ለዮሐንስ የተገለጠለት ራእይ 14:1-20

  • በጉና 144,000ዎቹ (1-5)

  • ሦስት መላእክት ያስተላለፉት መልእክት (6-12)

    • ምሥራች የያዘ መልአክ በሰማይ መካከል ሲበር ታየ (6, 7)

  • “ከጌታ ጋር ያላቸውን አንድነት ጠብቀው የሚሞቱ ደስተኞች ናቸው” (13)

  • የምድር መከር (14-20)

14  ከዚያም አየሁ፤ እነሆ፣ በጉ+ በጽዮን ተራራ+ ላይ ቆሟል፤ ከእሱም ጋር የእሱ ስምና የአባቱ ስም+ በግንባራቸው ላይ የተጻፈባቸው 144,000+ ነበሩ።  ከሰማይ እንደ ብዙ ውኃዎችና እንደ ኃይለኛ የነጎድጓድ ድምፅ ያለ ድምፅ ሲወጣ ሰማሁ፤ የሰማሁትም ድምፅ በገናቸውን እየደረደሩ የሚዘምሩ ዘማሪዎች ዓይነት ድምፅ ነው።  እነሱም በዙፋኑ ፊት እንዲሁም በአራቱ ሕያዋን ፍጥረታትና+ በሽማግሌዎቹ+ ፊት አዲስ የሚመስል መዝሙር እየዘመሩ ነበር፤+ ከምድር ከተዋጁት ከ144,000ዎቹ+ በስተቀር ማንም ይህን መዝሙር ጠንቅቆ ሊያውቀው አልቻለም።  እነዚህ ራሳቸውን በሴቶች ያላረከሱ ናቸው፤ እንዲያውም ደናግል ናቸው።+ ምንጊዜም በጉ በሄደበት ሁሉ ይከተሉታል።+ እነዚህ ለአምላክና ለበጉ እንደ በኩራት+ ሆነው ከሰዎች መካከል ተዋጅተዋል፤+  በአፋቸውም የማታለያ ቃል አልተገኘም፤ ምንም ዓይነት እንከን የለባቸውም።+  ሌላም መልአክ በሰማይ መካከል* ሲበር አየሁ፤ እሱም በምድር ላይ ለሚኖር ብሔር፣ ነገድ፣ ቋንቋና ሕዝብ ሁሉ የሚያበስረው የዘላለም ምሥራች ይዞ ነበር።+  እሱም በታላቅ ድምፅ “አምላክን ፍሩ፤ ክብርም ስጡት፤ ምክንያቱም የሚፈርድበት ሰዓት ደርሷል፤+ በመሆኑም ሰማይን፣ ምድርን፣ ባሕርንና የውኃ ምንጮችን የሠራውን+ አምልኩ” አለ።  ሌላ ሁለተኛ መልአክ “ወደቀች! ብሔራት ሁሉ የዝሙቷን* የፍትወት* ወይን ጠጅ እንዲጠጡ ያደረገችው+ ታላቂቱ ባቢሎን+ ወደቀች!”+ እያለ ተከተለው።  ሌላ ሦስተኛ መልአክ በታላቅ ድምፅ እንዲህ እያለ ተከተላቸው፦ “ማንም አውሬውንና+ ምስሉን የሚያመልክና በግንባሩ ወይም በእጁ ላይ ምልክት የሚቀበል ከሆነ+ 10  እሱም፣ ሳይበረዝ ወደ ቁጣው ጽዋ የተቀዳውን የአምላክ የቁጣ ወይን ጠጅ ይጠጣል፤+ እንዲሁም በቅዱሳኑ መላእክት ፊትና በበጉ ፊት በእሳትና በድኝ ይሠቃያል።+ 11  የሥቃያቸውም ጭስ ለዘላለም ወደ ላይ ይወጣል፤+ ደግሞም አውሬውንና ምስሉን የሚያመልኩ እንዲሁም የስሙን ምልክት የሚቀበሉ ሁሉ ቀንና ሌሊት ምንም እረፍት አይኖራቸውም።+ 12  የአምላክን ትእዛዛት የሚጠብቁና የኢየሱስን እምነት አጥብቀው የሚከተሉ+ ቅዱሳን፣+ መጽናት የሚያስፈልጋቸው እዚህ ላይ ነው።” 13  ከሰማይም እንዲህ የሚል ድምፅ ሰማሁ፦ “ይህን ጻፍ፦ ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ከጌታ ጋር ያላቸውን አንድነት ጠብቀው የሚሞቱ+ ደስተኞች ናቸው። መንፈስም ‘አዎ፣ ያከናወኑት ሥራ ወዲያው ስለሚከተላቸው* ከድካማቸው ይረፉ’ ይላል።” 14  ከዚያም አየሁ፤ እነሆም፣ ነጭ ደመና ነበር፤ በደመናውም ላይ የሰውን ልጅ የሚመስል ተቀምጧል፤+ እሱም በራሱ ላይ የወርቅ አክሊል ደፍቷል፤ በእጁም ስለታም ማጭድ ይዟል። 15  ሌላ መልአክ ከቤተ መቅደሱ ቅዱስ ስፍራ* ወጥቶ በደመናው ላይ ለተቀመጠው “የአጨዳው ሰዓት ስለደረሰ ማጭድህን ስደድና እጨድ፤ ምክንያቱም የምድር መከር ደርሷል” ሲል በታላቅ ድምፅ ጮኸ።+ 16  በደመናውም ላይ የተቀመጠው ማጭዱን ወደ ምድር ሰደደ፤ ምድርም ታጨደች። 17  አሁንም ሌላ መልአክ በሰማይ ካለው ቤተ መቅደስ ቅዱስ ስፍራ ወጣ፤ እሱም ስለታም ማጭድ ይዞ ነበር። 18  እንደገናም ሌላ መልአክ ከመሠዊያው ወጣ፤ እሱም በእሳቱ ላይ ሥልጣን ነበረው። በታላቅ ድምፅ ጮኾም ስለታም ማጭድ የያዘውን መልአክ “የምድሪቱ የወይን ፍሬዎች ስለበሰሉ ስለታም ማጭድህን ስደድና የምድርን የወይን ዘለላዎች ሰብስብ” አለው።+ 19  መልአኩ ማጭዱን ወደ ምድር በመስደድ የምድርን ወይን ሰበሰበ፤ ከዚያም ወደ ታላቁ የአምላክ የቁጣ ወይን መጭመቂያ ወረወረው።+ 20  ወይኑ ከከተማው ውጭ ተረገጠ፤ ከመጭመቂያውም እስከ ፈረሶች ልጓም የሚደርስ ከፍታ ያለውና 296 ኪሎ ሜትር ገደማ* ርቀት ያለው ደም ወጣ።

የግርጌ ማስታወሻ

ወይም “በአየር ላይ፤ ከላይ።”
ወይም “የቁጣ።”
ግሪክኛ፣ ፖርኒያ። የቃላት መፍቻውን ተመልከት።
ወይም “አብሯቸው ስለሚሄድ።”
የቤተ መቅደሱን ቅድስተ ቅዱሳን ያመለክታል።
ቃል በቃል “1,600 ስታዲዮን።” አንድ ስታዲዮን 185 ሜትር ነው። ከተጨማሪው መረጃ ላይ ለ14ን ተመልከት።