ኢሳይያስ 27:1-13

  • ይሖዋ ሌዋታንን ይገድለዋል (1)

  • በወይን እርሻ ለተመሰለችው እስራኤል የተዘመረ መዝሙር (2-13)

27  በዚያን ቀን ይሖዋ፣ በፍጥነት እየተሳበ የሚሄደውን እባብ ሌዋታንን፣*ደግሞም እየተጥመለመለ የሚጓዘውን እባብ ሌዋታንንትልቅ፣ ኃይለኛና ምሕረት የለሽ በሆነው ሰይፉ ይቀጣዋል፤+በባሕር ውስጥ ያለውንም ግዙፍ ፍጥረት ይገድለዋል።   በዚያ ቀን ለእሷ* እንዲህ ብላችሁ ዘምሩ፦ “የሚፈላ የወይን ጠጅ የሚመረትባት የወይን እርሻ!+   እኔ ይሖዋ እጠብቃታለሁ።+ በየጊዜው ውኃ አጠጣታለሁ።+ ማንም ጉዳት እንዳያደርስባትሌት ተቀን እጠብቃታለሁ።+   ከእንግዲህ አልቆጣትም።+ በውጊያው ላይ ቁጥቋጦና አረም ይዞ የሚገጥመኝ ማን ነው? ሁሉንም በአንድ ላይ እረግጣቸዋለሁ፤ በእሳትም አቃጥላቸዋለሁ።   አለዚያ ምሽጌን የሙጥኝ ይበል። ከእኔ ጋር ሰላም ይፍጠር፤አዎ፣ ከእኔ ጋር ሰላም ይፍጠር።”   በመጪዎቹ ቀናት ያዕቆብ ሥር ይሰዳል፤እስራኤል ያብባል እንዲሁም ይለመልማል፤+ምድሩንም በምርት ይሞሉታል።+   እሱ አሁን በተመታበት ሁኔታ መመታቱ ተገቢ ነው? ወይስ የተገደሉበት ሰዎች በተፈጁበት መንገድ መገደሉ አስፈላጊ ነው?   እሷን በምትልካት ጊዜ በአስደንጋጭ ጩኸት ትፋለማታለህ። የምሥራቅ ነፋስ በሚነፍስበት ቀን በኃይለኛ አውሎ ነፋሱ ያስወግዳታል።+   በመሆኑም የያዕቆብ በደል በዚህ መንገድ ይሰረይለታል፤+ኃጢአቱ በሚወገድበት ጊዜ ፍሬው በሙሉ ይህ ይሆናል፦ የመሠዊያ ድንጋዮቹን ሁሉእንደደቀቀ የኖራ ድንጋይ ያደርጋል፤የማምለኪያ ግንዶቹም* ሆኑ የዕጣን ማጨሻዎቹ አይተርፉም።+ 10  የተመሸገችው ከተማ ትተዋለችና፤የግጦሽ መሬቱም ወና ይሆናል፤ እንደ ምድረ በዳም የተተወ ይሆናል።+ በዚያ ጥጃ ይግጣል፤ ይተኛልም፤ቅርንጫፎቿንም ይበላል።+ 11  ቀንበጦቿ በሚደርቁበት ጊዜሴቶች መጥተው ይሰብሯቸዋል፤ከዚያም ማገዶ ያደርጓቸዋል። ይህ ሕዝብ ማስተዋል ይጎድለዋልና።+ በዚህም ምክንያት ፈጣሪያቸው ምንም ምሕረት አያደርግላቸውም፤ሠሪያቸውም ምንም ዓይነት ሞገስ አያሳያቸውም።+ 12  በዚያም ቀን የእስራኤል ሕዝብ ሆይ፣ ሰው ዛፍ ላይ ያሉ ፍሬዎችን አርግፎ አንድ በአንድ እንደሚለቅም ሁሉ፣ ይሖዋም ከታላቁ ወንዝ* አንስቶ እስከ ግብፅ ደረቅ ወንዝ*+ ድረስ ባለው ቦታ ሁሉ የተበተናችሁትን ይሰበስባችኋል።+ 13  በዚያም ቀን ትልቅ ቀንደ መለከት ይነፋል፤+ በአሦር ምድር+ የጠፉትና በግብፅ ምድር+ የተበተኑት መጥተው በኢየሩሳሌም በሚገኘው ቅዱስ ተራራ ላይ ለይሖዋ ይሰግዳሉ።+

የግርጌ ማስታወሻ

እዚህ ላይ በአንስታይ ፆታ የተገለጸችውና በወይን እርሻ የተመሰለችው እስራኤል ልትሆን ትችላለች።
ኤፍራጥስን ያመለክታል።