አሞጽ 8:1-14

  • የበጋ ፍሬ የያዘው ቅርጫት ራእይ (1-3)

  • ጨቋኞች ተወገዙ (4-14)

    • መንፈሳዊ ረሃብ (11)

8  ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ይህን አሳየኝ፦ እነሆ፣ የበጋ ፍሬ* የያዘ ቅርጫት ነበር።  ከዚያም “አሞጽ፣ ምን ይታይሃል?” አለኝ። እኔም “የበጋ ፍሬ የያዘ ቅርጫት” ብዬ መለስኩ። ይሖዋም እንዲህ አለኝ፦ “የሕዝቤ የእስራኤል ፍጻሜ ደርሷል። ከእንግዲህ ወዲህ ይቅር አልላቸውም።+  ‘በዚያን ቀን የቤተ መቅደሱ መዝሙሮች ወደ ዋይታ ይቀየራሉ’+ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ። ‘በየቦታው የተጣሉ ብዙ አስከሬኖች ይኖራሉ፤+ ዝምታ ይስፈን!’   እናንተ ድሆችን የምትረጋግጡ፣በምድሪቱ ላይ ያሉትንም የዋሆች የምታጠፉ ይህን ስሙ፤+   እንዲህም ትላላችሁ፦ ‘እህላችንን መሸጥ እንድንችል የወር መባቻው የሚያልፈው መቼ ነው?+አዝመራችንንስ መሸጥ እንድንችል ሰንበት+ የሚያልፈው መቼ ነው? ያን ጊዜ በሐሰተኛ ሚዛን ለማጭበርበርየኢፍ* መስፈሪያውን ማሳነስ፣ሰቅሉንም* ከፍ ማድረግ እንችላለን፤+   ደግሞም ችግረኛውን በብር፣ድሃውንም በጥንድ ጫማ ዋጋ እንገዛለን፤+መናኛውንም እህል መሸጥ እንችላለን።’   የያዕቆብ ክብር+ የሆነው ይሖዋ በራሱ ምሏል፦‘ሥራቸውን ሁሉ ፈጽሞ አልረሳም።+   ከዚህ የተነሳ አገሪቱ* ትሸበራለች፤በውስጧም የሚኖሩ ሁሉ ለሐዘን ይዳረጋሉ።+ ምድሪቱ በሙሉ እንደ አባይ ወደ ላይ አትነሳም?በግብፅ እንዳለውም የአባይ ወንዝ ወደ ላይ ከወጣች በኋላ ተመልሳ ወደ ታች አትወርድም?’+   ‘በዚያ ቀን’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ፣‘ፀሐይ በቀትር እንድትጠልቅ አደርጋለሁ፤ብሩህ በሆነ ቀንም ምድሪቱን አጨልማለሁ።+ 10  በዓሎቻችሁን ወደ ሐዘን፣መዝሙሮቻችሁንም ሁሉ ወደ ሙሾ* እለውጣለሁ።+ ወገብን ሁሉ ማቅ አስታጥቃለሁ፤ ራስንም ሁሉ እመልጣለሁ፤ለአንድያ ልጅ እንደሚለቀስ ያለቅሳሉ፤ፍጻሜውም እንደ መራራ ቀን ይሆናል።’ 11  ‘እነሆ፣ በምድሪቱ ላይ ረሃብ የምሰድበት ጊዜ ይመጣል’ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ፤‘ረሃቡ የይሖዋን ቃል የመስማት ረሃብ እንጂምግብን የመራብ ወይም ውኃን የመጠማት አይደለም።+ 12  እነሱ ከባሕር ወደ ባሕር፣ከሰሜንም ወደ ምሥራቅ* ይባዝናሉ። የይሖዋን ቃል ፍለጋ በየቦታው ይንከራተታሉ፤ ሆኖም አያገኙትም። 13  በዚያ ቀን፣ ውብ የሆኑት ደናግልናወጣት ወንዶች ከውኃ ጥም የተነሳ ራሳቸውን ይስታሉ፤ 14  በሰማርያ በደል+ የሚምሉደግሞም “ዳን ሆይ፣ ሕያው በሆነው በአምላክህ እምላለሁ!”+ እንዲሁም “ሕያው በሆነው በቤርሳቤህ መንገድ+ እምላለሁ!” የሚሉ ሰዎች፣ ይወድቃሉ፤ ዳግመኛም አይነሱም።’”+

የግርጌ ማስታወሻ

የበጋ ፍሬ በዋነኝነት የሚያመለክተው “በለስን” ሲሆን “ቴምርንም” ሊጨምር ይችላል።
ከተጨማሪው መረጃ ላይ ለ14ን ተመልከት።
ከተጨማሪው መረጃ ላይ ለ14ን ተመልከት።
ወይም “ምድሪቱ።”
ወይም “ወደ ሐዘን እንጉርጉሮ።”
ወይም “ፀሐይ መውጫ።”