ምሳሌ 17:1-28
17 ጠብ እያለ ትልቅ ድግስ ከተደገሰበት* ቤት ይልቅሰላም* ባለበት ደረቅ የዳቦ ቁራሽ መብላት ይሻላል።+
2 ጥልቅ ማስተዋል ያለው አገልጋይ አሳፋሪ ድርጊት በሚፈጽም ልጅ ላይ ሥልጣን ይኖረዋል፤ከወንድማማቾቹ እንደ አንዱ ውርስ ይካፈላል።
3 ማቅለጫ ለብር፣ ምድጃ ለወርቅ ነው፤+ልብን የሚመረምር ግን ይሖዋ ነው።+
4 ክፉ ሰው ጎጂ የሆነን ንግግር በትኩረት ያዳምጣል፤አታላይ ሰውም ተንኮለኛ የሆነን አንደበት ያዳምጣል።+
5 በድሃ የሚያፌዝ ሁሉ ፈጣሪውን ይሳደባል፤+በሌላው ሰው ላይ በደረሰው መከራ የሚደሰትም ሁሉ ከቅጣት አያመልጥም።+
6 የልጅ ልጆች* የሽማግሌዎች ዘውድ ናቸው፤አባቶችም * ለወንዶች ልጆቻቸው* ክብር ናቸው።
7 ለሞኝ ሰው ቀና* ንግግር አይስማማውም።+
ለገዢ* ደግሞ ሐሰተኛ ንግግር ጨርሶ አይሆነውም!+
8 ስጦታ ለባለቤቱ እንደከበረ ድንጋይ* ነው፤+በሄደበት ሁሉ ስኬት ያስገኝለታል።+
9 በደልን ይቅር የሚል* ሁሉ ፍቅርን ይሻል፤+አንድን ጉዳይ ደጋግሞ የሚያወራ ግን የልብ ጓደኛሞችን ይለያያል።+
10 ሞኝን ሰው መቶ ጊዜ ከመግረፍ ይልቅ+ማስተዋል ያለውን ሰው አንድ ጊዜ መገሠጽ የተሻለ ውጤት ያስገኛል።+
11 ክፉ ሰው የሚሻው ዓመፅን ብቻ ነው፤ሆኖም እሱን እንዲቀጣ ጨካኝ መልእክተኛ ይላክበታል።+
12 የቂል ሥራ እየሠራ ካለ ሞኝ ሰው ጋር ከመገናኘት ይልቅግልገሎቿን ካጣች ድብ ጋር መገናኘት ይሻላል።+
13 ማንኛውም ሰው ለመልካም ነገር ክፉ የሚመልስ ከሆነክፉ ነገር ከቤቱ አይጠፋም።+
14 ጠብ መጫር ግድብን ከመሸንቆር* ተለይቶ አይታይም፤ስለዚህ ጥል ከመነሳቱ በፊት ከአካባቢው ራቅ።+
15 ክፉውን ነፃ የሚያደርግ፣ በጻድቁም ላይ የሚፈርድ፣+ሁለቱም በይሖዋ ዘንድ አስጸያፊ ናቸው።
16 ሞኝ ሰው ጥበብን የራሱ የሚያደርግበት ልብ* ከሌለውጥበብ የሚያገኝበት መንገድ ቢኖር ምን ይጠቅማል?+
17 እውነተኛ ወዳጅ ምንጊዜም አፍቃሪ ነው፤+ደግሞም ለመከራ ቀን የተወለደ ወንድም ነው።+
18 ማስተዋል የጎደለው ሰውበባልንጀራው ፊት እጅ በመጨበጥ ዋስ* ለመሆን ይስማማል።+
19 ጠብ የሚወድ ሁሉ በደልን ይወዳል።+
በሩን ወደ ላይ አስረዝሞ የሚሠራ ጥፋትን ይጋብዛል።+
20 ልቡ ጠማማ የሆነ አይሳካለትም፤*+በምላሱም የሚያታልል ጥፋት ይደርስበታል።
21 የሞኝ ልጅ አባት ሐዘን ላይ ይወድቃል፤የማመዛዘን ችሎታ የጎደለው ልጅ የወለደም ደስታ አይኖረውም።+
22 ደስተኛ ልብ ጥሩ መድኃኒት ነው፤*+የተደቆሰ መንፈስ ግን ኃይል ያሟጥጣል።*+
23 ክፉ ሰው ፍትሕን ለማዛባትበስውር* ጉቦ ይቀበላል።+
24 ጥልቅ ግንዛቤ ባለው ሰው ፊት ጥበብ ትገኛለች፤የሞኝ ሰው ዓይን ግን እስከ ምድር ዳርቻ ይንከራተታል።+
25 ሞኝ ልጅ በአባቱ ላይ ሐዘን ያስከትላል፤እናቱም እንድትመረር ያደርጋል።+
26 ጻድቁን መቅጣት* መልካም አይደለም።
የተከበሩ ሰዎችንም መግረፍ ትክክል አይደለም።
27 አዋቂ ሰው ንግግሩ ቁጥብ ነው፤+ጥልቅ ግንዛቤ ያለው ሰውም የተረጋጋ ነው።*+
28 ሞኝ ሰው እንኳ ዝም ሲል እንደ ጥበበኛ ይቆጠራል፤ከንፈሮቹንም የሚዘጋ ማስተዋል እንዳለው ተደርጎ ይታያል።
የግርጌ ማስታወሻ
^ ወይም “ጸጥታ።”
^ ቃል በቃል “መሥዋዕቶች ከሞሉበት።”
^ ቃል በቃል “ወንዶች የልጅ ልጆች።”
^ ወይም “ወላጆችም።”
^ ወይም “ለልጆቻቸው።”
^ ወይም “ለተከበረ ሰው።”
^ ወይም “መልካም።”
^ ወይም “ሞገስ የሚያስገኝ ድንጋይ።”
^ ቃል በቃል “የሚሸፍን።”
^ ቃል በቃል “ውኃን ከመልቀቅ።”
^ ወይም “ማስተዋል።”
^ ወይም “ተያዥ።”
^ ቃል በቃል “መልካም ነገር አያገኝም።”
^ ወይም “ፈውስ ያስገኛል።”
^ ወይም “አጥንትን ያደርቃል።”
^ ቃል በቃል “ከሰው ጉያ።”
^ ወይም “መቀጫ ማስከፈል።”
^ ቃል በቃል “መንፈሱ ቀዝቃዛ ነው።”