ምሳሌ 13:1-25
13 ጥበበኛ ልጅ የአባቱን ተግሣጽ ይቀበላል፤+ፌዘኛ ግን ተግሣጽን* አይሰማም።+
2 ሰው ከአፉ ፍሬ መልካም ነገር ይበላል፤+ከዳተኞች* ግን ዓመፅን ይመኛሉ።
3 አፉን የሚጠብቅ ሕይወቱን ይጠብቃል።*+
አፉን የሚከፍት ግን ይጠፋል።+
4 ሰነፍ ሰው ይመኛል፤ ነገር ግን ምንም አያገኝም፤*+ትጉ ሰው* ግን በሚገባ ይጠግባል።*+
5 ጻድቅ ውሸትን ይጠላል፤+የክፉ ሰው ድርጊት ግን ኀፍረትና ውርደት ያመጣበታል።
6 በመንገዱ ነቀፋ የሌለበትን ሰው ጽድቅ ትጠብቀዋለች፤+ክፋት ግን ኃጢአተኛውን ትጥለዋለች።
7 ምንም ሳይኖረው ባለጸጋ መስሎ ለመታየት የሚሞክር ሰው አለ፤+ሌላው ደግሞ ብዙ ሀብት እያለው ድሃ መስሎ ይኖራል።
8 የሰው ሀብት ለሕይወቱ* ቤዛ ነው፤+ድሃ ግን ምንም ዓይነት ስጋት የለበትም።+
9 የጻድቃን ብርሃን ደምቆ ይበራል፤*+የክፉዎች መብራት ግን ይጠፋል።+
10 እብሪተኝነት ጠብ ከመፍጠር ውጭ የሚያመጣው ነገር የለም፤+ምክር በሚሹ* ዘንድ ግን ጥበብ ትገኛለች።+
11 በፍጥነት የተገኘ ሀብት* ይመናመናል፤+ጥቂት በጥቂት የሚያጠራቅም* ሰው ግን ሀብቱ ይጨምራል።
12 የዘገየ ተስፋ ልብን ያሳምማል፤+የተሳካ ምኞት ግን የሕይወት ዛፍ ነው።+
13 መመሪያን የሚንቅ* ሁሉ ይቀጣል፤+ትእዛዝን የሚያከብር ግን ብድራት ያገኛል።+
14 የጥበበኛ ሰው ትምህርት* የሕይወት ምንጭ ነው፤+ሰውን ከሞት ወጥመድ እንዲያመልጥ ይረዳዋል።
15 ጥልቅ ማስተዋል ሞገስ ያስገኛል፤የከዳተኞች መንገድ ግን አስቸጋሪ ነው።
16 ብልህ ሰው ተግባሩን በእውቀት ያከናውናል፤+ሞኝ ሰው ግን የገዛ ራሱን ሞኝነት ይገልጣል።+
17 ክፉ መልእክተኛ ችግር ውስጥ ይወድቃል፤+ታማኝ መልእክተኛ ግን ፈውስ ያመጣል።+
18 ተግሣጽን ችላ የሚል ሁሉ ይደኸያል፤ ይዋረዳልም፤እርማትን የሚቀበል* ግን ይከበራል።+
19 ሰው* የተመኘው ነገር ሲፈጸም ደስ ይለዋል፤+ሞኞች ግን ከክፋት መራቅን ይጸየፋሉ።+
20 ከጥበበኞች ጋር የሚሄድ ጥበበኛ ይሆናል፤+ከሞኞች ጋር የሚገጥም ግን ጉዳት ይደርስበታል።+
21 ኃጢአተኞችን ጥፋት ያሳድዳቸዋል፤+ጻድቃንን ግን ብልጽግና ይክሳቸዋል።+
22 ጥሩ ሰው ለልጅ ልጆቹ ውርስ ይተዋል፤የኃጢአተኛ ሀብት ግን ለጻድቅ ይከማቻል።+
23 የድሃ እርሻ ብዙ እህል ያስገኛል፤ሆኖም ከፍትሕ መጓደል የተነሳ ተጠራርጎ ይጠፋል።*
24 ልጁን በበትር ከመምታት* ወደኋላ የሚል ይጠላዋል፤+የሚወደው ግን ተግቶ* ይገሥጸዋል።+
25 ጻድቅ ይበላል፤ የምግብ ፍላጎቱንም * ያረካል፤+የክፉ ሰው ሆድ ግን ባዶ ነው።+
የግርጌ ማስታወሻ
^ ወይም “እርማትን።”
^ ወይም “የከዳተኞች ነፍስ።”
^ ወይም “ተጠንቅቆ የሚናገር ነፍሱን ይጠብቃል።”
^ ወይም “ነፍሱ ምንም አታገኝም።”
^ ወይም “ነፍስ።”
^ ቃል በቃል “ትሰባለች።”
^ ወይም “ለነፍሱ።”
^ ቃል በቃል “ሐሴት ያደርጋል።”
^ ወይም “እርስ በርስ በሚመካከሩ።”
^ ወይም “ከምንም ተነስቶ የተገኘ ሀብት።”
^ ቃል በቃል “በእጁ የሚሰበስብ።”
^ ወይም “ቃልን የሚንቅ።”
^ ወይም “ሕግ።”
^ ወይም “ወቀሳን የሚቀበል።”
^ ወይም “ነፍስ።”
^ ወይም “እሱ ይጠፋል።”
^ ወይም “ልጁን ከመገሠጽ፤ ልጁን ከመቅጣት።”
^ “ወዲያው” ማለትም ሊሆን ይችላል።
^ ወይም “ነፍሱንም።”