ኢሳይያስ 18:1-7
-
ለኢትዮጵያ የተነገረ የማስጠንቀቂያ መልእክት (1-7)
18 በክንፋቸው ጥዝ የሚል ድምፅ የሚያሰሙ ጥቃቅን ነፍሳት ላሉባትበኢትዮጵያ ወንዞች አካባቢ ለምትገኝ ምድር ወዮላት!+
2 ይህች ምድር በባሕር ላይ፣በደንገል ጀልባ ውኃዎችን አቋርጠው የሚሄዱ መልእክተኞችን እንዲህ በማለት ትልካለች፦
“እናንተ ፈጣን መልእክተኞች፣ረጃጅም የሆኑና ለስላሳ ቆዳ ያላቸው ሰዎች ወደሚገኙበት ብሔር፣*ከቅርብም ሆነ ከሩቅ ወደሚፈራ ሕዝብ፣+ጥንካሬ ወዳለውና ድል አድራጊ ወደሆነው*እንዲሁም መሬቱ በወንዞች ተጠርጎ ወደተወሰደበት ብሔር ሂዱ።”
3 እናንተ በአገሪቱ የምትኖሩ ሁሉና እናንተ የምድር ነዋሪዎች ሁሉ፣በተራሮች ላይ እንደሚቆም ምልክት* ያለ ነገር ትመለከታላችሁ፤እንዲሁም ቀንደ መለከት ሲነፋ የሚሰማው ዓይነት ድምፅ ትሰማላችሁ።
4 ይሖዋ እንዲህ ብሎኛልና፦
“በቀን ብርሃን እንዳለ የሚያጥበረብር ሐሩር፣በመከርም ሙቀት እንዳለ የደመና ጠል፣ጸጥ ብዬ ተቀምጬ ጽኑ ሆኖ የተመሠረተውን ስፍራዬን* እመለከታለሁ።
5 ከመከር በፊት፣አበባው በሚረግፍበትና የወይን ፍሬው በሚበስልበት ጊዜቀንበጦቹ በማጭድ ይቆረጣሉና፤ሐረጎቹም ተቆርጠው ይወገዳሉ።
6 ሁሉም በተራሮች ላይ ላሉ አዳኝ አሞሮችናለምድር አራዊት ይተዋሉ።
አዳኝ አሞሮቹም እነሱን በመመገብ በጋውን ያሳልፋሉ፤በምድር ላይ ያሉ አራዊትም ሁሉ እነሱን በመመገብ የመከሩን ወቅት ያሳልፋሉ።
7 በዚያን ጊዜ ረጃጅም የሆኑና ለስላሳ ቆዳ ያላቸው ሰዎች የሚገኙበት ብሔር፣*ከቅርብም ሆነ ከሩቅ የሚፈራው ሕዝብ፣ጥንካሬ ያለው፣ ድል አድራጊ የሆነውና*መሬቱ በወንዞች ተጠርጎ የተወሰደበት ብሔርለሠራዊት ጌታ ለይሖዋ ስጦታ ያመጣል፤ስጦታውንም የሚያመጣው የሠራዊት ጌታ የይሖዋ ስም ወዳለበት ወደ ጽዮን ተራራ+ ነው።”