ነህምያ 3:1-32

  • ቅጥሩን መልሶ መገንባት (1-32)

3  ሊቀ ካህናቱ ኤልያሺብና+ ካህናት የሆኑት ወንድሞቹ የበግ በርን+ ለመገንባት ተነሱ። እነሱም ቀደሱት፤*+ መዝጊያዎቹንም ገጠሙለት፤ እስከ መአህ ማማና+ እስከ ሃናንኤል ማማ+ ድረስ ቀደሱት።  ከእነሱ ቀጥሎ ያለውን ደግሞ የኢያሪኮ+ ሰዎች እየገነቡ ነበር፤ ከእነሱ ቀጥሎ ያለውን የኢምሪ ልጅ ዛኩር እየገነባ ነበር።  የሃስናአ ልጆች የዓሣ በርን+ ገነቡ፤ የጣውላ መቃኑንም ሠሩ፤+ ከዚያም መዝጊያዎቹን፣ መወርወሪያዎቹንና መቀርቀሪያዎቹን ገጠሙለት።  ከእነሱ ቀጥሎ ያለውን ደግሞ የሃቆጽ ልጅ የሆነው የዑሪያህ ልጅ መሬሞት+ ጠገነ፤ ቀጥሎ ያለውን የመሺዛቤል ልጅ የሆነው የቤራክያህ ልጅ መሹላም+ ጠገነ፤ ከዚያ ቀጥሎ ያለውን የባአና ልጅ ሳዶቅ ጠገነ።  ከእነሱ ቀጥሎ ያለውን ደግሞ የተቆአ+ ሰዎች ጠገኑ፤ ሆኖም ከእነሱ መካከል ታዋቂ የሆኑት ሰዎች ራሳቸውን ዝቅ በማድረግ* አለቆቻቸው በሚያሠሩት ሥራ መካፈል አልፈለጉም።  የፓሰአህ ልጅ ዮያዳ እና የቤሶድያህ ልጅ መሹላም የአሮጌ ከተማ በርን+ ጠገኑ፤ የጣውላ መቃኑንም ሠሩ፤ ከዚያም መዝጊያዎቹን፣ መወርወሪያዎቹንና መቀርቀሪያዎቹን ገጠሙለት።  ከእነሱ ቀጥሎ ያለውን ደግሞ ከወንዙ+ ባሻገር* ባለው ክልል ገዢ ሥልጣን* ሥር የሚገኙት የገባኦንና የምጽጳ+ ሰዎች የሆኑት ገባኦናዊው+ መላጥያህና መሮኖታዊው ያዶን ጠገኑ።  ከእነሱ ቀጥሎ ያለውን ከወርቅ አንጥረኞቹ አንዱ የሆነው የሃርሐያህ ልጅ ዑዚኤል ጠገነ፤ ከእሱ ቀጥሎ ያለውን ከቅባት ቀማሚዎች* አንዱ የሆነው ሃናንያህ ጠገነ፤ ኢየሩሳሌምንም እስከ ሰፊ ቅጥር+ ድረስ ድንጋይ አነጠፉባት።  ከእነሱ ቀጥሎ ያለውን ደግሞ የኢየሩሳሌም አውራጃ እኩሌታ ገዢ የሆነው የሁር ልጅ ረፋያህ ጠገነ። 10  የሃሩማፍ ልጅ የዳያህ ከእነሱ ቀጥሎ የሚገኘውን ከራሱ ቤት ፊት ለፊት ያለውን ጠገነ፤ ከእሱ ቀጥሎ ያለውን ደግሞ የሃሻበንያህ ልጅ ሃጡሽ ጠገነ። 11  የሃሪም+ ልጅ ማልኪያህና የፓሃትሞአብ+ ልጅ ሃሹብ ሌላኛውን ክፍል* ጠገኑ፤ እንዲሁም የምድጃዎች ማማን+ ጠገኑ። 12  ከእነሱ ቀጥሎ ያለውን ደግሞ የኢየሩሳሌም አውራጃ እኩሌታ ገዢ የሆነው የሃሎሔሽ ልጅ ሻሉም እና ሴቶች ልጆቹ ጠገኑ። 13  ሃኑን እና የዛኖሃ+ ነዋሪዎች የሸለቆ በርን+ ጠገኑ፤ እነሱም ከሠሩት በኋላ መዝጊያዎቹን፣ መወርወሪያዎቹንና መቀርቀሪያዎቹን ገጠሙለት፤ በተጨማሪም እስከ አመድ ቁልል በር+ ድረስ ያለውን 1,000 ክንድ* ቅጥር ጠገኑ። 14  የቤትሃኬሬም+ አውራጃ ገዢ የሆነው የሬካብ ልጅ ማልኪያህ የአመድ ቁልል በርን ጠገነ፤ እሱም ከሠራው በኋላ መዝጊያዎቹን፣ መወርወሪያዎቹንና መቀርቀሪያዎቹን ገጠመለት። 15  የምጽጳ+ አውራጃ ገዢ የሆነው የኮልሆዜ ልጅ ሻሉን የምንጭ በርን+ ጠገነ፤ እሱም ከሠራው በኋላ ጣሪያ አበጀለት፤ ከዚያም መዝጊያዎቹን፣ መወርወሪያዎቹንና መቀርቀሪያዎቹን ገጠመ፤ በተጨማሪም በንጉሡ የአትክልት ስፍራ+ ያለውን የሼላ የውኃ ገንዳ* ግንብ+ ከዳዊት ከተማ+ ተነስቶ ቁልቁል እስከሚወርደው ደረጃ+ ድረስ ጠገነ። 16  ከእሱ ቀጥሎ ደግሞ የቤትጹር+ አውራጃ እኩሌታ ገዢ የሆነው የአዝቡቅ ልጅ ነህምያ ከዳዊት የመቃብር ስፍራ+ ፊት ለፊት አንስቶ እስከ ሰው ሠራሹ ኩሬና+ እስከ ኃያላኑ ቤት ድረስ ገነባ። 17  ከእሱ ቀጥሎ ያለውን በባኒ ልጅ በረሁም ሥር ያሉት ሌዋውያን ጠገኑት፤ ከእሱ ቀጥሎ ደግሞ የቀኢላ+ አውራጃ እኩሌታ ገዢ የሆነው ሃሻብያህ የራሱን አውራጃ ጠገነ። 18  ከእሱ ቀጥሎ ያለውን የቀኢላ አውራጃ እኩሌታ ገዢ በሆነው በሄናዳድ ልጅ በባዋይ ሥር ያሉት ወንድሞቻቸው ጠገኑ። 19  ከእሱ ቀጥሎ ደግሞ የምጽጳ ገዢ የሆነው የኤጼር ልጅ የሹዋ+ በቅጥሩ ቅስት+ አጠገብ ወደሚገኘው የጦር መሣሪያ ግምጃ ቤት ከሚያስወጣው አቀበት ፊት ለፊት ያለውን ሌላኛውን ክፍል ጠገነ። 20  ከእሱ ቀጥሎ ደግሞ የዛባይ+ ልጅ ባሮክ የቅጥሩ ቅስት ከሚገኝበት አንስቶ እስከ ሊቀ ካህናቱ ኤልያሺብ+ ቤት መግቢያ ድረስ ያለውን ሌላኛውን ክፍል በቅንዓት ጠገነ። 21  ከእሱ ቀጥሎ የሃቆጽ ልጅ የሆነው የዑሪያህ ልጅ መሬሞት+ ከኤልያሺብ ቤት መግቢያ አንስቶ እስከ ኤልያሺብ ቤት መጨረሻ ድረስ ያለውን ሌላኛውን ክፍል ጠገነ። 22  ከእሱ ቀጥሎ ያለውን ደግሞ ካህናቱ ይኸውም የዮርዳኖስ አውራጃ*+ ሰዎች ጠገኑት። 23  ከእነሱ ቀጥሎ ቢንያምና ሃሹብ ከቤታቸው ፊት ለፊት ያለውን ጠገኑ። ከእነሱ ቀጥሎ ደግሞ የአናንያ ልጅ የሆነው የማአሴያህ ልጅ አዛርያስ ከራሱ ቤት አጠገብ ያለውን ጠገነ። 24  ከእሱ ቀጥሎ የሄናዳድ ልጅ ቢኑይ ከአዛርያስ ቤት አንስቶ እስከ ቅጥሩ ቅስትና+ እስከ ማዕዘኑ ድረስ ያለውን ሌላኛውን ክፍል ጠገነ። 25  ከእሱ ቀጥሎ የዑዛይ ልጅ ፓላል ከቅስቱ ፊት ለፊት ያለውን ቅጥርና በንጉሡ ቤት*+ አጠገብ በክብር ዘቦቹ ግቢ+ ውስጥ የሚገኘውን የላይኛውን ማማ ጠገነ። ከእሱ ቀጥሎ የፓሮሽ+ ልጅ ፐዳያህ ነበር። 26  እንዲሁም በኦፌል+ የሚኖሩት የቤተ መቅደስ አገልጋዮች*+ በስተ ምሥራቅ እስከ ውኃ በር+ ፊት ለፊት ድረስ ያለውን ቅጥርና ወጣ ያለውን ማማ ጠገኑ። 27  ከእነሱ ቀጥሎ የተቆአ+ ሰዎች ወጣ ካለው ትልቅ ማማ ፊት ለፊት አንስቶ እስከ ኦፌል ቅጥር ድረስ ያለውን ሌላኛውን ክፍል ጠገኑ። 28  ካህናቱ ከፈረስ በር+ በላይ ያለውን ጠገኑ፤ እያንዳንዳቸውም ከቤታቸው ፊት ለፊት ያለውን ጠገኑ። 29  ከእነሱ ቀጥሎ የኢሜር ልጅ ሳዶቅ+ ከራሱ ቤት ፊት ለፊት ያለውን ጠገነ። ከእሱ ቀጥሎ ደግሞ የምሥራቅ በር+ ጠባቂ የሆነው የሸካንያህ ልጅ ሸማያህ ጠገነ። 30  ከእሱ ቀጥሎ የሸሌምያህ ልጅ ሃናንያህና የጻላፍ ስድስተኛ ልጅ ሃኑን ሌላኛውን ክፍል ጠገኑ። ከዚያ ቀጥሎ ደግሞ የቤራክያህ ልጅ መሹላም+ ከራሱ አዳራሽ ፊት ለፊት ያለውን ጠገነ። 31  ከእሱ ቀጥሎ ደግሞ የወርቅ አንጥረኞች ማኅበር አባል የሆነው ማልኪያህ በመቆጣጠሪያ በር አጠገብ እስከሚገኘው እስከ ቤተ መቅደስ አገልጋዮቹና*+ እስከ ነጋዴዎቹ ቤት እንዲሁም በማዕዘኑ ላይ እስካለው ሰገነት ድረስ ያለውን ጠገነ። 32  የወርቅ አንጥረኞቹና ነጋዴዎቹም በሰገነቱ ማዕዘን ላይ በሚገኘው ክፍልና በበግ በር+ መካከል ያለውን ጠገኑ።

የግርጌ ማስታወሻ

ወይም “ወሰኑት።”
ቃል በቃል “አንገታቸውን በማስገባት።”
ቃል በቃል “ዙፋን።”
ወይም “ኤፍራጥስን ተሻግሮ።”
ወይም “ከሽቶ ቀማሚዎች።”
ወይም “የተለካውን ክፍል።”
ወደ 445 ሜትር ገደማ ነው። ከተጨማሪው መረጃ ላይ ለ14ን ተመልከት።
ሼላ ማለት ‘ቦይ’ ማለት ነው። ይህ የውኃ ገንዳ ውኃ በቦይ አማካኝነት የሚገባበት ገንዳ ነው።
“በአቅራቢያው ያለው አውራጃ” ማለትም ሊሆን ይችላል።
ወይም “በንጉሡ ቤተ መንግሥት።”
ወይም “ናታኒሞች።” ቃል በቃል “የተሰጡ ሰዎች።”
ወይም “ናታኒሞቹና።” ቃል በቃል “የተሰጡት ሰዎችና።”