ኢሳይያስ 25:1-12

  • የአምላክ ሕዝብ የሚያገኘው የተትረፈረፈ በረከት (1-12)

    • ይሖዋ ጥሩ የወይን ጠጅ የሚቀርብበት ታላቅ ግብዣ ያዘጋጃል (6)

    • “ሞትን ለዘላለም ይውጣል” (8)

25  ይሖዋ ሆይ፣ አንተ አምላኬ ነህ። ድንቅ ነገሮችን ስላደረግክና+ከጥንት ዘመን ጀምሮ ያሰብካቸውን ነገሮች*+በታማኝነትና+ እምነት በሚጣልበት መንገድ ስለፈጸምክከፍ ከፍ አደርግሃለሁ፤ ስምህንም አወድሳለሁ።   ከተማዋን የድንጋይ ቁልል፣የተመሸገችውንም ከተማ የፍርስራሽ ክምር አድርገሃልና። የባዕዳኑ ማማ፣ ከተማ መሆኑ አብቅቶለታል፤ከተማዋ በምንም ዓይነት ዳግመኛ አትገነባም።   ከዚህም የተነሳ ኃያል የሆነ ሕዝብ ያከብርሃል፤የጨቋኝ ብሔራት ከተማም ትፈራሃለች።+   ለችግረኛው ምሽግ ሆነሃልና፤ለድሃውም ከደረሰበት ጭንቀት መሸሸጊያ፣+ከውሽንፍርም መጠለያ፣ከፀሐይ ንዳድም ጥላ ሆነሃል።+ የጨቋኞች ቁጣ ከግንብ ጋር እንደሚላተም ውሽንፍር በሚሆንበት ጊዜ ጥበቃ ታደርጋለህ፤   ውኃ በተጠማ ምድር እንዳለ ሙቀትየባዕዳንን ሁከት ጸጥ ታደርጋለህ። በደመና ጥላ እንደሚበርድ ሙቀት፣የጨቋኞችም ዝማሬ ጸጥ ረጭ ይላል።   የሠራዊት ጌታ ይሖዋ በዚህ ተራራ+ ላይ ለሕዝቦች ሁሉምርጥ ምግቦች* የሚገኙበት ታላቅ ግብዣ ያዘጋጃል፤+ያረጀ የወይን ጠጅ ግብዣ፣መቅኒ የሞላባቸው ምርጥ ምግቦችእንዲሁም የተጣራና ጥሩ የወይን ጠጅ የሚቀርቡበት ታላቅ ግብዣ ያደርጋል።   በዚህ ተራራ ላይ ሕዝቦችን ሁሉ የሸፈነውን ከፈንእንዲሁም ብሔራትን ሁሉ ተብትቦ የያዘውን መሸፈኛ ያስወግዳል።*   ሞትን ለዘላለም ይውጣል፤*+ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ከፊት ሁሉ እንባን ያብሳል።*+ በሕዝቡ ላይ የደረሰውን ነቀፋ ከመላው ምድር ያስወግዳል፤ይሖዋ ራሱ ይህን ተናግሯልና።   በዚያም ቀን እንዲህ ይላሉ፦ “እነሆ፣ አምላካችን ይህ ነው!+ እሱን ተስፋ አድርገናል፤+እሱም ያድነናል።+ ይሖዋ ይህ ነው! እሱን ተስፋ አድርገናል። በእሱ ማዳን ደስ ይበለን፤ ሐሴትም እናድርግ።”+ 10  የይሖዋ እጅ በዚህ ተራራ ላይ ያርፋልና፤+ጭድ በፍግ ክምር ላይ እንደሚረገጥሞዓብም በስፍራው እንዲሁ ይረገጣል።+ 11  አንድ ዋናተኛ በሚዋኝበት ጊዜ በእጆቹ ውኃውን እንደሚመታእሱም እጁን ዘርግቶ ሞዓብን ይመታዋል፤በእጆቹ በጥበብ በመምታትትዕቢቱን ያበርድለታል።+ 12  የተመሸገውን ከተማከረጃጅም የመከላከያ ግንቦችህ ጋር ያፈርሳል፤ምድር ላይ ጥሎ ከአፈር ይደባልቀዋል።

የግርጌ ማስታወሻ

ወይም “ምክሮች።”
ቃል በቃል “ቅባት የሞላባቸው ምግቦች።”
ቃል በቃል “ይውጣል።”
ወይም “ያስወግዳል።”
ወይም “ይጠርጋል።”