አሞጽ 4:1-13

  • ለባሳን ላሞች የተነገረ የማስጠንቀቂያ መልእክት (1-3)

  • ይሖዋ የእስራኤልን የሐሰት አምልኮ አንቋሸሸ (4, 5)

  • እስራኤል የተሰጠውን ተግሣጽ አልተቀበለም (6-13)

    • “አምላክህን ለመገናኘት ተዘጋጅ” (12)

    • ‘አምላክ ሐሳቡን ለሰው ይገልጻል’ (13)

4  “እናንተ በሰማርያ ተራራ ላይ ያላችሁ፣+ችግረኛ በሆኑ ሰዎች ላይ ግፍ የምትፈጽሙና+ ድሆችን የምትጨቁኑ ሴቶች፣ባሎቻችሁንም* ‘የምንጠጣው ነገር አምጡልን!’የምትሉ የባሳን ላሞች ሆይ፣ ይህን ቃል ስሙ።   ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ በቅድስናው ምሏል፤‘“እነሆ፣ እናንተን በሜንጦ፣ከእናንተ የቀሩትንም በመንጠቆ የሚያነሳበት ቀን እየመጣባችሁ ነው።   እያንዳንዳችሁ ከፊታችሁ በምታገኟቸው፣ በቅጥሩ ላይ ባሉት ክፍተቶች በኩል ትወጣላችሁ፤ወደ ሃርሞንም ትጣላላችሁ” ይላል ይሖዋ።’   ‘ወደ ቤቴል ኑና ኃጢአት ሥሩ፤*+ወደ ጊልጋልም ሄዳችሁ ብዙ ኃጢአት ፈጽሙ!+ በማለዳ መሥዋዕቶቻችሁን፣+በሦስተኛውም ቀን አሥራቶቻችሁን* አቅርቡ።+   እርሾ ያለበትን ዳቦ የሚቃጠል የምስጋና መሥዋዕት አድርጋችሁ አቅርቡ፤+በፈቃዳችሁ የምታቀርቡትንም መባ በአዋጅ አስነግሩ! የእስራኤል ሕዝብ ሆይ፣ ማድረግ የምትወዱት ይህን ነውና’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።   ‘እኔም በከተሞቻችሁ ሁሉ አፋችሁን ባዶ አደረግኩት፤*በቤታችሁም ሁሉ የምትበሉት ነገር አሳጣኋችሁ፤+እናንተ ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም’+ ይላል ይሖዋ።   ‘በተጨማሪም መከር ከመድረሱ ከሦስት ወር በፊት ዝናብ ከለከልኳችሁ፤+በአንዱ ከተማ ዝናብ እንዲዘንብ ሳደርግ በሌላው ከተማ ግን እንዳይዘንብ አደረግኩ። አንዱ እርሻ ዝናብ ያገኛል፤ዝናብ ያላገኘው ሌላው እርሻ ግን ይደርቃል።   በሁለት ወይም በሦስት ከተሞች የሚኖሩ ሰዎች ውኃ ለመጠጣት ወደ አንዲት ከተማ እያዘገሙ ሄዱ፤+ይሁንና ጥማቸውን ማርካት አልቻሉም፤እናንተ ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም’+ ይላል ይሖዋ።   ‘በሚያቃጥል ሙቀትና በዋግ መታኋችሁ።+ የአትክልት ስፍራዎቻችሁንና የወይን እርሻዎቻችሁን አበዛችሁ፤ይሁንና የበለስ ዛፎቻችሁንና የወይራ ዛፎቻችሁን አንበጣ ይበላቸዋል፤+ያም ሆኖ ወደ እኔ አልተመለሳችሁም’+ ይላል ይሖዋ። 10  ‘በግብፅ ላይ የደረሰውን ዓይነት ቸነፈር ሰደድኩባችሁ።+ ወጣቶቻችሁን በሰይፍ ገደልኩ፤+ ፈረሶቻችሁንም ማረክሁ።+ የሰፈሮቻችሁ ግማት ወደ አፍንጫችሁ እንዲገባ አደረግኩ፤+እናንተ ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም’ ይላል ይሖዋ። 11  ‘ሰዶምንና ገሞራን እንደገለበጥኳቸው ሁሉምድራችሁን ገለበጥኩ።+ እናንተም ከእሳት እንደተነጠቀ ጉማጅ ነበራችሁ፤ያም ሆኖ ወደ እኔ አልተመለሳችሁም’+ ይላል ይሖዋ። 12  ስለዚህ እስራኤል ሆይ፣ እንዲሁ አደርግብሃለሁ። እስራኤል ሆይ፣ ይህን ነገር ስለማደርግብህአምላክህን ለመገናኘት ተዘጋጅ። 13  እነሆ፣ ተራሮችን የሠራው፣+ ነፋስን የፈጠረው እሱ ነው፤+ሐሳቡ ምን እንደሆነ ለሰው ይነግረዋል፤የንጋት ብርሃንን ያጨልማል፤+በምድር ላይ ያሉ ከፍ ያሉ ስፍራዎችን ይረግጣል፤+ስሙ የሠራዊት አምላክ ይሖዋ ነው።”

የግርጌ ማስታወሻ

ወይም “ጌቶቻችሁንም።”
ወይም “ዓምፁ።”
ወይም “አንድ አሥረኛችሁን።”
ወይም “የምትበሉት ምግብ አልሰጠኋችሁም።” ቃል በቃል “ጥርሳችሁን አጠራሁ።”