ምሳሌ 2:1-22

  • ጥበብ ያላት የላቀ ዋጋ (1-22)

    • ጥበብን እንደተሸሸገ ሀብት አጥብቆ መሻት (4)

    • የማመዛዘን ችሎታ ይጠብቅሃል (11)

    • የሥነ ምግባር ብልግና ለውድቀት ይዳርጋል (16-19)

2  ልጄ ሆይ፣ ቃሌን ብትቀበልናትእዛዛቴን እንደ ውድ ሀብት ብታስቀምጥ፣+   ይህን ለማድረግ ጆሮህን ወደ ጥበብ ብታቀና፣+ጥልቅ ግንዛቤ ለማግኘት ልብህን ብታዘነብል፣+   ደግሞም ማስተዋልን ብትጣራና+ጥልቅ ግንዛቤ ለማግኘት ድምፅህን ብታሰማ፣+   እንደ ብር ተግተህ ብትፈልጋት፣+እንዲሁም እንደተሸሸገ ሀብት አጥብቀህ ብትሻት፣+   ያን ጊዜ ይሖዋን መፍራት ምን ማለት እንደሆነ ትረዳለህ፤+ደግሞም ስለ አምላክ እውቀት ትቀስማለህ።+   ይሖዋ ራሱ ጥበብ ይሰጣልና፤+ከአፉ እውቀትና ጥልቅ ግንዛቤ ይወጣል።   ለቅኖች ጥበብን* እንደ ውድ ሀብት ያከማቻል፤ንጹሕ አቋማቸውን* ጠብቀው ለሚመላለሱት ጋሻ ነው።+   የፍትሕን ጎዳና ይከታተላል፤የታማኞቹንም መንገድ ይጠብቃል።+   በዚህ ጊዜ ጽድቅ፣ ፍትሕና ትክክል የሆነውን ነገርይኸውም የጥሩነትን ጎዳና በሙሉ ትረዳለህ።+ 10  ጥበብ ወደ ልብህ ስትገባና+እውቀት ነፍስህን* ደስ ስታሰኝ፣+ 11  የማመዛዘን ችሎታ ምንጊዜም ይጠብቅሃል፤+ጥልቅ ግንዛቤም ይጋርድሃል፤ 12  ይህም አንተን ከክፉ መንገድ ለማዳንእንዲሁም ጠማማ ነገር ከሚናገር ሰው፣+ 13  በጨለማ መንገድ ለመጓዝቀናውን ጎዳና ከሚተዉ፣+ 14  መጥፎ ድርጊት በመፈጸም ሐሴት ከሚያደርጉ፣ጠማማ በሆኑ ክፉ ነገሮች ከሚደሰቱ፣ 15  መንገዳቸው ጠማማ ከሆነናአካሄዳቸው በተንኮል ከተሞላ ሰዎች አንተን ለመታደግ ነው። 16  ጋጠወጥ* ከሆነች ሴት፣ባለጌ* ሴት ከምትናገረው የሚያባብል* ቃል ያድንሃል፤+ 17  ይህች ሴት በወጣትነቷ የነበራትን የቅርብ ወዳጇን*+ የምትተውእንዲሁም ከአምላኳ ጋር የገባችውን ቃል ኪዳን የምትረሳ ናት፤ 18  ቤቷ ሰውን ይዞ ወደ ሞት ይወርዳልና፤አካሄዷም* በሞት ወደተረቱት ይወስዳል።+ 19  ከእሷ ጋር ግንኙነት ያላቸው* ሁሉ አይመለሱም፤የሕይወትንም መንገድ ዳግመኛ አያገኙም።+ 20  በመሆኑም የጥሩ ሰዎችን መንገድ ተከተል፤እንዲሁም ከጻድቃን ጎዳና አትውጣ፤+ 21  በምድር ላይ የሚኖሩት ቅኖች ብቻ ናቸውና፤በእሷም ላይ የሚቀሩት ነቀፋ የሌለባቸው* ናቸው።+ 22  ክፉዎች ግን ከምድር ገጽ ይጠፋሉ፤+ከዳተኞችም ከእሷ ይወገዳሉ።+

የግርጌ ማስታወሻ

ወይም “ማስተዋል የታከለበት ጥበብን።”
እዚህ ላይ የገባው የዕብራይስጥ ቃል የሥነ ምግባር ንጽሕናን፣ ሁለት ልብ አለመሆንንና እንከን የለሽ መሆንን ያመለክታል።
ቃል በቃል “እንግዳ።” ከምትከተለው የሥነ ምግባር አቋም የተነሳ ከአምላክ ጋር የተቆራረጠችን ሴት የሚያመለክት ሳይሆን አይቀርም።
ቃል በቃል “ባዕድ።” ከምትከተለው የሥነ ምግባር አቋም የተነሳ ከአምላክ የራቀችን ሴት የሚያመለክት ሳይሆን አይቀርም።
ወይም “የሚያማልል።”
ወይም “ባሏን።”
ቃል በቃል “መንገዷም።”
ቃል በቃል “ወደ እሷ የሚገቡ።”
ወይም “ንጹሕ አቋማቸውን የሚጠብቁ።”