ምሳሌ 30:1-33
30 የያቄ ልጅ አጉር ለኢቲኤል፣ ለኢቲኤልና ለዑካል የተናገራቸው ከፍተኛ ቁም ነገር ያዘሉ ቃላት።
2 እኔ ከማንም የባሰ አላዋቂ ነኝ፤+ሰው ሊኖረው የሚገባው ማስተዋልም የለኝም።
3 ጥበብን አልተማርኩም፤እጅግ ቅዱስ የሆነው አምላክ እውቀትም የለኝም።
4 ወደ ሰማይ የወጣ፣ ከዚያም የወረደ ማን ነው?+
ነፋስን በእፍኙ ሰብስቦ የያዘ ማን ነው?
ውኃን በልብሱ የጠቀለለ ማን ነው?+
የምድርን ዳርቻዎች ሁሉ የወሰነ* ማን ነው?+
ስሙ ማን ነው? የልጁስ ስም ማን ነው? ታውቅ እንደሆነ ንገረኝ።
5 የአምላክ ቃል ሁሉ የነጠረ ነው።+
እሱ፣ መጠጊያቸው ለሚያደርጉት ሁሉ ጋሻ ነው።+
6 በቃሉ ላይ ምንም አትጨምር፤+አለዚያ ይወቅስሃል፤ሐሰተኛም ሆነህ ትገኛለህ።
7 ሁለት ነገር እንድታደርግልኝ እለምንሃለሁ።
እነሱንም ከመሞቴ በፊት አትንፈገኝ።
8 ውሸትንና ሐሰትን ከእኔ አርቅ።+
ድሃም ሆነ ባለጸጋ አታድርገኝ።
ብቻ የሚያስፈልገኝን ቀለብ አታሳጣኝ፤+
9 አለዚያ እጠግብና እክድሃለሁ፤ ከዚያም “ይሖዋ ማን ነው?” እላለሁ፤+
ደግሞም ድሃ ሆኜ እንድሰርቅና የአምላኬን ስም እንዳሰድብ* አትፍቀድ።
10 እንዳይረግምህና በደለኛ ሆነህ እንዳትገኝበጌታው ፊት የአገልጋዩን ስም አታጥፋ።+
11 አባቱን የሚረግም፣እናቱንም የማይባርክ ትውልድ አለ።+
12 በገዛ ዓይኑ ፊት ንጹሕ የሆነ፣+ሆኖም ከቆሻሻው* ያልነጻ ትውልድ አለ።
13 እጅግ ትዕቢተኛ ዓይን ያለው ትውልድ አለ፤ዓይኖቹም በታላቅ እብሪት ይመለከታሉ!+
14 ጥርሱ ሰይፍ፣መንገጭላው ደግሞ ቢላ የሆነ ትውልድ አለ፤በምድር ላይ ያሉ ምስኪኖችን፣በሰው ዘር መካከል ያሉ ድሆችንም ይውጣል።+
15 አልቅቶች “ስጡን! ስጡን!” እያሉ የሚጮኹ ሁለት ሴቶች ልጆች አሏቸው።
ፈጽሞ የማይጠግቡ ሦስት ነገሮች አሉ፤ደግሞም “በቃኝ!” የማያውቁ አራት ነገሮች አሉ።
16 እነሱም መቃብር፣*+ መሃን የሆነ ማህፀን፣ውኃ የተጠማ መሬትእንዲሁም “በቃኝ!” የማይል እሳት ናቸው።
17 በአባቷ ላይ የምታፌዝን፣ የእናቷንም ትእዛዝ የምትንቅን+ ዓይንየሸለቆ* ቁራዎች ይጎጠጉጧታል፤የንስር ጫጩቶችም ይበሏታል።+
18 ከመረዳት አቅሜ በላይ የሆኑ* ሦስት ነገሮች አሉ፤የማልገነዘባቸውም አራት ነገሮች አሉ፦
19 ንስር በሰማያት የሚበርበት መንገድ፣እባብ በዓለት ላይ የሚሄድበት መንገድ፣መርከብ በባሕር ላይ የሚጓዝበት መንገድ፣ሰውም ከሴት ልጅ ጋር የሚሄድበት መንገድ ናቸው።
20 የአመንዝራ ሴት መንገድ ይህ ነው፦
በልታ አፏን ከጠራረገች በኋላ“ምንም የሠራሁት ጥፋት የለም” ትላለች።+
21 ምድርን የሚያናውጡ ሦስት ነገሮች አሉ፤መታገሥ የማትችላቸውም አራት ነገሮች አሉ፦
22 ባሪያ ንጉሥ ሆኖ ሲገዛ፣+ሞኝ በልቶ ሲጠግብ፣
23 የተጠላች* ሴት ባል ስታገኝ፣ሴት አገልጋይም የእመቤቷን ቦታ ስትወስድ* የሚከሰቱ ሁኔታዎች ናቸው።+
24 በምድር ላይ በጣም ትናንሽ የሆኑ አራት ፍጥረታት አሉ፤ሆኖም በደመ ነፍስ ጥበበኞች* ናቸው፦+
25 ጉንዳኖች ኃይል የሌላቸው ፍጥረታት* ናቸው፤ይሁንና ምግባቸውን በበጋ ያዘጋጃሉ።+
26 ሽኮኮዎች+ ኃያላን ፍጥረታት* አይደሉም፤ነገር ግን መኖሪያቸውን በቋጥኞች ውስጥ ያደርጋሉ።+
27 አንበጦች+ ንጉሥ የላቸውም፤ሆኖም ሁሉም በሰልፍ ወደ ፊት* ይጓዛሉ።+
28 እንሽላሊት*+ በእግሮቿ ቆንጥጣ ትይዛለች፤ወደ ንጉሥ ቤተ መንግሥትም ትገባለች።
29 ግርማ የተላበሰ አረማመድ ያላቸው ሦስት ፍጥረታት አሉ፤አዎ፣ እየተጎማለሉ የሚሄዱ አራት ፍጥረታት አሉ፦
30 ከአራዊት ሁሉ ኃያል የሆነውናማንንም አይቶ ወደ ኋላ የማይመለሰው አንበሳ፣+
31 አዳኝ ውሻ፣ አውራ ፍየል፣እንዲሁም በሠራዊቱ የታጀበ ንጉሥ ናቸው።
32 በሞኝነት ራስህን ከፍ ከፍ ካደረግክ፣+ወይም እንዲህ ለማድረግ ካሰብክእጅህን በአፍህ ላይ አድርግ።+
33 ወተት ሲናጥ ቅቤ እንደሚወጣው፣አፍንጫም ሲጨመቅ እንደሚደማ ሁሉቁጣን ማነሳሳትም ጠብ ያስከትላል።+