ነህምያ 10:1-39

  • ሕዝቡ ሕጉን ለመጠበቅ ተስማማ (1-39)

    • “የአምላካችንን ቤት ቸል አንልም” (39)

10  በስምምነቱ ላይ ማኅተማቸውን በማተም ያጸደቁት+ እነዚህ ናቸው፦ የሃካልያህ ልጅ የሆነው ገዢው* ነህምያ፣ ሴዴቅያስ፣  ሰራያህ፣ አዛርያስ፣ ኤርምያስ፣  ጳስኮር፣ አማርያህ፣ ማልኪያህ፣  ሃጡሽ፣ ሸባንያህ፣ ማሉክ፣  ሃሪም፣+ መሬሞት፣ አብድዩ፣  ዳንኤል፣+ ጊነቶን፣ ባሮክ፣  መሹላም፣ አቢያህ፣ ሚያሚን፣  ማአዝያህ፣ ቢልጋይ እና ሸማያህ፤ ካህናቱ እነዚህ ናቸው።  ሌዋውያኑ ደግሞ የሚከተሉት ናቸው፦ የአዛንያህ ልጅ የሹዋ፣ ከሄናዳድ ወንዶች ልጆች አንዱ የሆነው ቢኑይ፣ ቃድሚኤል፣+ 10  እንዲሁም ወንድሞቻቸው የሆኑት ሸባንያህ፣ ሆዲያህ፣ ቀሊጣ፣ ፐላያህ፣ ሃናን፣ 11  ሚካ፣ ሬሆብ፣ ሃሻብያህ፣ 12  ዛኩር፣ ሸረበያህ፣+ ሸባንያህ፣ 13  ሆዲያህ፣ ባኒ እና ቤኒኑ። 14  የሕዝቡ መሪዎች የሚከተሉት ናቸው፦ ፓሮሽ፣ ፓሃትሞአብ፣+ ኤላም፣ ዛቱ፣ ባኒ፣ 15  ቡኒ፣ አዝጋድ፣ ቤባይ፣ 16  አዶንያስ፣ ቢግዋይ፣ አዲን፣ 17  አጤር፣ ሕዝቅያስ፣ አዙር፣ 18  ሆዲያህ፣ ሃሹም፣ ቤጻይ፣ 19  ሃሪፍ፣ አናቶት፣ ነባይ፣ 20  ማግፒአሽ፣ መሹላም፣ ሄዚር፣ 21  መሺዛቤል፣ ሳዶቅ፣ ያዱአ፣ 22  ጰላጥያህ፣ ሃናን፣ አናያ፣ 23  ሆሺአ፣ ሃናንያህ፣ ሃሹብ፣ 24  ሃሎሔሽ፣ ፒልሃ፣ ሾቤቅ፣ 25  ረሁም፣ ሃሻብናህ፣ ማአሴያህ፣ 26  አኪያህ፣ ሃናን፣ አናን፣ 27  ማሉክ፣ ሃሪም እና ባአናህ። 28  የቀረው ሕዝብ ማለትም ካህናቱ፣ ሌዋውያኑ፣ በር ጠባቂዎቹ፣ ዘማሪዎቹ፣ የቤተ መቅደስ አገልጋዮቹ* እንዲሁም የእውነተኛውን አምላክ ሕግ ለመጠበቅ በምድሪቱ ካሉት ሕዝቦች ራሳቸውን የለዩ ሁሉ+ ሚስቶቻቸውን፣ ወንዶች ልጆቻቸውንና ሴቶች ልጆቻቸውን ጨምሮ እውቀትና ማስተዋል ያለው* ማንኛውም ሰው 29  ከወንድሞቻቸውና ታዋቂ ከሆኑት ሰዎቻቸው ጋር በመሆን የእውነተኛው አምላክ አገልጋይ በሆነው በሙሴ እጅ በተሰጠው የእውነተኛው አምላክ ሕግ መሠረት ለመሄድ እንዲሁም የጌታችንን የይሖዋን ትእዛዛት፣ ፍርዶችና ሥርዓቶች ሁሉ በጥንቃቄ ለመጠበቅ በእርግማንና በመሐላ ራሳቸውን ግዴታ ውስጥ አስገቡ። 30  ሴቶች ልጆቻችንን በምድሪቱ ለሚኖሩ ሰዎች አንሰጥም፤ ሴቶች ልጆቻቸውንም ለወንዶች ልጆቻችን አንወስድም።+ 31  በምድሪቱ የሚኖሩት ሕዝቦች በሰንበት ቀን ሸቀጣ ሸቀጦቻቸውንና የተለያዩ ጥራጥሬዎችን ለመሸጥ ቢያመጡ በሰንበት+ ወይም ቅዱስ በሆነ ቀን+ ከእነሱ ላይ ምንም ነገር አንገዛም። በተጨማሪም በሰባተኛው ዓመት+ ምርት ከማምረት እንቆጠባለን፤ ያልተከፈለን ዕዳም ሁሉ እንሰርዛለን።+ 32  በተጨማሪም እያንዳንዳችን በአምላካችን ቤት* ለሚከናወነው አገልግሎት በየዓመቱ አንድ ሦስተኛ ሰቅል* ለመስጠት ራሳችንን ግዴታ ውስጥ እናስገባለን፤+ 33  ይህም በሰንበት ቀናትና+ በአዲስ ጨረቃ ወቅት+ ለሚቀርበው የሚነባበር ዳቦ*+ እንዲሁም በእነዚህ ጊዜያት ዘወትር ለሚቀርበው የእህል መባና+ የሚቃጠል መባ፣ በተጨማሪም በተወሰኑ ጊዜያት ለሚከበሩት በዓላት፣+ ቅዱስ ለሆኑት ነገሮች፣ እስራኤልን ለማስተሰረይ ለሚቀርቡት የኃጢአት መባዎችና+ በአምላካችን ቤት ለሚከናወኑ ሥራዎች ሁሉ ይውላል። 34  ከዚህም ሌላ ካህናቱ፣ ሌዋውያኑና ሕዝቡ በሕጉ ላይ በተጻፈው መሠረት በየዓመቱ በተወሰነው ጊዜ በአምላካችን በይሖዋ መሠዊያ ላይ እንዲቃጠል በየአባቶቻችን ቤት በየተራ ወደ አምላካችን ቤት ሊያመጡ የሚገባውን እንጨት በተመለከተ ዕጣ ጣልን።+ 35  እንዲሁም መሬታችን የሚያፈራውን መጀመሪያ የደረሰውን ፍሬና ማንኛውም ዓይነት የፍራፍሬ ዛፍ የሚያፈራውን መጀመሪያ የደረሰውን ፍሬ ሁሉ በየዓመቱ ወደ ይሖዋ ቤት እናመጣለን፤+ 36  በተጨማሪም በሕጉ ላይ በተጻፈው መሠረት ከወንዶች ልጆቻችንና ከእንስሶቻችን በኩሩን+ እንዲሁም ከከብቶቻችንና ከመንጎቻችን በኩሩን እናመጣለን። ወደ አምላካችን ቤት ይኸውም በአምላካችን ቤት ወደሚያገለግሉት ካህናት እናመጣለን።+ 37  ከዚህም በተጨማሪ የተፈጨውን የእህላችንን በኩር፣+ መዋጮዎቻችንን፣ ማንኛውም ዛፍ የሚያፈራውን ፍሬ፣+ አዲስ የወይን ጠጅና ዘይት+ ወደ አምላካችን ቤት ግምጃ ቤቶች*+ ወደ ካህናቱ እናመጣለን፤ እንዲሁም ከእርሻ ከተሞቻችን ሁሉ አንድ አሥረኛውን* የሚቀበሉት ሌዋውያኑ ስለሆኑ የመሬታችንን አንድ አሥረኛ ለሌዋውያኑ እናመጣለን።+ 38  ሌዋውያኑ አንድ አሥረኛውን በሚቀበሉበት ጊዜ ካህኑ የአሮን ልጅ ከሌዋውያኑ ጋር አብሮ መሆን አለበት፤ ሌዋውያኑም የአንድ አሥረኛውን አንድ አሥረኛ ወደ አምላካችን ቤት ይኸውም በግምጃ ቤቱ ውስጥ ወደሚገኙት ክፍሎች* መውሰድ ይኖርባቸዋል።+ 39  ምክንያቱም እስራኤላውያንም ሆኑ የሌዋውያኑ ልጆች የእህሉን፣ የአዲሱን ወይን ጠጅና የዘይቱን+ መዋጮ ማምጣት ያለባቸው ወደ ግምጃ ቤቶቹ* ነው፤+ ደግሞም የመቅደሱ ዕቃዎች የሚቀመጡትም ሆነ የሚያገለግሉት ካህናት፣ በር ጠባቂዎቹና ዘማሪዎቹ የሚገኙት በዚያ ነው። እኛም የአምላካችንን ቤት ቸል አንልም።+

የግርጌ ማስታወሻ

ወይም “ቲርሻታው።” ለአንድ የአውራጃ ገዢ የሚሰጥ የፋርሳውያን የማዕረግ ስም ነው።
ወይም “ናታኒሞቹ።” ቃል በቃል “የተሰጡት ሰዎች።”
“ለማስተዋል የሚያስችል ዕድሜ ላይ የደረሰ” ማለትም ሊሆን ይችላል።
ወይም “ቤተ መቅደስ።”
አንድ ሰቅል 11.4 ግራም ነው። ከተጨማሪው መረጃ ላይ ለ14ን ተመልከት።
ገጸ ኅብስቱን ያመለክታል።
ወይም “አሥራቱን።”
ወይም “መመገቢያ አዳራሾች።”
ወይም “መመገቢያ አዳራሾች።”
ወይም “መመገቢያ አዳራሾቹ።”