ምሳሌ 31:1-31

  • የንጉሥ ልሙኤል ቃል (1-31)

    • ባለሙያ ሚስትን ማን ሊያገኛት ይችላል? (10)

    • ታታሪና ትጉ ሠራተኛ ናት (17)

    • ‘የደግነት ሕግ በአንደበቷ አለ’ (26)

    • ልጆቿና ባሏ ያወድሷታል (28)

    • ውበትና ቁንጅና አላፊ ነው (30)

31  የንጉሥ ልሙኤል ቃል፤ እናቱ እሱን ለማስተማር የተናገረችው ከፍተኛ ቁም ነገር ያዘለ መልእክት፦+   ልጄ ሆይ፣ ምን ልበልህ?የማህፀኔ ልጅ ሆይ፣ ምን ልበልህ?የስእለቴ ልጅ ሆይ፣ ምን ልበልህ?+   ጉልበትህን ለሴቶች አትስጥ፤+ነገሥታትንም ለጥፋት የሚዳርግ መንገድ አትከተል።+   ልሙኤል ሆይ፣ ነገሥታት የወይን ጠጅ መጠጣት የለባቸውም፤አዎ፣ ነገሥታት ይህን ማድረግ አይገባቸውም፤ገዢዎችም “መጠጤ የት አለ?” ሊሉ አይገባም።+   አለዚያ ጠጥተው የተደነገገውን ሕግ ይረሳሉ፤የችግረኞችንም መብት ይጥሳሉ።   ሊጠፉ ለተቃረቡ ሰዎች መጠጥ፣+ከባድ ጭንቀት ለደረሰባቸውም* የወይን ጠጅ ስጧቸው።+   ጠጥተው ድህነታቸውን ይርሱ፤ችግራቸውንም ዳግመኛ አያስታውሱ።   ስለ ራሳቸው መናገር ለማይችሉት አንተ ተናገርላቸው፤ሊጠፉ ለተቃረቡት ሰዎች ሁሉ መብት ተሟገት።+   ተናገር፤ በጽድቅም ፍረድ፤ለችግረኛውና ለድሃው መብት ጥብቅና ቁም።*+ א [አሌፍ] 10  ባለሙያ ሚስትን* ማን ሊያገኛት ይችላል?+ ዋጋዋ ከዛጎል* እጅግ ይበልጣል። ב [ቤት] 11  ባሏ ከልቡ ይታመንባታል፤አንዳችም ጠቃሚ ነገር አይጎድልበትም። ג [ጊሜል] 12  በሕይወቷ ዘመን ሁሉመልካም ነገር ታደርግለታለች እንጂ ክፉ ነገር አታደርግበትም። ד [ዳሌት] 13  ሱፍና በፍታ ታመጣለች፤በእጆቿ መሥራት ያስደስታታል።+ ה [] 14  እሷ እንደ ነጋዴ መርከብ ናት፤+ምግቧን ከሩቅ ቦታ ታመጣለች። ו [ዋው] 15  ገና ሳይነጋም ትነሳለች፤ለቤተሰቦቿም ምግባቸውን፣ለሴት አገልጋዮቿም ድርሻቸውን ትሰጣለች።+ ז [ዛየን] 16  በጥሞና ካሰበችበት በኋላ መሬት ትገዛለች፤በራሷ ጥረት* ወይን ትተክላለች። ח [ኼት] 17  ወገቧን ታጥቃ ለሥራ ትነሳለች፤*+ክንዶቿንም ታበረታለች። ט [ቴት] 18  ንግዷ ትርፋማ እንደሆነ ታስተውላለች፤መብራቷ በሌሊት አይጠፋም። י [ዮድ] 19  እጆቿ አመልማሎ የያዘ ዘንግ ይጨብጣሉ፤ጣቶቿም እንዝርት ይይዛሉ።*+ כ [ካፍ] 20  እጆቿን ለተቸገረ ሰው ትዘረጋለች፤ለድሃውም እጇን ትከፍታለች።+ ל [ላሜድ] 21  ቤተሰቦቿ ሁሉ የሚያሞቅ* ልብስ ስለሚለብሱበበረዶ ወቅት እንኳ አትሰጋም። מ [ሜም] 22  ለራሷ የአልጋ ልብስ ትሠራለች። ልብሷ ከበፍታና ከሐምራዊ ሱፍ የተሠራ ነው። נ [ኑን] 23  ባሏ ከአገሩ ሽማግሌዎች ጋር በሚቀመጥበት በከተማዋ በሮች+በሰዎች ዘንድ በሰፊው የታወቀ ነው። ס [ሳሜኽ] 24  የበፍታ ልብሶች እየሠራች* ትሸጣለች፤ለነጋዴዎችም ቀበቶ ታስረክባለች። ע [አይን] 25  ብርታትንና ግርማን ትጎናጸፋለች፤የወደፊቱንም ጊዜ በልበ ሙሉነት ትጠባበቃለች።* פ [] 26  አፏን በጥበብ ትከፍታለች፤+የደግነት ሕግም* በአንደበቷ አለ። צ [ጻዴ] 27  የቤተሰቧን እንቅስቃሴ በደንብ ትከታተላለች፤የስንፍናንም ምግብ አትበላም።+ ק [ኮፍ] 28  ልጆቿ ተነስተው ደስተኛ ይሏታል፤ባሏ ተነስቶ ያወድሳታል። ר [ረሽ] 29  ባለሙያ* የሆኑ ብዙ ሴቶች አሉ፤አንቺ ግን፣ አዎ አንቺ ከሁሉም ትበልጫለሽ። ש [ሺን] 30  ውበት ሐሰት፣ ቁንጅናም አላፊ* ነው፤+ይሖዋን የምትፈራ ሴት ግን ትመሰገናለች።+ ת [ታው] 31  ላከናወነችው ነገር ሽልማት ስጧት፤*+ሥራዎቿም በከተማዋ በሮች ያስመስግኗት።+

የግርጌ ማስታወሻ

ወይም “በነፍሳቸው ለተመረሩትም።”
ወይም “ጉዳይ ተሟገት።”
ወይም “እጅግ ጥሩ የሆነችን ሚስት።”
ወይም “በምታገኘው ገቢ።” ቃል በቃል “ከእጆቿ ፍሬ።”
ቃል በቃል “ዳሌዋን በኃይል ትታጠቃለች።”
የአመልማሎ ዘንግና እንዝርት፣ ድርና ማግ ለማጠንጠን ወይም ለመሥራት የሚያገለግሉ ቀጫጭን እንጨቶች ናቸው።
ቃል በቃል “ድርብ።”
ወይም “የውስጥ ልብሶች እየሠራች።”
ወይም “በመጪው ጊዜ ላይ ትስቃለች።”
ወይም “ፍቅራዊ መመሪያም፤ የታማኝ ፍቅር ሕግም።”
ወይም “እጅግ ጥሩ።”
ወይም “ከንቱ።”
ቃል በቃል “ከእጆቿ ፍሬ ስጧት።”