ሰቆቃወ ኤርምያስ 4:1-22

  • የኢየሩሳሌም መከበብ ያስከተለው መጥፎ ውጤት

    • የምግብ እጦት (4, 5, 9)

    • ሴቶች ልጆቻቸውን ቀቀሉ (10)

    • “ይሖዋ ቁጣውን ገልጿል” (11)

א [አሌፍ] 4  ያንጸባርቅ የነበረው ጥሩው ወርቅ፣+ ምንኛ ደበዘዘ! የተቀደሱት ድንጋዮች*+ በየመንገዱ ማዕዘኖች* ላይ እንዴት ተበተኑ!+ ב [ቤት]   በጠራ ወርቅ የተመዘኑት* የጽዮን ውድ ልጆች፣የሸክላ ሠሪ እጅ እንደሠራውየሸክላ ዕቃ እንዴት ተቆጠሩ! ג [ጊሜል]   ቀበሮዎች እንኳ ግልገሎቻቸውን ለማጥባት ጡታቸውን ይሰጣሉ፤የሕዝቤ ሴት ልጅ ግን በምድረ በዳ እንዳሉ ሰጎኖች ጨካኝ ሆነች።+ ד [ዳሌት]   ከውኃ ጥም የተነሳ፣ የሚጠባው ሕፃን ምላስ ከላንቃው ጋር ይጣበቃል። ልጆች ምግብ ይለምናሉ፤+ አንዳች ነገር የሚሰጣቸው ግን የለም።+ ה []   ምርጥ ምግብ ይበሉ የነበሩ ሰዎች በየጎዳናው ላይ ጠኔ ይዟቸው ይተኛሉ።*+ ውድ ልብስ* ለብሰው ያደጉም+ የአመድ ቁልል ያቅፋሉ። ו [ዋው]   የሕዝቤ ሴት ልጅ የደረሰባት ቅጣት፣*የማንም እጅ ሳይረዳት በድንገት የተገለበጠችው ሰዶም፣ በሠራችው ኃጢአት የተነሳ ከደረሰባት ቅጣት ይበልጥ ታላቅ ነው።+ ז [ዛየን]   ናዝራውያኗ+ ከበረዶ ይልቅ የጠሩ፣ ከወተትም ይልቅ የነጡ ነበሩ። ከዛጎል ይበልጥ የቀሉ ነበሩ፤ እንደተወለወለም ሰንፔር ነበሩ። ח [ኼት]   መልካቸው ከጥላሸት ይልቅ ጠቁሯል፤በጎዳና ላይ ማንነታቸውን መለየት የቻለ የለም። ቆዳቸው ተሸብሽቦ አጥንታቸው ላይ ተጣብቋል፤+ እንደደረቀ እንጨት ሆኗል። ט [ቴት]   በሰይፍ የሚወድቁት በረሃብ ከሚያልቁት ይሻላሉ፤+እነዚህ የምድርን ፍሬ በማጣታቸው መንምነው ያልቃሉ። י [ዮድ] 10  ሩኅሩኅ የሆኑ ሴቶች በገዛ እጃቸው ልጆቻቸውን ቀቅለዋል።+ የሕዝቤ ሴት ልጅ ጥፋት በደረሰባት ጊዜ እንደ እዝን እንጀራ ሆነውላቸዋል።+ כ [ካፍ] 11  ይሖዋ ቁጣውን ገልጿል፤የሚነድ ቁጣውንም አፍስሷል።+ በጽዮን መሠረቶቿን የሚበላ እሳት አንድዷል።+ ל [ላሜድ] 12  የምድር ነገሥታትና የምድር ነዋሪዎች ሁሉባላጋራም ሆነ ጠላት በኢየሩሳሌም በሮች ይገባል የሚል እምነት አልነበራቸውም።+ מ [ሜም] 13  ይህ የደረሰው ነቢያቷ በሠሩት ኃጢአትና ካህናቷ በፈጸሙት በደል የተነሳ ነው፤+እነሱ በመካከሏ የነበሩትን ጻድቃን ደም አፍስሰዋል።+ נ [ኑን] 14  ታውረው በየጎዳናው ተቅበዘበዙ።+ በደም ስለተበከሉ+ማንም ልብሳቸውን ለመንካት አይደፍርም። ס [ሳሜኽ] 15  “እናንተ ርኩሳን! ሂዱ!” ይሏቸዋል። “ሂዱ! ሂዱ! አትንኩን!” ብለው ይጮኹባቸዋል። መኖሪያ አጥተው ይቅበዘበዛሉና። በብሔራት መካከል ያሉ ሰዎች እንዲህ ብለዋል፦ “ከእንግዲህ ከእኛ ጋር እዚህ መኖር አይችሉም።*+ פ [] 16  ይሖዋ ራሱ በታትኗቸዋል፤+ዳግመኛም በሞገስ ዓይን አይመለከታቸውም። ሰዎች ለካህናቱ አክብሮት አይኖራቸውም፤+ ለሽማግሌዎቹም ሞገስ አያሳዩም።”+ ע [አይን] 17  አሁንም እንኳ እርዳታ እናገኛለን ብለን በከንቱ ስንጠባበቅ ዓይኖቻችን ደከሙ።+ ሊያድነን ከማይችል ብሔር እርዳታ ለማግኘት ስንጠባበቅ ቆየን።+ צ [ጻዴ] 18  እግር በእግር ተከታተሉን፤+ በመሆኑም በአደባባዮቻችን መንቀሳቀስ አልቻልንም። መጨረሻችን ቀርቧል፤ የሕይወት ዘመናችን አብቅቷል፤ ፍጻሜያችን ደርሷልና። ק [ኮፍ] 19  አሳዳጆቻችን በሰማይ ከሚበርሩ ንስሮች ይልቅ ፈጣኖች ነበሩ።+ በተራሮች ላይ አጥብቀው አሳደዱን፤ በምድረ በዳ አድፍጠው አጠቁን። ר [ረሽ] 20  በይሖዋ የተቀባው፣+ የሕይወታችን እስትንፋስ፣ ጥልቅ ጉድጓዳቸው ውስጥ ገብቶ ተያዘ፤+“በእሱ ጥላ ሥር በብሔራት መካከል እንኖራለን” ብለን ነበር። ש [ሲን] 21  በዑጽ ምድር የምትኖሪ የኤዶም ሴት ልጅ ሆይ፣+ ሐሴት አድርጊ፤ ደስም ይበልሽ። ይሁንና ጽዋው ለአንቺም ይደርስሻል፤+ ትሰክሪያለሽ፤ እርቃንሽንም ትገልጫለሽ።+ ת [ታው] 22  የጽዮን ሴት ልጅ ሆይ፣ በበደልሽ ምክንያት የደረሰብሽ ቅጣት አብቅቷል። ከእንግዲህ ወዲህ ወደ ግዞት አይወስድሽም።+ ይሁንና የኤዶም ሴት ልጅ ሆይ፣ ትኩረቱን በሠራሽው በደል ላይ ያደርጋል። ኃጢአትሽን ይገልጣል።+

የግርጌ ማስታወሻ

ቃል በቃል “በጎዳናዎቹ ሁሉ ራስ።”
ወይም “የመቅደሱ ድንጋዮች።”
ወይም “እንደጠራ ወርቅ ውድ የነበሩት።”
ቃል በቃል “ደማቅ ቀይ።” ይኸውም ደማቅ ቀይ የሆነ ውድ ልብስ።
ቃል በቃል “ይጠፋሉ።”
ቃል በቃል “በደል።”
ወይም “የባዕድ አገር ሰዎች ሆነው መኖር አይችሉም።”