አሞጽ 6:1-14

  • ዘና ብለው የሚኖሩ ወዮላቸው! (1-14)

    • ከዝሆን ጥርስ የተሠራ አልጋ፤ የወይን ጠጅ የተሞላ ጽዋ (4, 6)

6  “በጽዮን በራሳቸው ተማምነው* የሚኖሩ፣በሰማርያም ተራራ ያለስጋት የተቀመጡ ወዮላቸው!+እነሱ ከብሔራት ሁሉ መካከል ዋነኛ በሆነው ብሔር ውስጥ የጎላ ስፍራ ያላቸው ናቸው፤ የእስራኤል ቤትም ወደ እነሱ ይመጣል።   ወደ ካልኔ ተሻግራችሁ ተመልከቱ። ከዚያም ተነስታችሁ ወደ ታላቋ ሃማት+ ሂዱ፤የፍልስጤማውያን ከተማ ወደሆነችውም ወደ ጌት ውረዱ። እነሱ ከእነዚህ መንግሥታት* ይሻላሉ?የምድራቸውስ ስፋት ከእናንተ ይበልጣል?   የጥፋትን ቀን ከአእምሯችሁ አውጥታችሁ+የዓመፅ አገዛዝ* እንዲሰፍን ታደርጋላችሁ?+   የመንጋውን ጠቦቶች እንዲሁም የሰቡ ጥጃዎችን* እየበሉ+ከዝሆን ጥርስ በተሠራ አልጋ ላይ ይተኛሉ፤+ በድንክ አልጋም ላይ ይንጋለላሉ፤+   በገና* እየተጫወቱ የመጣላቸውን ዘፈን ያቀናብራሉ፤+እንደ ዳዊትም የሙዚቃ መሣሪያዎች+ ይፈለስፋሉ፤   በትላልቅ ጽዋዎች የወይን ጠጅ ሞልተው ይጠጣሉ፤+ምርጥ የሆኑ ዘይቶችም ይቀባሉ። በዮሴፍ ላይ ስለደረሰው መቅሰፍት ግን ግድ የላቸውም።+   ስለዚህ እነሱ በግዞት ከሚወሰዱት መካከል የመጀመሪያዎቹ ይሆናሉ፤+ተንጋለው በመዝናናት የሚያሳልፉት ጊዜም ያበቃል።   ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ በራሱ* ምሏል’+ ይላል የሠራዊት አምላክ ይሖዋ፤‘“የያዕቆብን ኩራት እጸየፋለሁ፤+የማይደፈሩ ማማዎቹን እጠላለሁ፤+ከተማዋንና በውስጧ ያለውን ነገር ሁሉ አሳልፌ እሰጣለሁ።+  “‘“በአንድ ቤት ውስጥ አሥር ሰዎች ቢቀሩ እነሱም ይሞታሉ። 10  እነሱን አንድ በአንድ አውጥቶ ለማቃጠል አንድ ዘመድ* ይመጣል። አጥንቶቻቸውን ከቤት ውስጥ ያወጣል፤ ከዚያም በቤቱ ውስጠኛ ክፍል ላለ ሰው ‘ከአንተ ጋር የቀሩ ሌሎች ሰዎች አሉ?’ ይለዋል። ሰውየውም ‘ማንም የለም!’ ይላል። ከዚያም ‘ዝም በል! ይህ የይሖዋ ስም የሚጠራበት ጊዜ አይደለም’ ይላል።” 11  ትእዛዝ የሰጠው ይሖዋ ነውና፤+እሱም ትልቁን ቤት አመድ፣ትንሹንም ቤት የፍርስራሽ ክምር ያደርጋል።+ 12  ፈረሶች በቋጥኝ ላይ ይሮጣሉ?ሰውስ እዚያ ላይ በከብት ያርሳል? እናንተ ፍትሕን ወደ መርዛማ ተክል፣የጽድቅንም ፍሬ ወደ ጭቁኝ* ለውጣችኋልና።+ 13  እናንተ ከንቱ በሆነ ነገር ሐሴት ታደርጋላችሁ፤ደግሞም “በራሳችን ብርታት ኃይለኞች ሆነን የለም?”* ትላላችሁ።+ 14  ስለዚህ የእስራኤል ቤት ሆይ፣ በእናንተ ላይ አንድ ብሔር አመጣለሁ’+ ይላል የሠራዊት አምላክ ይሖዋ፤‘እነሱም ከሌቦሃማት*+ አንስቶ እስከ አረባ ደረቅ ወንዝ* ድረስ ይጨቁኗችኋል።’”

የግርጌ ማስታወሻ

ወይም “ዘና ብለው።”
የይሁዳንና የእስራኤልን መንግሥታት የሚያመለክት ሳይሆን አይቀርም።
ቃል በቃል “ወንበር።”
ወይም “ወይፈኖችን።”
ወይም “ባለ አውታር መሣሪያ።”
ወይም “በነፍሱ።”
ቃል በቃል “የአባቱ ወንድም።”
ወይም “መራራነት።”
ቃል በቃል “ለራሳችን ቀንዶች ወስደን የለም?”
ወይም “ከሃማት መግቢያ።”