ሰቆቃወ ኤርምያስ 2:1-22

  • የይሖዋ ቁጣ በኢየሩሳሌም ላይ ነደደ

    • ርኅራኄ አላሳያትም (2)

    • ይሖዋ ጠላት ሆነባት (5)

    • በጽዮን የተነሳ የፈሰሰው እንባ (11-13)

    • በመንገድ የሚያልፉ ውብ በነበረችው ከተማ ላይ ያፌዛሉ (15)

    • ጠላቶች በጽዮን ላይ በደረሰው ጥፋት ይደሰታሉ (17)

א [አሌፍ] 2  ይሖዋ የጽዮንን ሴት ልጅ በቁጣው ደመና እንዴት ሸፈናት! የእስራኤልን ውበት ከሰማይ ወደ ምድር ጥሏል።+ በቁጣው ቀን የእግሩን ማሳረፊያ አላስታወሰም።+ ב [ቤት]   ይሖዋ የያዕቆብን መኖሪያዎች በሙሉ ያላንዳች ርኅራኄ ውጧል። የይሁዳን ሴት ልጅ የተመሸጉ ቦታዎች በቁጣው አፈራርሷል።+ መንግሥቱንና መኳንንቷን ወደ መሬት ጥሏል፤ ደግሞም አርክሷል።+ ג [ጊሜል]   የእስራኤልን ብርታት* ሁሉ በታላቅ ቁጣ ቆረጠ። ጠላት በቀረበ ጊዜ እሱ ቀኝ እጁን መለሰ፤+በዙሪያው ያለውን ሁሉ እንደሚበላ እሳትም ቁጣው በያዕቆብ ላይ ነደደ።+ ד [ዳሌት]   እንደ ጠላት ደጋኑን ወጠረ፤* ቀኝ እጁም እንደ ባላጋራ ተዘጋጀች፤+ለዓይን የሚማርኩትን ሁሉ ገደለ።+ በጽዮን ሴት ልጅ ድንኳንም ላይ+ ቁጣውን እንደ እሳት አፈሰሰ።+ ה []   ይሖዋ እንደ ጠላት ሆነ፤+እስራኤልን ዋጠ። ማማዎቿን ሁሉ ዋጠ፤የተመሸጉ ስፍራዎቿን ሁሉ አወደመ። በይሁዳ ሴት ልጅ ዘንድ ለቅሶንና ዋይታን አበዛ። ו [ዋው]   የራሱን ዳስ በአትክልት ቦታ እንዳለች ጎጆ አፈረሰ።+ በዓሉ እንዲያከትም* አደረገ።+ ይሖዋ በጽዮን፣ በዓልና ሰንበት እንዲረሳ አድርጓል፤በኃይለኛ ቁጣውም ንጉሡንና ካህኑን አቃሏል።+ ז [ዛየን]   ይሖዋ መሠዊያውን ናቀ፤መቅደሱን ተወ።+ የማይደፈሩ ማማዎቿን ግንቦች ለጠላት አሳልፎ ሰጠ።+ በበዓል ቀን እንደሚደረገው ሁሉ በይሖዋ ቤት በታላቅ ድምፅ ጮኹ።+ ח [ኼት]   ይሖዋ የጽዮንን ሴት ልጅ ቅጥር ለማፍረስ ቆርጧል።+ የመለኪያ ገመዱን ዘርግቷል።+ ከማጥፋትም እጁን አልመለሰም። የመከላከያ ግንቡና ቅጥሩ እንዲያዝኑ አደረገ። በአንድነትም ደከሙ። ט [ቴት]   በሮቿ ወደ መሬት ሰጠሙ።+ መቀርቀሪያዎቿን አስወገደ፤ ደግሞም ሰባበረ። ንጉሥዋና መኳንንቷ በብሔራት መካከል ናቸው።+ ሕግ* የለም፤ ነቢያቷም እንኳ ከይሖዋ የተገለጠላቸው ራእይ የለም።+ י [ዮድ] 10  የጽዮን ሴት ልጅ ሽማግሌዎች ዝም ብለው መሬት ላይ ይቀመጣሉ።+ በራሳቸው ላይ አቧራ ይነሰንሳሉ፤ ማቅም ይለብሳሉ።+ የኢየሩሳሌም ደናግል ራሳቸውን ወደ መሬት ደፍተዋል። כ [ካፍ] 11  ከማልቀሴ ብዛት ዓይኖቼ ፈዘዙ።+ አንጀቴ ተላወሰ። በሕዝቤ ሴት ልጅ* ላይ ከደረሰው ውድቀት+እንዲሁም በከተማዋ አደባባዮች ተዝለፍልፈው ከወደቁት ልጆችና ሕፃናት+ የተነሳ ጉበቴ መሬት ላይ ፈሰሰ። ל [ላሜድ] 12  ልክ እንደቆሰለ ሰው በከተማዋ አደባባዮች ተዝለፍልፈው ሲወድቁና በእናቶቻቸው ጉያ ሆነው ለመሞት ሲያጣጥሩ፣*እናቶቻቸውን “እህልና የወይን ጠጅ የት አለ?” ብለው ይጠይቃሉ።+ מ [ሜም] 13  የኢየሩሳሌም ሴት ልጅ ሆይ፣ ምሥክር የሚሆን ምን ነገር ላቀርብልሽ እችላለሁ?ከምንስ ጋር ላመሳስልሽ እችላለሁ? ድንግሊቱ የጽዮን ሴት ልጅ ሆይ፣ አጽናናሽ ዘንድ ከማን ጋር ላወዳድርሽ እችላለሁ? የደረሰብሽ ጥፋት እንደ ባሕር ሰፊ ነውና።+ ማን ሊፈውስሽ ይችላል?+ נ [ኑን] 14  ነቢያትሽ ያዩልሽ ራእይ ሐሰትና ከንቱ ነው፤+ተማርከሽ እንዳትወሰጂ ለማድረግ በደልሽን አላጋለጡም፤+ይልቁንም ራእይ ተገለጠልን እያሉ ሐሰትና አሳሳች ቃል ይነግሩሻል።+ ס [ሳሜኽ] 15  በመንገድ የሚያልፉ ሁሉ በማሾፍ እጃቸውን ያጨበጭቡብሻል።+ “‘ፍጹም ውበት የተላበሰችና የምድር ሁሉ ደስታ’+ በማለት ይጠሯት የነበረችው ከተማ ይህች ናት?” እያሉ በመገረም በኢየሩሳሌም ሴት ልጅ ላይ ያፏጫሉ፤+ ራሳቸውንም ይነቀንቃሉ። פ [] 16  ጠላቶችሽ ሁሉ በአንቺ ላይ አፋቸውን ከፍተዋል። እነሱ ያፏጫሉ፤ ጥርሳቸውንም ያፋጫሉ፤ ደግሞም “ዋጥናት።+ ስንጠብቀው የነበረው ቀን ይህ ነው!+ ጊዜው ደርሶ ለማየት በቃን!”+ ይላሉ። ע [አይን] 17  ይሖዋ ያሰበውን አድርጓል፤+የተናገረውን፣ ከጥንትም ጀምሮ ያዘዘውን+ ፈጽሟል።+ ያላንዳች ርኅራኄ አፍርሷል።+ ጠላት በአንቺ ላይ በደረሰው ነገር ደስ እንዲሰኝ፣ የባላጋራዎችሽም ብርታት* ከፍ ከፍ እንዲል አድርጓል። צ [ጻዴ] 18  የጽዮን ሴት ልጅ ቅጥር ሆይ፣ ልባቸው ወደ ይሖዋ ይጮኻል። እንባሽ እንደ ጅረት ቀን ከሌት ይፍሰስ። ለራስሽ ፋታ አትስጪ፤ ዓይንሽ እንባ ማፍሰሱን አያቋርጥ።* ק [ኮፍ] 19  ተነሺ! ሌሊት፣ ክፍለ ሌሊቶቹ ሲጀምሩ ጩኺ። በይሖዋ ፊት ልብሽን እንደ ውኃ አፍስሺ። በረሃብ ምክንያት በየመንገዱ ማዕዘን* ተዝለፍልፈው ለወደቁት+ ልጆችሽ ሕይወት* ስትዪ፣እጆችሽን ወደ እሱ ዘርጊ። ר [ረሽ] 20  ይሖዋ ሆይ፣ ክፉኛ የቀጣኸውን እይ፤ ደግሞም ተመልከት። ሴቶች የሆዳቸውን ፍሬ፣ የገዛ ራሳቸውን ልጆች* ይብሉ?+ደግሞስ ካህናቱና ነቢያቱ በይሖዋ መቅደስ ውስጥ ይገደሉ?+ ש [ሺን] 21  ወንድ ልጅና ሽማግሌ ሞተው በየመንገዱ ተዘርረዋል።+ ደናግሌና* ወጣት ወንዶቼ በሰይፍ ወድቀዋል።+ በቁጣህ ቀን ገደልክ፤ ያላንዳች ርኅራኄ አረድክ።+ ת [ታው] 22  በበዓል ቀን እንደሚደረገው ሁሉ+ ሽብርን ከየአቅጣጫው ጠራህ። በይሖዋ የቁጣ ቀን ያመለጠም ሆነ በሕይወት የተረፈ የለም፤+የወለድኳቸውንና* ያሳደግኳቸውን ልጆች ጠላቴ ፈጃቸው።+

የግርጌ ማስታወሻ

ቃል በቃል “ቀንድ።”
ቃል በቃል “ረገጠ።”
ወይም “እንዲጠፋ።”
ወይም “መመሪያ፤ ትምህርት።”
በሰውኛ ዘይቤ የተገለጸ ቅኔያዊ አነጋገር፤ አዘኔታን ወይም ርኅራኄን የሚያመለክት ሊሆን ይችላል።
ወይም “ነፍሳቸው ስታጣጥር።”
ቃል በቃል “ቀንድ።”
ቃል በቃል “የዓይንሽ ሴት ልጅ እንባ ማፍሰሷን አታቋርጥ።”
ቃል በቃል “በጎዳና ሁሉ ራስ ላይ።”
ወይም “ነፍስ።”
ወይም “የገዛ ራሳቸውን ጤናማ ልጆች።”
ወይም “ወጣት ሴቶቼና።”
ወይም “ጤናማ ሆነው የወለድኳቸውንና።”