በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የኢሳይያስ መጽሐፍ

ምዕራፎች

የመጽሐፉ ይዘት

  • 1

    • አንድ አባትና ዓመፀኛ ልጆቹ (1-9)

    • ይሖዋ ለታይታ ተብሎ የሚቀርብን አምልኮ ይጠላል (10-17)

    • “የተፈጠረውን ችግር ተወያይተን እንፍታ” (18-20)

    • ጽዮን ዳግመኛ የታመነች ከተማ ትሆናለች (21-31)

  • 2

    • የይሖዋ ተራራ ከፍ ከፍ ይላል (1-5)

      • ሰይፋቸውን ማረሻ ያደርጋሉ (4)

    • በይሖዋ ቀን ትዕቢተኞች ይዋረዳሉ (6-22)

  • 3

    • የይሁዳ መሪዎች ሕዝቡን ያስታሉ (1-15)

    • እየተጣቀሱ የሚሄዱት የጽዮን ሴቶች ተፈረደባቸው (16-26)

  • 4

    • ሰባት ሴቶች ለአንድ ወንድ (1)

    • ይሖዋ እንዲያቆጠቁጥ ያደረገው ተክል ክብር የተላበሰ ይሆናል (2-6)

  • 5

    • ስለ ይሖዋ የወይን እርሻ የተዘመረ መዝሙር (1-7)

    • በይሖዋ የወይን እርሻ ላይ የተነገረ ወዮታ (8-24)

    • በሕዝቡ ላይ የነደደው የአምላክ ቁጣ (25-30)

  • 6

    • ይሖዋ በቤተ መቅደሱ ውስጥ ሆኖ በራእይ ታየ (1-4)

      • “ይሖዋ ቅዱስ፣ ቅዱስ፣ ቅዱስ ነው” (3)

    • የኢሳይያስ ከንፈሮች ነጹ (5-7)

    • ኢሳይያስ ተልእኮ ተሰጠው (8-10)

      • “እነሆኝ! እኔን ላከኝ!” (8)

    • “ይሖዋ ሆይ፣ እስከ መቼ ነው?” (11-13)

  • 7

    • ለንጉሥ አካዝ የተላከ መልእክት (1-9)

      • ሸአርያሹብ (3)

    • አማኑኤልን በተመለከተ የተሰጠ ምልክት (10-17)

    • ከዳተኛ መሆን የሚያስከትለው መዘዝ (18-25)

  • 8

    • የአሦር ወረራ (1-8)

      • ማኸር-ሻላል-ሃሽ-ባዝ (1-4)

    • አትፍሩ፤ “አምላክ ከእኛ ጋር ነው” (9-17)

    • ኢሳይያስና ልጆቹ ምልክት ሆነው ያገለግላሉ (18)

    • አጋንንትን ከመጠየቅ ይልቅ ሕጉን ተመልከቱ (19-22)

  • 9

    • በገሊላ ምድር ላይ ታላቅ ብርሃን ወጣ (1-7)

      • “የሰላም መስፍን” ተወለደ (6,7)

    • በእስራኤል ላይ የተዘረጋው የአምላክ እጅ (8-21)

  • 10

    • በእስራኤል ላይ የተዘረጋው የአምላክ እጅ (1-4)

    • አሦር፣ የአምላክ የቁጣ በትር (5-11)

    • በአሦር ላይ የሚደርስ ቅጣት (12-19)

    • ከያዕቆብ ቤት የሚተርፉት ይመለሳሉ (20-27)

    • አምላክ በአሦር ላይ ይፈርዳል (28-34)

  • 11

    • የእሴይ ቀንበጥ የጽድቅ አገዛዝ (1-10)

      • ተኩላ ከበግ ጠቦት ጋር ይቀመጣል (6)

      • ምድር በይሖዋ እውቀት ትሞላለች (9)

    • የሕዝቡ ቀሪዎች ይመለሳሉ (11-16)

  • 12

    • የምስጋና መዝሙር (1-6)

      • ‘ያህ ይሖዋ ብርታቴ ነው’ (2)

  • 13

    • በባቢሎን ላይ የተላለፈ ፍርድ (1-22)

      • “የይሖዋ ቀን ቀርቧል” (6)

      • ሜዶናውያን ባቢሎንን ይገለብጣሉ (17)

      • ባቢሎን ከዚያ በኋላ የሚቀመጥባት አይኖርም (20)

  • 14

    • እስራኤላውያን በገዛ ምድራቸው ላይ ይሰፍራሉ (1, 2)

    • በባቢሎን ንጉሥ ላይ ትሳለቃለህ (3-23)

      • የሚያበራው ኮከብ ከሰማይ ወደቀ (12)

    • የይሖዋ እጅ አሦራዊውን ያደቃል (24-27)

    • በፍልስጤም ላይ የተላለፈ ፍርድ (28-32)

  • 15

    • በሞዓብ ላይ የተላለፈ ፍርድ (1-9)

  • 16

    • ለሞዓብ የተነገረው የፍርድ መልእክት ቀጣይ ክፍል (1-14)

  • 17

    • በደማስቆ ላይ የተላለፈ ፍርድ (1-11)

    • ይሖዋ ብሔራትን ይገሥጻቸዋል (12-14)

  • 18

    • ለኢትዮጵያ የተነገረ የማስጠንቀቂያ መልእክት (1-7)

  • 19

    • በግብፅ ላይ የተላለፈ ፍርድ (1-15)

    • ይሖዋ በግብፃውያን ዘንድ የታወቀ ይሆናል (16-25)

      • በግብፅ ምድር ለይሖዋ መሠዊያ ይሠራል (19)

  • 20

    • ለግብፅና ለኢትዮጵያ የተሰጠ የማስጠንቀቂያ ምልክት (1-6)

  • 21

    • በምድረ በዳው ባሕር ላይ የተላለፈ ፍርድ (1-10)

      • “በመጠበቂያው ግንብ ላይ ቆሜአለሁ” (8)

      • “ባቢሎን ወደቀች!” (9)

    • በዱማና በበረሃማው ሜዳ ላይ የተላለፈ ፍርድ (11-17)

      • “ጠባቂ ሆይ፣ ስለ ሌሊቱ ምን ትላለህ?” (11)

  • 22

    • ስለ ራእይ ሸለቆ የተነገረ የፍርድ መልእክት (1-14)

    • መጋቢው ሸብና በኤልያቄም ተተካ (15-25)

      • ምሳሌያዊው ማንጠልጠያ (23-25)

  • 23

    • ስለ ጢሮስ የተነገረ የፍርድ መልእክት (1-18)

  • 24

    • ይሖዋ አገሪቱን ወና ያደርጋታል (1-23)

      • ይሖዋ በጽዮን ነግሦአል (23)

  • 25

    • የአምላክ ሕዝብ የሚያገኘው የተትረፈረፈ በረከት (1-12)

      • ይሖዋ ጥሩ የወይን ጠጅ የሚቀርብበት ታላቅ ግብዣ ያዘጋጃል (6)

      • “ሞትን ለዘላለም ይውጣል” (8)

  • 26

    • በይሖዋ ስለ መታመንና ስለ መዳን የተዘመረ መዝሙር (1-21)

      • “ያህ ይሖዋ የዘላለም ዓለት ነው” (4)

      • የምድር ነዋሪዎች ስለ ጽድቅ ይማራሉ (9)

      • “ሙታንህ ሕያዋን ይሆናሉ” (19)

      • ወደ ውስጠኛው ክፍልህ ገብተህ ተሸሸግ (20)

  • 27

    • ይሖዋ ሌዋታንን ይገድለዋል (1)

    • በወይን እርሻ ለተመሰለችው እስራኤል የተዘመረ መዝሙር (2-13)

  • 28

    • የኤፍሬም ሰካራሞች ወዮላቸው! (1-6)

    • የይሁዳ ካህናትና ነቢያት ይንገዳገዳሉ (7-13)

    • “ከሞት ጋር ቃል ኪዳን ገብተናል” (14-22)

      • በጽዮን የተቀመጠ ክቡር የማዕዘን ድንጋይ (16)

      • ይሖዋ ያከናወነው እንግዳ የሆነ ተግባር (21)

    • የይሖዋን ተግሣጽ የሚያሳይ ምሳሌ (23-29)

  • 29

    • ለአርዔል ወዮላት! (1-16)

      • ‘በከንፈሩ ያከብረኛል’ (13)

    • መስማት የተሳናቸው ይሰማሉ፤ ዓይነ ስውራኑም ያያሉ (17-24)

  • 30

    • ግብፅ የምትሰጠው እርዳታ ዋጋ የለውም (1-7)

    • ሕዝቡ ትንቢታዊ መልእክቱን ንቀዋል (8-14)

    • “ተማምናችሁ በመኖር ብርቱ መሆናችሁን ታሳያላችሁ” (15-17)

    • ይሖዋ ለሕዝቡ ሞገስ ያሳያል (18-26)

      • ታላቅ አስተማሪ የሆነው ይሖዋ (20)

      • “መንገዱ ይህ ነው” (21)

    • ይሖዋ በአሦር ላይ ፍርዱን ያስፈጽማል (27-33)

  • 31

    • አስተማማኝ እርዳታ የሚገኘው ከሰው ሳይሆን ከአምላክ ነው (1-9)

      • የግብፅ ፈረሶች ሥጋ ናቸው (3)

  • 32

    • ንጉሥና ገዢዎች ለፍትሕ ይገዛሉ (1-8)

    • ደንታ ቢስ ሴቶች ማስጠንቀቂያ ተሰጣቸው (9-14)

    • መንፈስ ሲፈስ የሚገኝ በረከት (15-20)

  • 33

    • ጻድቃን የሚያገኙት ፍትሕና የሚጠብቃቸው ተስፋ (1-24)

      • ይሖዋ ዳኛ፣ ሕግ ሰጪና ንጉሥ ነው (22)

      • “ታምሜአለሁ” የሚል አይኖርም (24)

  • 34

    • ይሖዋ በብሔራት ላይ የሚወስደው የበቀል እርምጃ (1-4)

    • ኤዶም ትወድማለች (5-17)

  • 35

    • ምድር ገነት ትሆናለች (1-7)

      • ዓይነ ስውራን ያያሉ፤ መስማት የተሳናቸውም ይሰማሉ (5)

    • የተዋጁት የሚጓዙበት “የቅድስና ጎዳና” (8-10)

  • 36

    • ሰናክሬም ይሁዳን ወረረ (1-3)

    • ራብሻቁ በይሖዋ ላይ ተሳለቀ (4-22)

  • 37

    • ሕዝቅያስ በኢሳይያስ በኩል የአምላክን እርዳታ ጠየቀ (1-7)

    • ሰናክሬም በኢየሩሳሌም ላይ ዛተ (8-13)

    • የሕዝቅያስ ጸሎት (14-20)

    • ኢሳይያስ አምላክ የሰጠውን መልስ ተናገረ (21-35)

    • አንድ መልአክ 185,000 አሦራውያንን ገደለ (36-38)

  • 38

    • ሕዝቅያስ ከሕመሙ አገገመ (1-22)

      • የምስጋና መዝሙር (10-20)

  • 39

    • ከባቢሎን የመጡ መልእክተኞች (1-8)

  • 40

    • ለአምላክ ሕዝብ የተሰጠ ማጽናኛ (1-11)

      • በምድረ በዳ የተሰማ ድምፅ (3-5)

    • የአምላክ ታላቅነት (12-31)

      • “ብሔራት በገንቦ ውስጥ እንዳለች ጠብታ ናቸው” (15)

      • ‘አምላክ ክብ ከሆነችው ምድር በላይ ይኖራል’ (22)

      • ከዋክብትን ሁሉ በየስማቸው ይጠራቸዋል (26)

      • አምላክ ፈጽሞ አይደክምም (28)

      • ይሖዋን ተስፋ ማድረግ ኃይል ያድሳል (29-31)

  • 41

    • ከፀሐይ መውጫ የመጣ ድል አድራጊ (1-7)

    • እስራኤል የአምላክ አገልጋይ እንዲሆን ተመረጠ (8-20)

      • ‘ወዳጄ አብርሃም’ (8)

    • ለአማልክት የቀረበ ፈተና (21-29)

  • 42

    • የአምላክ አገልጋይ የተሰጠው ተልእኮ (1-9)

      • ‘ስሜ ይሖዋ ነው’ (8)

    • ለይሖዋ የቀረበ አዲስ የውዳሴ መዝሙር (10-17)

    • እስራኤል ዕውርና ደንቆሮ ነው (18-25)

  • 43

    • ይሖዋ ሕዝቡን መልሶ ሰበሰበ (1-7)

    • አማልክት የገጠማቸው ግድድር (8-13)

      • “እናንተ ምሥክሮቼ ናችሁ” (10, 12)

    • ከባቢሎን ነፃ መውጣት (14-21)

    • “ጉዳያችንን አቅርበን እንሟገት” (22-28)

  • 44

    • አምላክ የመረጠው ሕዝብ የሚያገኘው በረከት (1-5)

    • ከይሖዋ በቀር ሌላ አምላክ የለም (6-8)

    • ሰው ሠራሽ ጣዖታት ከንቱ ናቸው (9-20)

    • እስራኤልን የሚቤዠው ይሖዋ (21-23)

    • በቂሮስ አማካኝነት ቀድሞ ወደነበሩበት ሁኔታ ይመለሳሉ (24-28)

  • 45

    • ቂሮስ ባቢሎንን ድል እንዲያደርግ ተቀብቷል (1-8)

    • ሸክላ ከሠሪው ጋር ሙግት አይገጥምም (9-13)

    • ሌሎች ብሔራት ለእስራኤል እውቅና ይሰጣሉ (14-17)

    • የአምላክ የፍጥረት ሥራም ሆነ የሚናገረው ትንቢት አስተማማኝ ነው (18-25)

      • ምድር የተፈጠረችው መኖሪያ እንድትሆን ነው (18)

  • 46

    • በባቢሎን ጣዖታትና በእስራኤል አምላክ መካከል ያለው ልዩነት (1-13)

      • ይሖዋ ስለ ወደፊቱ ጊዜ አስቀድሞ ይናገራል (10)

      • ከፀሐይ መውጫ የሚመጣ አዳኝ አሞራ (11)

  • 47

    • የባቢሎን መውደቅ (1-15)

      • ኮከብ ቆጣሪዎች ተጋለጡ (13-15)

  • 48

    • እስራኤል ተወቀሰች፤ ደግሞም ጠራች (1-11)

    • ይሖዋ በባቢሎን ላይ እርምጃ ይወስዳል (12-16ሀ)

    • የአምላክ ትምህርት ጠቃሚ ነው (16ለ-19)

    • “ከባቢሎን ውጡ!” (20-22)

  • 49

    • ለይሖዋ አገልጋይ የተሰጠ ሥራ (1-12)

      • “ለብሔራት ብርሃን” (6)

    • ለእስራኤል የተነገረ ማጽናኛ (13-26)

  • 50

    • የእስራኤል ኃጢአት ያስከተለው ችግር (1-3)

    • የይሖዋ ታዛዥ አገልጋይ (4-11)

      • ከአምላክ የተማሩ ሰዎች አንደበትና ጆሮ (4)

  • 51

    • ጽዮን ተመልሳ እንደ ኤደን የአትክልት ስፍራ ትሆናለች (1-8)

    • ጽዮንን የሠራው ኃያል አምላክ የተናገረው ማጽናኛ (9-16)

    • የይሖዋ የቁጣ ጽዋ (17-23)

  • 52

    • “ጽዮን ሆይ፣ ተነሺ!” (1-12)

      • ምሥራች ይዘው የሚመጡ ያማሩ እግሮች (7)

      • የጽዮን ጠባቂዎች በአንድነት እልል ይላሉ (8)

      • የይሖዋን ዕቃ የሚሸከሙ ንጹሕ መሆን ይጠበቅባቸዋል (11)

    • የይሖዋ አገልጋይ ከፍ ከፍ ይላል (13-15)

      • ከሰው ልጆች ሁሉ ይልቅ ተጎሳቆለ (14)

  • 53

    • የይሖዋ አገልጋይ የደረሰበት ሥቃይ፣ አሟሟቱና የተቀበረበት ሁኔታ (1-12)

      • ሰዎች ናቁት፤ ደግሞም አገለሉት (3)

      • ሕመማችንንና ሥቃያችንን ተሸከመ (4)

      • “እንደ በግ ለመታረድ ተነዳ” (7)

      • የብዙ ሰዎችን ኃጢአት ተሸከመ (12)

  • 54

    • መሃን የሆነችው ጽዮን ብዙ ልጆች ትወልዳለች (1-17)

      • የጽዮን ባል የሆነው ይሖዋ (5)

      • የጽዮን ልጆች ከይሖዋ የተማሩ ይሆናሉ (13)

      • ጽዮንን ለማጥቃት የተሠራ መሣሪያ ይከሽፋል (17)

  • 55

    • በነፃ እንዲበሉና እንዲጠጡ የቀረበ ግብዣ (1-5)

    • ይሖዋንና አስተማማኝ የሆነውን ቃሉን ፈልጉ (6-13)

      • የአምላክ መንገድ ከሰው መንገድ ከፍ ያለ ነው (8, 9)

      • የአምላክ ቃል መፈጸሙ የተረጋገጠ ነው (10, 11)

  • 56

    • የባዕድ አገር ሰውና ጃንደረባ የሚያገኙት በረከት (1-8)

      • ለሰው ሁሉ የሚሆን የጸሎት ቤት (7)

    • ዕውር ጠባቂዎች፤ መናገር የማይችሉ ውሾች (9-12)

  • 57

    • ጻድቅ ሰውም ሆነ ታማኝ ሰዎች ይሞታሉ (1, 2)

    • እስራኤል የፈጸመችው መንፈሳዊ ምንዝር ተጋለጠ (3-13)

    • ለችግረኞች የተነገረ ማጽናኛ (14-21)

      • ክፉዎች የሚናወጥ ባሕር ናቸው (20)

      • “ክፉዎች ሰላም የላቸውም” (21)

  • 58

    • እውነተኛ ጾምና የይስሙላ ጾም (1-12)

    • ሰንበትን በማክበር መደሰት (13, 14)

  • 59

    • እስራኤል የፈጸመችው ኃጢአት ከአምላክ አራቃት (1-8)

    • የኃጢአት ኑዛዜ (9-15ሀ)

    • ይሖዋ ንስሐ ለገቡት ሲል ጣልቃ ገባ (15ለ-21)

  • 60

    • የይሖዋ ክብር በጽዮን ላይ ያበራል (1-22)

      • ‘ወደ ቤታቸው እንደሚተሙ ርግቦች’ (8)

      • በመዳብ ፋንታ ወርቅ (17)

      • ‘ጥቂት የሆነው ሺህ ይሆናል’ (22)

  • 61

    • “ምሥራች እንድናገር ቀብቶኛል” (1-11)

      • ‘ይሖዋ በጎ ፈቃድ የሚያሳይበት ዓመት’ (2)

      • “ትላልቅ የጽድቅ ዛፎች” (3)

      • የባዕድ አገር ሰዎች እርዳታ ያበረክታሉ (5)

      • “የይሖዋ ካህናት” (6)

  • 62

    • የጽዮን አዲስ ስም (1-12)

  • 63

    • ይሖዋ በብሔራት ላይ የሚወስደው የበቀል እርምጃ (1-6)

    • የይሖዋ ታማኝ ፍቅር (7-14)

    • የንስሐ ጸሎት (15-19)

  • 64

    • የንስሐ ጸሎት ቀጣይ ክፍል (1-12)

      • ይሖዋ ሠሪያችን ነው (8)

  • 65

    • ይሖዋ በጣዖት አምላኪዎች ላይ ያስተላለፈው ፍርድ (1-16)

      • የመልካም ዕድልና የዕጣ አማልክት (11)

      • “አገልጋዮቼ ይበላሉ” (13)

    • አዲስ ሰማያትና አዲስ ምድር (17-25)

      • ቤቶችን ይሠራሉ፤ ወይንንም ይተክላሉ (21)

      • በከንቱ አይለፉም (23)

  • 66

    • እውነተኛና ሐሰተኛ አምልኮ (1-6)

    • ጽዮንና ወንዶች ልጆቿ (7-17)

    • ሰዎች ለአምልኮ በኢየሩሳሌም ይሰበሰባሉ (18-24)