ናሆም 2:1-13

  • ነነዌ ትጠፋለች (1-13)

    • “የወንዞቹ በሮች ይከፈታሉ” (6)

2  የሚበትን መጥቶብሻል።*+ ምሽጎቹን ጠብቂ። መንገዱን በትኩረት ተመልከቺ። ወገብሽን ታጠቂ፤* ኃይልሽንም ሁሉ አሰባስቢ።   ይሖዋ የያዕቆብን ክብርከእስራኤል ክብር ጋር ይመልሳልና፤አጥፊዎች አጥፍተዋቸዋልና፤+ቀንበጦቻቸውንም ከጥቅም ውጭ አድርገዋል።   የኃያላኑ ጋሻዎች ቀይ ቀለም የተነከሩ ናቸው፤ተዋጊዎቹ ደማቅ ቀይ ልብስ ለብሰዋል። ለጦርነት ዝግጁ በሚሆንበት ቀን፣የጦር ሠረገላው ብረቶች እንደ እሳት ያብረቀርቃሉ፤ከጥድ የተሠሩት ረጃጅም ጦሮች ይወዛወዛሉ።   የጦር ሠረገሎቹ በጎዳናዎቹ ላይ ይከንፋሉ። በአደባባዮቹም ላይ ወዲያ ወዲህ ይራወጣሉ። እንደሚነድ ችቦ ያበራሉ፤ እንደ መብረቅም ያንጸባርቃሉ።   እሱ አለቆቹን ይጠራል። እነሱ ወደ ፊት ሲገሰግሱ ይሰናከላሉ። ወደ ቅጥሯ እየተጣደፉ ይሄዳሉ፤መከላከያም ያቆማሉ።   የወንዞቹ በሮች ይከፈታሉ፤ቤተ መንግሥቱም ይቀልጣል።*   ጉዳዩ ታውጇል፦* እሷ ተጋልጣለች፤ተማርካ ተወስዳለች፤ ሴቶች ባሪያዎቿም ያቃስታሉ፤ደረታቸውን* እየደቁ እንደ ርግብ ያላዝናሉ።   ነነዌ ከተቆረቆረችበት+ ጊዜ አንስቶ እንደ ውኃ ኩሬ ነበረች፤አሁን ግን እነሱ ይሸሻሉ። አንዳንዶች “ቁሙ! ቁሙ!” ብለው ይጮኻሉ። ሆኖም ወደ ኋላ የሚዞር የለም።+   ብሩን ዝረፉ፤ ወርቁን ዝረፉ! የተከማቸው ሀብት ስፍር ቁጥር የለውም። በብዙ ዓይነት የከበሩ ዕቃዎች ተሞልቷል። 10  ከተማዋ ባዶና ወና እንዲሁም ባድማ ሆናለች!+ ልባቸው በፍርሃት ቀልጧል፤ ጉልበታቸው ተብረክርኳል፤ ወገባቸውም ተንቀጥቅጧል፤የሁሉም ፊት ቀልቷል። 11  ደቦል አንበሶቹ የሚመገቡበት፣ማንም ሳያስፈራቸው አንበሳው ግልገሎቹን እየመራ የሚወጣበትየአንበሶቹ ዋሻ የት አለ?+ 12  አንበሳው ለግልገሎቹ የሚበቃቸውን ያህል አደነ፤ለእንስቶቹም አንቆ ገደለላቸው። ጎሬውን በታደኑ እንስሶች፣ዋሻውንም በተቦጫጨቁ እንስሶች ሞላ። 13  “እነሆ፣ በአንቺ ላይ ተነስቻለሁ” ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ፤+“የጦር ሠረገላዋን በጭስ መካከል አቃጥላለሁ፤+ደቦል አንበሶችሽንም ሰይፍ ይበላቸዋል። አደንሽን ከምድር ገጽ አስወግዳለሁ፤የመልእክተኞችሽም ድምፅ ከእንግዲህ ወዲህ አይሰማም።”+

የግርጌ ማስታወሻ

ነነዌን ያመለክታል።
ቃል በቃል “ዳሌዎችሽን አጠንክሪ።”
ወይም “ይፈርሳል።”
ወይም “ተቆርጧል።”
ቃል በቃል “ልባቸውን።”