕይወት ይሰጣል” (30)

    • 15

      • “የለዘበ መልስ ቁጣን ያበርዳል” (1)

      • “የይሖዋ ዓይኖች በሁሉም ቦታ ናቸው” (3)

      • ‘የቅኖች ጸሎት አምላክን ደስ ያሰኛል’ (8)

      • “መመካከር ከሌለ የታቀደው ነገር ሳይሳካ ይቀራል” (22)

      • መልስ ከመስጠትህ በፊት አሰላስል (28)

    • 16

      • ‘ይሖዋ ውስጣዊ ዓላማን ይመረምራል’ (2)

      • ሥራህን ለይሖዋ አደራ ስጥ (3)

      • ‘ትክክለኛ ሚዛን ከይሖዋ ነው’ (11)

      • ‘ኩራት ጥፋትን ይቀድማል’ (18)

      • ‘ሽበት የውበት ዘውድ ነው’ (31)

    • 17

      • ለመልካም ነገር ክፉ አትመልስ (13)

      • “ጥል ከመነሳቱ በፊት ከአካባቢው ራቅ” (14)

      • “እውነተኛ ወዳጅ ምንጊዜም አፍቃሪ ነው” (17)

      • “ደስተኛ ልብ ጥሩ መድኃኒት ነው” (22)

      • ጥልቅ ግንዛቤ ያለው ሰው ንግግሩ ቁጥብ ነው (27)

    • 18

      • ራስን ማግለል ራስ ወዳድነትና ጥበብ የጎደለው ነው (1)

      • “የይሖዋ ስም ጽኑ ግንብ ነው” (10)

      • ሀብት ጥበቃ አያስገኝም (11)

      • ሁለቱንም ወገኖች መስማት ጥበብ ነው (17)

      • “ከወንድም ይበልጥ የሚቀርብ ጓደኛ” (24)

    • 19

      • ጥልቅ ማስተዋል ያለው ሰው ቶሎ አይቆጣም (11)

      • ‘ጨቅጫቃ ሚስት እንደሚያንጠባጥብ ጣሪያ ናት’ (13)

      • ‘ልባም ሚስት የምትገኘው ከይሖዋ ነው’ (14)

      • “ገና ተስፋ ሳለ ልጅህን ገሥጽ” (18)

      • ምክርን መስማት ጥበብ ነው (20)

    • 20

      • የወይን ጠጅ ፌዘኛ ያደርጋል (1)

      • ‘ሰነፍ በክረምት አያርስም’ (4)

      • የሰው ሐሳብ እንደ ጥልቅ ውኃ ነው (5)

      • በችኮላ ስእለት ከመሳል ተቆጠብ (25)

      • “የወጣቶች ክብር ጉልበታቸው ነው” (29)

    • 21

      • ይሖዋ የንጉሥን ልብ ይመራል (1)

      • ፍትሕ መሥዋዕት ከማቅረብ ይሻላል (3)

      • ትጋት ለስኬት ያበቃል (5)

      • የችግረኛውን ጩኸት የማይሰማ ራሱም ሰሚ አያገኝም (13)

      • ይሖዋን የሚጻረር ጥበብ ከንቱ ነው (30)

    • 22

      • “መልካም ስም ከብዙ ሀብት ይመረጣል” (1)

      • በልጅነት የሚሰጥ ሥልጠና ዘላቂ ጥቅም አለው (6)

      • ሰነፍ “ውጭ አንበሳ አለ!” ይላል (13)

      • ተግሣጽ ሞኝነትን ያስወግዳል (15)

      • በሥራው የተካነ በነገሥታት ፊት ይቆማል (29)

    • 23

      • ግብዣ ላይ ስትገኝ አስተዋይ ሁን (2)

      • ሀብት አታሳድ (4)

      • ሀብት በሮ ሊጠፋ ይችላል (5)

      • ብዙ የወይን ጠጅ ከሚጠጡ ጋር አትሁን (20)

      • መጠጥ እንደ እባብ ይናደፋል (32)

    • 24

      • “በክፉ ሰዎች አትቅና” (1)

      • “ቤት በጥበብ ይገነባል” (3)

      • ጻድቅ ቢወድቅ እንኳ ይነሳል (16)

      • “እንዳደረገብኝ እንዲሁ አደርግበታለሁ” አትበል (29)

      • ማንቀላፋት ድህነት ያስከትላል (33, 34)

  • የንጉሥ ሕዝቅያስ ሰዎች የጻፏቸው የሰለሞን ምሳሌዎች (25:1–29:27)

    • 25

      • ሚስጥር መጠበቅ (9)

      • የተመረጡ ቃላት (11)

      • “ባልንጀራህ ቤት እግር አታብዛ” (17)

      • በጠላት ራስ ላይ ፍም መከመር (21, 22)

      • መልካም ወሬ እንደ ቀዝቃዛ ውኃ ነው (25)

    • 26

      • ስለ ሰነፍ ሰው የተሰጠ መግለጫ (13-16)

      • በሌሎች ጠብ አትግባ (17)

      • ከአጉል ቀልድ ራቅ (18, 19)

      • “እንጨት ከሌለ እሳት ይጠፋል” (20, 21)

      • ስም አጥፊ የሚናገረው ቃል እንደ ጣፋጭ ምግብ ነው (22)

    • 27

      • የወዳጅ ወቀሳ ጠቃሚ ነው (5, 6)

      • ልጄ ሆይ፣ ልቤን ደስ አሰኘው (11)

      • ብረት ብረትን ይስላል (17)

      • መንጋህን በሚገባ እወቅ (23)

      • “ሀብት ለዘላለም አይኖርም” (24)

    • 28

      • ሕግን የማይሰማ ሰው ጸሎት አስጸያፊ ነው (9)

      • ኃጢአቱን የሚናዘዝ ምሕረት ያገኛል (13)

      • ለሀብት የሚጣደፍ ንጽሕናውን ያጎድፋል (20)

      • ወቀሳ ከሽንገላ ይሻላል (23)

      • ለጋስ አይቸገርም (27)

    • 29

      • መረን የተለቀቀ ልጅ ለውርደት ይዳርጋል (15)

      • “ራእይ ከሌለ ሕዝብ እንዳሻው ይሆናል” (18)

      • “የሚቆጣ ሰው ጠብ ያስነሳል” (22)

      • ትሑት ሰው ክብር ይጎናጸፋል (23)

      • “ሰውን መፍራት ወጥመድ ነው” (25)

  • 30

    • አጉር የተናገራቸው ቃላት (1-33)

      • “ድሃም ሆነ ባለጸጋ አታድርገኝ” (8)

      • ፈጽሞ የማይጠግቡ ነገሮች (15, 16)

      • ለመገንዘብ አዳጋች የሆኑ ነገሮች (18, 19)

      • አመንዝራ ሴት (20)

      • በደመ ነፍስ ጥበበኞች የሆኑ እንስሳት (24)

  • 31

    • የንጉሥ ልሙኤል ቃል (1-31)

      • ባለሙያ ሚስትን ማን ሊያገኛት ይችላል? (10)

      • ታታሪና ትጉ ሠራተኛ ናት (17)

      • ‘የደግነት ሕግ በአንደበቷ አለ’ (26)

      • ልጆቿና ባሏ ያወድሷታል (28)

      • ውበትና ቁንጅና አላፊ ነው (30)