ምሳሌ 22:1-29

  • “መልካም ስም ከብዙ ሀብት ይመረጣል” (1)

  • በልጅነት የሚሰጥ ሥልጠና ዘላቂ ጥቅም አለው (6)

  • ሰነፍ “ውጭ አንበሳ አለ!” ይላል (13)

  • ተግሣጽ ሞኝነትን ያስወግዳል (15)

  • በሥራው የተካነ በነገሥታት ፊት ይቆማል (29)

22  መልካም ስም* ከብዙ ሀብት ይመረጣል፤+መከበር* ከብርና ከወርቅ ይሻላል።   ሀብታምንና ድሃን የሚያመሳስላቸው ነገር አለ፦* ሁለቱንም የፈጠረው ይሖዋ ነው።+   ብልህ ሰው አደጋ ሲያይ ይሸሸጋል፤ተሞክሮ የሌለው ግን ዝም ብሎ ይሄዳል፤ መዘዙንም* ይቀበላል።   ትሕትናና ይሖዋን መፍራትሀብት፣ ክብርና ሕይወት ያስገኛል።+   በጠማማ ሰው መንገድ ላይ እሾህና ወጥመድ አለ፤ለሕይወቱ* ትልቅ ግምት የሚሰጥ ሁሉ ግን ከእነዚህ ይርቃል።+   ልጅን* ሊሄድበት በሚገባው መንገድ አሠልጥነው፤+በሚያረጅበት ጊዜም እንኳ ከዚያ ፈቀቅ አይልም።+   ሀብታም ድሃን ይገዛል፤ተበዳሪም የአበዳሪው ባሪያ ነው።+   ክፋትን የሚዘራ ሁሉ ጥፋትን ያጭዳል፤+የቁጣውም በትር ያከትማል።+   ለጋስ ሰው* ይባረካል፤ምግቡን ለድሃ ያካፍላልና።+ 10  ንቀት የሚያሳይን ሰው አባረው፤ጭቅጭቅም ይቀራል፤ጥልና* ስድብ ያከትማል። 11  ንጹሕ ልብ የሚወድና ንግግሩ ለዛ ያለው ሰው፣የንጉሥ ወዳጅ ይሆናል።+ 12  የይሖዋ ዓይኖች እውቀትን ይጠብቃሉ፤የከዳተኛን ቃል ግን ይሽራል።+ 13  ሰነፍ “ውጭ አንበሳ አለ! አደባባይ ላይ እገደላለሁ!” ይላል።+ 14  የጋጠወጥ* ሴት አፍ ጥልቅ ጉድጓድ ነው።+ ይሖዋ ያወገዘው ሰው እዚያ ውስጥ ይወድቃል። 15  ሞኝነት በልጅ* ልብ ውስጥ ታስሯል፤+የተግሣጽ በትር ግን ከእሱ ያርቀዋል።+ 16  ሀብቱን ለመጨመር ድሃውን የሚያጭበረብር+እንዲሁም ለባለጸጋ ስጦታ የሚሰጥ ሰውየኋላ ኋላ ይደኸያል። 17  እውቀቴን በሙሉ ልብ እንድትቀበል+ጆሮህን አዘንብል፤ የጥበበኞችንም ቃል አዳምጥ፤+ 18  ምንጊዜም ይህ ቃል ሙሉ በሙሉ በከንፈሮችህ ላይ እንዲሆን+ቃሉን በውስጥህ መያዝህ መልካም ነውና።+ 19  በይሖዋ እንድትተማመን፣ዛሬ እውቀት እሰጥሃለሁ። 20  ከዚህ ቀደም ምክርናእውቀት የያዙ ሐሳቦች አልጻፍኩልህም? 21  ይህን ያደረግኩት ለላከህ ትክክለኛ ወሬ ይዘህ እንድትመለስ፣እውነት የሆነውንና እምነት የሚጣልበትን ቃል ላስተምርህ አይደለም? 22  ድሃውን ድሃ ስለሆነ ብቻ አትዝረፈው፤+ችግረኛውንም በከተማው በር ላይ ግፍ አትፈጽምበት፤+ 23  ይሖዋ ራሱ ይሟገትላቸዋልና፤+የሚያጭበረብሯቸውንም ሰዎች ሕይወት ያጠፋል።* 24  ከግልፍተኛ ሰው ጋር አትግጠም፤በቀላሉ ቱግ ከሚል ሰውም ጋር አትቀራረብ፤ 25  አለዚያ መንገዱን ትማራለህ፤ለራስህም* ወጥመድ ይሆናል።+ 26  ዋስ ለመሆን እጅ እንደሚመቱ፣*ለብድር ተያዥ እንደሚሆኑ ሰዎች አትሁን።+ 27  የምትከፍለው ካጣህየተኛህበት አልጋ ከሥርህ ይወሰድብሃል! 28  አባቶችህ ያደረጉትንየጥንቱን የወሰን ምልክት ከቦታው አታንቀሳቅስ።+ 29  በሥራው የተካነን ሰው አይተሃል? በነገሥታት ፊት ይቆማል፤+ተራ በሆኑ ሰዎች ፊት አይቆምም።

የግርጌ ማስታወሻ

ቃል በቃል “ሞገስ።”
ወይም “ዝና።” ቃል በቃል “ስም።”
ቃል በቃል “ተገናኙ።”
ወይም “ቅጣቱንም።”
ወይም “ለነፍሱ።”
ወይም “ሕፃንን፤ ወጣትን።”
ቃል በቃል “ጥሩ ዓይን ያለው ሰው።”
ወይም “ክስና።”
ቃል በቃል “የእንግዳ።” ምሳሌ 2:16ን ተመልከት።
ወይም “በሕፃን፤ በወጣት።”
ወይም “ነፍስ ይቀማል።”
ወይም “ለነፍስህም።”
ወይም “እንደሚጨብጡ።”