አብድዩ 1:1-21

  • ትዕቢተኛው ኤዶም ይዋረዳል (1-9)

  • ኤዶም በያዕቆብ ላይ የፈጸመው ግፍ (10-14)

  • “ይሖዋ በብሔራት ሁሉ ላይ የሚነሳበት ቀን” (15, 16)

  • የያዕቆብ ቤት ቀድሞ ወደነበረበት ሁኔታ ይመለሳል (17-21)

    • የያዕቆብ ቤት ኤዶምን ይበላል (18)

    • ‘ንግሥናው የይሖዋ ይሆናል’ (21)

 የአብድዩ* ራእይ፦ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ስለ ኤዶም እንዲህ ይላል፦+ “ከይሖዋ የመጣ አንድ መልእክት ሰምተናል፤በብሔራት መካከል አንድ መልእክተኛ ተልኳል፦ ‘ተነሱ፤ እሷን ለመውጋት እንዘጋጅ።’”+   “እነሆ፣ በብሔራት መካከል ከቁብ የማትቆጠር አድርጌሃለሁ፤አንተ እጅግ ተንቀሃል።+   አንተ በቋጥኝ መሸሸጊያ ውስጥ የምትኖር፣መኖሪያህን በከፍታ ቦታ ላይ ያደረግክ፣በልብህ ‘ማን ወደ ምድር ሊያወርደኝ ይችላል?’ የምትል፣የልብህ እብሪት አታሎሃል።+   መኖሪያህን እንደ ንስር ከፍ ብታደርግ*ወይም ጎጆህን በከዋክብት መካከል ብትሠራ እንኳእኔ ከዚያ አወርድሃለሁ” ይላል ይሖዋ።   “ሌቦች ወደ አንተ ቢመጡ፣ ዘራፊዎች በሌሊት ቢገቡ(ታላቅ ጥፋት በደረሰብህ ነበር!)* የሚሰርቁት የሚፈልጉትን ያህል ብቻ አይደለም? ደግሞስ ወይን ለቃሚዎች ወደ አንተ ቢመጡጥቂት ቃርሚያ አያስቀሩም?+   ኤሳው ምንኛ ተበረበረ! የተደበቀው ውድ ሀብቱ ምንኛ ተፈለገ!   እስከ ድንበሩ ድረስ እንድትሄድ አስገደዱህ። አጋሮችህ* ሁሉ አታለውሃል። ከአንተ ጋር ሰላማዊ ግንኙነት የነበራቸው ሰዎች አይለውብሃል። ከአንተ ጋር የሚበሉ ሰዎች ከሥርህ መረብ ይዘረጉብሃል፤አንተ ግን አታስተውለውም።   በዚያ ቀን” ይላል ይሖዋ፣“ጥበበኞችን ከኤዶም አላጠፋም?+ማስተዋልንስ ከኤሳው ተራራማ ምድር አላስወግድም?   ቴማን+ ሆይ፣ ተዋጊዎችሽ ይሸበራሉ፤+ምክንያቱም እያንዳንዳቸው ታርደው ከተራራማው የኤሳው ምድር ይወገዳሉ።+ 10  በወንድምህ በያዕቆብ ላይ በተፈጸመው ግፍ የተነሳ+ኀፍረት ትከናነባለህ፤+ለዘላለምም ትጠፋለህ።+ 11  ዳር ቆመህ ትመለከት በነበረበት ጊዜ፣እንግዶች ሠራዊቱን ማርከው በወሰዱበትና+የባዕድ አገር ሰዎች በበሩ ገብተው በኢየሩሳሌም ላይ ዕጣ በተጣጣሉበት ጊዜ፣+አንተም ልክ እንደ እነሱ አደረግክ። 12  በወንድምህ ቀን ይኸውም ወንድምህ ክፉ ነገር በደረሰበት ቀን መፈንደቅ አይገባህም ነበር፤+የይሁዳ ሕዝብ በጠፋበት ቀን ሐሴት ማድረግ አልነበረብህም፤+ደግሞም በጭንቀታቸው ቀን በእብሪት መናገር አይገባህም ነበር። 13  በጥፋታቸው ቀን ወደ ሕዝቤ በር መምጣት አልነበረብህም፤+በጥፋቱ ቀን በደረሰበት መከራ መፈንደቅ አይገባህም ነበር፤ደግሞም ጥፋት በደረሰበት ቀን ሀብቱን መውሰድ አልነበረብህም።+ 14  የሚሸሹትን የይሁዳ ሰዎች ለመግደል መንታ መንገድ ላይ መቆም አይገባህም ነበር፤+በጭንቀቱም ቀን በሕይወት የተረፉትን አሳልፈህ መስጠት አልነበረብህም።+ 15  ይሖዋ በብሔራት ሁሉ ላይ የሚነሳበት ቀን ቀርቧልና።+ አንተ በእሱ ላይ እንዳደረግከው በአንተም ላይ ይደረጋል።+ በሌሎች ላይ ያደረግከው ነገር በገዛ ራስህ ላይ ይመለሳል። 16  እናንተ በቅዱሱ ተራራዬ ላይ እንደጠጣችሁ፣ልክ እንደዚሁ ብሔራት በሙሉ ዘወትር ይጠጣሉ።+ ይጠጣሉ፤ ደግሞም ይጨልጡታል፤ፈጽሞ እንዳልነበሩም ይሆናሉ። 17  ያመለጡት ግን በጽዮን ተራራ ላይ ይሆናሉ፤+እሱም የተቀደሰ ይሆናል፤+የያዕቆብ ቤት ሰዎችም የራሳቸው የሆኑትን ነገሮች ይወርሳሉ።+ 18  የያዕቆብ ቤት እሳት፣የዮሴፍም ቤት ነበልባል ይሆናል፤የኤሳው ቤት ደግሞ እንደ ገለባ ይሆናል፤እነሱም ያቃጥሏቸዋል፤ ይበሏቸዋልም፤ከኤሳውም ቤት የሚተርፍ አይኖርም፤+ይሖዋ ራሱ ተናግሯልና። 19  እነሱ ኔጌብንና የኤሳውን ተራራማ ምድር፣+ሸፌላንና የፍልስጤምን ምድር ይወርሳሉ።+ የኤፍሬምን መሬትና የሰማርያን መሬት ይወርሳሉ፤+ቢንያምም ጊልያድን ይወርሳል። 20  እስከ ሰራፕታ+ ድረስ ያለው የከነአናውያን ምድር፣ከዚህ የመከላከያ ግንብ* በግዞት የተወሰዱት ሰዎች+ ይኸውም የእስራኤል ሕዝብ ይዞታ ይሆናል። በሰፋራድ የነበሩት ከኢየሩሳሌም በግዞት የተወሰዱ ሰዎችም የኔጌብን ከተሞች ይወርሳሉ።+ 21  ሕዝቡን የሚታደጉ ሰዎችም በኤሳው ተራራማ ምድር ላይ ለመፍረድ+ወደ ጽዮን ተራራ ይወጣሉ፤ንግሥናውም የይሖዋ ይሆናል።”+

የግርጌ ማስታወሻ

“የይሖዋ አገልጋይ” የሚል ትርጉም አለው።
“እንደ ንስር መጥቀህ ብትበር” ማለትም ሊሆን ይችላል።
“ምን ያህል ጥፋት ያደርሱ ነበር?” ማለትም ሊሆን ይችላል።
ወይም “ከአንተ ጋር ቃል ኪዳን የገቡ።”
ወይም “ምሽግ።”