አሞጽ 5:1-27

  • “ድንግሊቱ እስራኤል ወድቃለች” (1-3)

  • አምላክን ፈልጉ፤ በሕይወትም ትኖራላችሁ (4-17)

    • “ክፉ የሆነውን ጥሉ፤ መልካም የሆነውንም ውደዱ” (15)

  • የይሖዋ ቀን የጨለማ ቀን ነው (18-27)

    • የእስራኤላውያን መሥዋዕት ተቀባይነት አጣ (22)

5  “የእስራኤል ቤት ሆይ፣ በእናንተ ላይ እንደ ሙሾ* አድርጌ የምናገረውን ይህን ቃል ስሙ፦   ‘ድንግሊቱ እስራኤል ወድቃለች፤ዳግመኛም አትነሳም። በገዛ ምድሯ ተጥላለች፤የሚያነሳትም የለም።’   “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦ ‘አንድ ሺህ ሰዎች ይዛ የምትዘምት ከተማ መቶ ሰዎች ብቻ ይቀሯታል፤መቶ ሰዎች ይዛ የምትዘምት ከተማም አሥር ሰዎች ብቻ ይቀሯታል። ይህ በእስራኤል ቤት ላይ ይደርሳል።’+   “ይሖዋ ለእስራኤል ቤት እንዲህ ይላልና፦ ‘እኔን ፈልጉ፤ በሕይወትም ትኖራላችሁ።+   ቤቴልን አትፈልጉ፤+ወደ ጊልጋል አትሂዱ፤+ ወደ ቤርሳቤህም አትሻገሩ፤+ጊልጋል ያለጥርጥር በግዞት ትወሰዳለችና፤+ቤቴልም እንዳልነበረች ትሆናለች።*   ይሖዋን ፈልጉ፤ በሕይወትም ትኖራላችሁ፤+አለዚያ በዮሴፍ ቤት ላይ ቁጣው እንደ እሳት ይነድዳል፤ቤቴልንም ይበላል፤ የሚያጠፋውም አይኖርም።   እናንተ ፍትሕን ወደ ጭቁኝ* ትለውጣላችሁ፤ጽድቅንም ወደ ምድር ትጥላላችሁ።+   የኪማ ኅብረ ከዋክብትንና* የከሲል ኅብረ ከዋክብትን* የሠራው፣+ድቅድቅ ጨለማን ወደ ንጋት ብርሃን የሚለውጠው፣ቀኑንም እንደ ሌሊት ጨለማ የሚያደርገው፣+ወደ ምድር ያፈሰው ዘንድየባሕርን ውኃ ወደ እሱ የሚጠራው፣+ስሙ ይሖዋ ነው።   የተመሸጉትን ቦታዎች በማውደም፣ብርቱ በሆነው ላይ ድንገተኛ ጥፋት ያመጣል። 10  እነሱ በከተማዋ በር ላይ ሆነው የሚወቅሱትን ይጠላሉ፤እውነት የሚናገሩትንም ይጸየፋሉ።+ 11  ድሃው ለእርሻ ቦታው ኪራይ* እንዲከፍል ስለምታደርጉ፣እህሉንም በግብር መልክ ስለምትወስዱ፣+በተጠረበ ድንጋይ በሠራችሁት ቤት ውስጥ አትኖሩም፤+ደግሞም ከተከላችኋቸው ምርጥ የወይን ተክሎች የሚገኘውን የወይን ጠጅ አትጠጡም።+ 12  ዓመፃችሁ* ምን ያህል እንደበዛናኃጢአታችሁ ምንኛ ታላቅ እንደሆነ አውቃለሁና፤ጻድቁን ትጨቁናላችሁ፤ጉቦ* ትቀበላላችሁ፤በከተማዋም በር ላይ የድሆችን መብት ትነፍጋላችሁ።+ 13  ስለሆነም ጥልቅ ማስተዋል ያላቸው ሰዎች በዚያን ጊዜ ዝም ይላሉ፤የመከራ ጊዜ ይሆናልና።+ 14  በሕይወት እንድትኖሩ+መልካም የሆነውን እንጂ ክፉውን አትፈልጉ።+ የሠራዊት አምላክ ይሖዋምእንደተናገራችሁት ከእናንተ ጋር ይሆናል።+ 15  ክፉ የሆነውን ጥሉ፤ መልካም የሆነውንም ውደዱ፤+በከተማዋም በር ላይ ፍትሕ እንዲሰፍን አድርጉ።+ የሠራዊት አምላክ ይሖዋከዮሴፍ ለቀሩት ሰዎች ሞገሱን ያሳያቸው ይሆናል።’+ 16  “ስለዚህ ይሖዋ፣ የሠራዊት አምላክ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘በየአደባባዩ ዋይታ ይሆናል፤በየመንገዱም ሰዎች “ወዮ! ወዮ!” ይላሉ። ገበሬዎችን ለለቅሶ፣አስለቃሾችንም ለዋይታ ይጠራሉ።’ 17  ‘በየወይን እርሻውም ዋይታ ይኖራል፤+እኔ በመካከልህ አልፋለሁና’ ይላል ይሖዋ። 18  ‘የይሖዋን ቀን ለሚናፍቁ ወዮላቸው!+ የይሖዋ ቀን ለእናንተ ምን ያመጣ ይሆን?+ ያ ቀን ጨለማ እንጂ ብርሃን አይሆንም።+ 19  ይህም ሰው ከአንበሳ ሲሸሽ ድብ እንደሚያጋጥመው፣ወደ ቤት ገብቶ እጁን በግድግዳው ላይ ሲያስደግፍም እባብ እንደሚነድፈው ዓይነት ይሆናል። 20  የይሖዋ ቀን ብርሃን የሌለበት ድቅድቅ ጨለማ ይሆን የለም?ደግሞስ የብርሃን ጸዳል የሌለበት ጨለማ ይሆን የለም? 21  በዓሎቻችሁን እጠላለሁ፤ ደግሞም እንቃለሁ፤+የተቀደሱ ጉባኤዎቻችሁ መዓዛም ደስ አያሰኘኝም። 22  ሙሉ በሙሉ የሚቃጠሉ መባዎችና የስጦታ መባዎች ብታቀርቡልኝ እንኳእነዚህ መባዎች አያስደስቱኝም፤+ለኅብረት መሥዋዕት የምታቀርቡልኝን የሰቡ እንስሳትም በሞገስ ዓይን አልመለከትም።+ 23  የተደበላለቁ መዝሙሮችህን ከእኔ አርቅ፤በባለ አውታር መሣሪያዎች የምትጫወተውንም ዜማ መስማት አልፈልግም።+ 24  ፍትሕ እንደ ውኃ፣+ጽድቅም ያለማቋረጥ እንደሚወርድ ጅረት ይፍሰስ። 25  የእስራኤል ቤት ሆይ፣ ለ40 ዓመት በምድረ በዳ በቆያችሁበት ጊዜመሥዋዕትና የስጦታ መባ አቅርባችሁልኝ ነበር?+ 26  አሁንም ለራሳችሁ የሠራችኋቸውን፣ ንጉሣችሁ የሆነውን የሳኩትን እንዲሁም የኪዋንን* ምስሎች፣ይኸውም የአምላካችሁን ኮከብ ተሸክማችሁ ትሄዳላችሁ። 27  እኔም ከደማስቆ ወዲያ ርቃችሁ በግዞት እንድትወሰዱ አደርጋለሁ’+ ይላል ስሙ ይሖዋ የሆነው የሠራዊት አምላክ።”+

የግርጌ ማስታወሻ

ወይም “እንደ ሐዘን እንጉርጉሮ።”
“ምትሃታዊ ድርጊት የሚፈጸምባት ቦታ ትሆናለች” ማለትም ሊሆን ይችላል።
ወይም “መራራነት።”
የኦርዮን ኅብረ ከዋክብት ሊሆን ይችላል።
በቶረስ ኅብረ ከዋክብት የታቀፉ ፐልያዲስ የሚባሉ ከዋክብት ሊሆኑ ይችላሉ።
ወይም “የመሬት ቀረጥ።”
ወይም “መረጃን ለመደበቅ የሚሰጥ ገንዘብ።”
ወይም “ወንጀላችሁ።”
እነዚህ ጣዖታት እንደ አምላክ ይመለክ የነበረውን የሳተርንን ፕላኔት ሊያመለክቱ ይችላሉ።