ኢሳይያስ 2:1-22

  • የይሖዋ ተራራ ከፍ ከፍ ይላል (1-5)

    • ሰይፋቸውን ማረሻ ያደርጋሉ (4)

  • በይሖዋ ቀን ትዕቢተኞች ይዋረዳሉ (6-22)

2  የአሞጽ ልጅ ኢሳይያስ ስለ ይሁዳና ስለ ኢየሩሳሌም ያየው ይህ ነው፦+   በዘመኑ መጨረሻ*የይሖዋ ቤት ተራራከተራሮች አናት በላይ ጸንቶ ይቆማል፤+ከኮረብቶችም በላይ ከፍ ከፍ ይላል፤ብሔራትም ሁሉ ወደዚያ ይጎርፋሉ።+   ብዙ ሕዝቦችም ሄደው እንዲህ ይላሉ፦ “ኑ፤ ወደ ይሖዋ ተራራ፣ወደ ያዕቆብ አምላክ ቤት እንውጣ።+ እሱ ስለ መንገዶቹ ያስተምረናል፤በጎዳናዎቹም እንሄዳለን።”+ ሕግ* ከጽዮን፣የይሖዋም ቃል ከኢየሩሳሌም ይወጣልና።+   እሱ በብሔራት መካከል ይፈርዳል፤ከብዙ ሕዝቦች ጋር በተያያዘም ሁሉንም ነገር ያቀናል።* እነሱ ሰይፋቸውን ማረሻ፣ጦራቸውንም ማጭድ ለማድረግ ይቀጠቅጣሉ።+ አንዱ ብሔር በሌላው ብሔር ላይ ሰይፍ አያነሳም፤ከእንግዲህ ወዲህ ጦርነት አይማሩም።+   እናንተ የያዕቆብ ቤት ሆይ፣ ኑ፤በይሖዋ ብርሃን እንሂድ።+   አንተ ሕዝብህን ይኸውም የያዕቆብን ቤት ትተሃል፤+ምክንያቱም እነሱ ከምሥራቅ በመጡ ነገሮች ተሞልተዋል፤እንደ ፍልስጤማውያን የአስማት ድርጊቶችን ይፈጽማሉ፤+በባዕድ አገር ሰዎች ልጆችም ተጥለቅልቀዋል።   ምድራቸው በብርና በወርቅ ተሞልታለች፤ሀብታቸውም ገደብ የለውም። ምድራቸው በፈረሶች ተሞልታለች፤ሠረገሎቻቸውም ስፍር ቁጥር የላቸውም።+   ምድራቸውም ከንቱ በሆኑ አማልክት ተጥለቅልቃለች።+ የገዛ እጃቸው ለሠራው፣የገዛ ጣታቸውም ላበጀው ነገር ይሰግዳሉ።   በመሆኑም ሰው አንገቱን ይደፋል፤ ኀፍረትም ይከናነባል፤አንተም ይቅር ልትላቸው አትችልም። 10  ይሖዋ አስፈሪ ከመሆኑ የተነሳናከታላቅ ግርማው የተነሳበዓለት ውስጥ ተደበቅ፤ በመሬትም ውስጥ ተሸሸግ።+ 11  ትዕቢተኛ ዓይኖች ይዋረዳሉ፤እብሪተኛ ሰዎችም አንገታቸውን ይደፋሉ።* በዚያም ቀን ይሖዋ ብቻ ከፍ ከፍ ይደረጋል። 12  ይህ ቀን የሠራዊት ጌታ የይሖዋ ነውና።+ ቀኑ ትዕቢተኛና ኩሩ በሆነው ሁሉ ላይ፣ከፍ ባለውም ሆነ ዝቅ ባለው ሁሉ ላይ ይመጣል፤+ 13  ታላላቅ በሆኑትና ከፍ ከፍ ባሉት አርዘ ሊባኖሶች ሁሉ ላይእንዲሁም በባሳን የባሉጥ ዛፎች ሁሉ ላይ፣ 14  ታላላቅ በሆኑት ተራሮች ሁሉናበረጃጅም ኮረብቶች ሁሉ ላይ፣ 15  ረጅም በሆነ ማማ ሁሉና ጠንካራ በሆነ ግንብ ሁሉ ላይ፣ 16  በተርሴስ መርከቦች+ ሁሉናበሚያማምሩ ጀልባዎች ሁሉ ላይ ይደርሳል። 17  ትዕቢተኛ ሰው ይዋረዳል፤እብሪተኞችም አንገታቸውን ይደፋሉ።* በዚያም ቀን ይሖዋ ብቻ ከፍ ከፍ ይደረጋል። 18  ከንቱ የሆኑት አማልክት ሙሉ በሙሉ ይወገዳሉ።+ 19  ይሖዋ ምድርን በሽብር ለማንቀጥቀጥ በሚነሳበት ጊዜ፣አስፈሪ ከመሆኑ የተነሳናከታላቅ ግርማው የተነሳ+ሰዎች በዓለት ዋሻዎችናበጉድጓዶች ውስጥ* ይደበቃሉ።+ 20  በዚያ ቀን፣ ሰዎች በፊታቸው ይሰግዱ ዘንድለራሳቸው የሠሯቸውን ከንቱ የሆኑ የብርና የወርቅ አማልክትለአይጦችና* ለሌሊት ወፎች ይወረውራሉ፤+ 21  ይሖዋ ምድርን በሽብር ለማንቀጥቀጥ በሚነሳበት ጊዜ፣አስፈሪ ከመሆኑ የተነሳናከታላቅ ግርማው የተነሳበዓለት ዋሻዎችናበቋጥኝ ስንጥቆች ውስጥ ይደበቃሉ። 22  ለራሳችሁ ስትሉ፣ከአፍንጫው እንደሚወጣ እስትንፋስ በሆነ ሰው* አትታመኑ። ለመሆኑ እሱ ያን ያህል ቦታ እንዲሰጠው የሚያደርግ ምን ነገር አለ?

የግርጌ ማስታወሻ

ወይም “በመጨረሻዎቹ ቀኖች።”
ወይም “መመሪያ፤ ትምህርት።”
ወይም “ያስተካክላል።”
ወይም “ኀፍረት ይከናነባሉ።”
ወይም “ኀፍረት ይከናነባሉ።”
ወይም “በመሬት ጉድጓዶች ውስጥ።”
በልተው የማይጠግቡ ትናንሽ አጥቢ እንስሳት።
ወይም “እስትንፋሱ በአፍንጫው ላይ ባለች ሰው።”