ኢሳይያስ 15:1-9

  • በሞዓብ ላይ የተላለፈ ፍርድ (1-9)

15  በሞዓብ ላይ የተላለፈ ፍርድ፦+ የሞዓብ ኤር+ በሌሊት ስለወደመችጸጥ ረጭ ብላለች። የሞዓብ ቂር+ በሌሊት ስለወደመችጸጥ ረጭ ብላለች።   ወደ ቤቱ፣* ወደ ዲቦን፣+ወደ ከፍታ ቦታዎቹም ለማልቀስ ወጥቷል። ሞዓብ ስለ ነቦና+ ስለ መደባ+ ዋይ ዋይ ይላል። ራስ ሁሉ ተመልጧል፤+ ጢምም ሁሉ ተላጭቷል።+   በጎዳናዎቹ ላይ ማቅ ለብሰው ይታያሉ። ሁሉም በጣሪያዎቻቸውና በአደባባዮቻቸው ላይ ዋይ ዋይ ይላሉ፤እያለቀሱም ይወርዳሉ።+   ሃሽቦንና ኤልዓሌ+ ያለቅሳሉ፤ድምፃቸው እስከ ያሃጽ+ ድረስ ተሰምቷል። ከዚህም የተነሳ የሞዓብ ተዋጊዎች ይጮኻሉ። እሱም* ይንቀጠቀጣል።   ልቤ ስለ ሞዓብ ያለቅሳል። የሚሸሹት የሞዓብ ሰዎች እስከ ዞአርና+ እስከ ኤግላት ሸሊሺያ+ ድረስ ተሰደዱ። እያለቀሱ የሉሂትን ዳገት ይወጣሉ፤በደረሰባቸው ድንገተኛ ጥፋት የተነሳ ወደ ሆሮናይም በሚወስደው መንገድ ላይ ሲሄዱ ይጮኻሉ።+   የኒምሪም ውኃዎች ደርቀዋልና፤ለምለሙ የግጦሽ መስክ ደርቋል፤ሣሩ ጠፍቷል፤ አንድም የለመለመ ነገር አይታይም።   በመሆኑም ካከማቹት ንብረት ውስጥ የተረፈውን እንዲሁም ሀብታቸውን ተሸክመውየአኻያ ዛፎች የሚገኙበትን ሸለቆ* ይሻገራሉ።   ጩኸታቸው እስከ ሞዓብ ወሰን ድረስ አስተጋብቷል።+ ዋይታቸው እስከ ኤግላይም፣እስከ በኤርዔሊም ድረስም ተሰምቷል።   የዲሞን ውኃዎች በደም ተሞልተዋልና፤በዲሞንም ላይ ተጨማሪ ነገሮች አመጣለሁ፦ በሚሸሹት ሞዓባውያንናበምድሪቱ ላይ በሚቀሩት ሰዎች ላይ አንበሶች እሰዳለሁ።+

የግርጌ ማስታወሻ

ወይም “ቤተ መቅደሱ።”
ወይም “ነፍሱም።”
ወይም “ደረቅ ወንዝ።”