ኢሳይያስ 26:1-21

  • በይሖዋ ስለ መታመንና ስለ መዳን የተዘመረ መዝሙር (1-21)

    • “ያህ ይሖዋ የዘላለም ዓለት ነው” (4)

    • የምድር ነዋሪዎች ስለ ጽድቅ ይማራሉ (9)

    • “ሙታንህ ሕያዋን ይሆናሉ” (19)

    • ወደ ውስጠኛው ክፍልህ ገብተህ ተሸሸግ (20)

26  በዚያ ቀን በይሁዳ ምድር ይህ መዝሙር ይዘመራል፦+ “ጠንካራ ከተማ አለችን።+ እሱ መዳንን፣ ቅጥሯና መከላከያ ግንቧ ያደርጋል።+   ጻድቅ ብሔር ይኸውም በታማኝነት የሚመላለሰው ብሔርእንዲገባ በሮቹን ክፈቱ።+   ሙሉ በሙሉ በአንተ የሚመኩትን* ትጠብቃለህ፤በአንተ ስለሚታመኑ+ዘላቂ ሰላም ትሰጣቸዋለህ።+   በይሖዋ ለዘላለም ታመኑ፤+ያህ* ይሖዋ የዘላለም ዓለት ነውና።+   ከፍ ባለ ቦታ የሚኖሩትን፣ ከፍ ያለችውንም ከተማ ዝቅ አድርጓልና።ያዋርዳታል፤ ወደ ምድር ይጥላታል፤ከአፈርም ይደባልቃታል።   የጎስቋላ ሰው እግር፣የችግረኞችም ኮቴ ይረግጣታል።”   የጻድቅ ሰው መንገድ ቀና* ነው። አንተ ቅን ስለሆንክየጻድቁን መንገድ ደልዳላ ታደርጋለህ።   ይሖዋ ሆይ፣ የፍትሕ ጎዳናህን ስንከተል፣ተስፋ የምናደርገው አንተን ነው። ስምህና መታሰቢያህ የልባችን* ምኞት ነው።*   ሁለንተናዬ* በሌሊት አንተን ለማግኘት ይጓጓል፤አዎ፣ መንፈሴ አንተን በጥብቅ ትፈልጋለች፤+በምድር ላይ በምትፈርድበት ጊዜየምድሪቱ ነዋሪዎች ስለ ጽድቅ+ ይማራሉና። 10  ክፉ ሰው ቸርነት ቢደረግለት እንኳፈጽሞ ጽድቅን አይማርም።+ በቅንነት* ምድር እንኳ ክፋት ይሠራል፤+የይሖዋንም ግርማ አያይም።+ 11  ይሖዋ ሆይ፣ እጅህ ከፍ ብሏል፤ እነሱ ግን አላዩትም።+ ለሕዝብህ ያለህን ቅንዓት በምታሳይበት ጊዜ ያያሉ፤ ለኀፍረትም ይዳረጋሉ። አዎ፣ ለጠላቶችህ የተዘጋጀው እሳት ይበላቸዋል። 12  ይሖዋ ሆይ፣ አንተ ሰላም ትሰጠናለህ፤+ምክንያቱም የሠራነውን ነገር ሁሉያከናወንክልን አንተ ነህ። 13  ይሖዋ አምላካችን ሆይ፣ ከአንተ ሌላ፣ ሌሎች ጌቶች ገዝተውናል፤+እኛ ግን የአንተን ስም ብቻ እንጠራለን።+ 14  እነሱ ሞተዋል፤ በሕይወትም አይኖሩም። በሞት ተረተዋል፤ አይነሱም።+ ታጠፋቸውና ስማቸው ጨርሶ እንዳይነሳ ታደርግ ዘንድትኩረትህን ወደ እነሱ አዙረሃልና። 15  ሕዝቡን አበዛህ፤ ይሖዋ ሆይ፣ሕዝቡን አበዛህ፤ራስህን አስከበርክ።+ የምድሪቱን ወሰን ሁሉ እጅግ አሰፋህ።+ 16  ይሖዋ ሆይ፣ በተጨነቁ ጊዜ አንተን ፈለጉ፤በገሠጽካቸው ጊዜ በሹክሹክታ ድምፅ በመጸለይ ልባቸውን አፈሰሱ።+ 17  ይሖዋ ሆይ፣ ነፍሰ ጡር ሴት ልትወልድ ስትልምጥ እንደሚይዛትና በምጥ ጣር እንደምትጮኽ ሁሉእኛም በአንተ የተነሳ እንዲሁ ሆነናል። 18  አርግዘን ነበር፤ ደግሞም አምጠን ነበር፤ይሁንና ነፋስን የወለድን ያህል ነበር። ለምድሪቱ መዳን አላስገኘንምእንዲሁም በምድሪቱ ላይ እንዲኖር የተወለደ አንድም ልጅ የለም። 19  “ሙታንህ ሕያዋን ይሆናሉ። የእኔ አስከሬኖች ይነሳሉ።+ እናንተ በአፈር ውስጥ የምትኖሩ፣+ተነሱ፤ በደስታም እልል በሉ! ጠልህ እንደ ማለዳ ጠል ነውና፤*ምድርም በሞት የተረቱት ዳግም ሕይወት እንዲያገኙ ታደርጋለች።* 20  ሕዝቤ ሆይ፣ ሂድ ወደ ውስጠኛው ክፍልህ ግባ፤በርህንም ከኋላህ ዝጋ።+ ቁጣው* እስኪያልፍ ድረስለጥቂት ጊዜ ተሸሸግ።+ 21  እነሆ፣ ይሖዋ የምድሪቱ ነዋሪ የፈጸመውን በደል ለመፋረድከመኖሪያ ቦታው ይመጣልና፤ምድሪቱም በላይዋ የፈሰሰውን ደም ትገልጣለች፤በላይዋም የተገደሉትን ከዚህ በኋላ አትደብቅም።”

የግርጌ ማስታወሻ

“የማይናወጥ ልብ ያላቸውን” ማለትም ሊሆን ይችላል።
“ያህ” የይሖዋ ስም አጭር መጠሪያ ነው።
ወይም “ደልዳላ።”
ወይም “የነፍሳችን።”
አምላክም ሆነ ስሙ እንዲታወስና እንዲታወቅ እንደሚጓጉ ያሳያል።
ወይም “ነፍሴ።”
ወይም “በጽድቅ።”
“እንደ ዕፀዋት (ልት) ጠል ነውና” ማለትም ሊሆን ይችላል።
ወይም “በሞት የተረቱትን ትወልዳለች።”
ወይም “ውግዘቱ።”