ኢሳይያስ 3:1-26
3 እነሆ፣ እውነተኛው ጌታ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋኢየሩሳሌምና ይሁዳ ማንኛውም ዓይነት ድጋፍና አቅርቦትይኸውም የምግብና የውኃ አቅርቦት ሁሉ እንዲቋረጥባቸው ያደርጋል፤+
2 ኃያሉን ሰውና ተዋጊውን፣ዳኛውንና ነቢዩን፣+ ሟርተኛውንና ሽማግሌውን፣
3 የሃምሳ አለቃውን፣+ ባለሥልጣኑንና አማካሪውን፣በአስማት የተካነውንና በድግምት የላቀ ችሎታ ያለውን ያስወግዳል።+
4 በእነሱ ላይ ልጆችን መኳንንት አድርጌ እሾማለሁ፤ያልሰከነ* ሰውም ይገዛቸዋል።
5 ሕዝቡ አንዱ ሌላውን፣እያንዳንዱም ባልንጀራውን ይጨቁናል።+
ልጅ በሽማግሌ ላይ ጥቃት ይሰነዝራል፤ተራው ሰውም የተከበረውን ይዳፈራል።+
6 እያንዳንዱ ሰው በአባቱ ቤት የሚኖረውን ወንድሙን ይዞ
“አንተ ካባ አለህ፤ ስለዚህ በእኛ ላይ አዛዥ ሁን።
ይህን የፍርስራሽ ክምር ግዛ” ይለዋል።
7 እሱ ግን በዚያ ቀን እንዲህ ሲል ይቃወማል፦
“እኔ ቁስላችሁን አላክምም፤*በቤቴ ምግብም ሆነ ልብስ የለም።
በሕዝቡ ላይ አዛዥ አድርጋችሁ አትሹሙኝ።”
8 ኢየሩሳሌም ተሰናክላለችና፤ይሁዳም ወድቃለች፤ምክንያቱም እነሱ በአንደበታቸውም ሆነ በሥራቸው ይሖዋን ይቃወማሉ፤በክብራማው አምላክ ፊት* አሻፈረን ይላሉ።+
9 የፊታቸው ገጽታ ይመሠክርባቸዋል፤ደግሞም እንደ ሰዶም+ ኃጢአታቸውን በይፋ ይናገራሉ፤ኃጢአታቸውን ለመደበቅ አይሞክሩም።
በራሳቸው ላይ ጥፋት ስለሚያመጡ ወዮላቸው!*
10 ለጻድቃን መልካም እንደሚሆንላቸው ንገሯቸው፤ለሥራቸው ወሮታ ይከፈላቸዋል።*+
11 ለክፉ ሰው ወዮለት!
ጥፋት ይደርስበታል፤በሌሎች ላይ ሲያደርግ የነበረው በራሱ ላይ ይደርሳልና!
12 የሕዝቤ አሠሪዎች ጨቋኞች ናቸው፤ሴቶችም ይገዟቸዋል።
ሕዝቤ ሆይ፣ የሚመሯችሁ ሰዎች እንድትባዝኑናበየትኛው መንገድ እንደምትሄዱ ግራ እንድትጋቡ እያደረጓችሁ ነው።+
13 ይሖዋ ለመክሰስ ተሰይሟል፤በሕዝቦች ላይ ብያኔውን ለማሰማት ተነስቷል።
14 ይሖዋ የሕዝቡን ሽማግሌዎችና አለቆች ይፋረዳል።
“የወይኑን እርሻ አቃጥላችኋል፤ከድሃው የዘረፋችሁት ንብረትም በቤታችሁ ይገኛል።+
15 ሕዝቤን የምታደቁት፣ የድሆችንም ፊት መሬት ላይ የምትፈጩትእንዴት ብትዳፈሩ ነው?”+ ይላል ሉዓላዊው ጌታ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ።
16 ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “የጽዮን ሴቶች ልጆች ትዕቢተኛ ስለሆኑ፣ራሳቸውን ቀና አድርገው* ስለሚራመዱ፣በዓይናቸው እየተጣቀሱና እየተውረገረጉ በመሄድእግራቸው ላይ ያደረጉትን አልቦ ስለሚያቃጭሉ፣
17 ይሖዋ የጽዮንን ሴቶች አናት በቁስል ይመታል፤ደግሞም ይሖዋ ግንባራቸውን ይገልጣል።+
18 በዚያ ቀን ይሖዋ ጌጦቻቸውን ሁሉ ይነጥቃል፦አልቦውን፣ የፀጉር ጌጡን፣ የጨረቃ ቅርጽ ያለውን ጌጥ፣+
19 የጆሮ ጉትቻውን፣* አምባሩን፣ መከናነቢያውን፣
20 የራስ መሸፈኛውን፣ የሰንሰለት አልቦውን፣ ጌጠኛውን መቀነት፣*የሽቶ ዕቃውን፣* ክታቡን፣
21 የጣት ቀለበቱን፣ የአፍንጫ ቀለበቱን፣
22 የክት ልብሱን፣ መደረቢያውን፣ ካባውን፣ የእጅ ቦርሳውን፣
23 የእጅ መስተዋቱን፣+ የበፍታ ልብሶቹን፣*ጥምጥሙንና መከናነቢያውን ይወስድባቸዋል።
24 በበለሳን ዘይት+ መዓዛ ፋንታ የጠነባ ሽታ፣በመታጠቂያ ፋንታ ገመድ፣አምሮ በተሠራ ፀጉር ፋንታ መላጣነት፣+ባማረ ልብስ ፋንታ ማቅ፣+በውበትም ፋንታ ጠባሳ* ይሆናል።
25 ወንዶችሽ በሰይፍ፣ኃያላኖችሽም በውጊያ ይወድቃሉ።+
26 የከተማዋም መግቢያዎች ያዝናሉ፣ ያለቅሳሉም፤+እሷም ባዶዋን ቀርታ በሐዘን መሬት ላይ ትቀመጣለች።”+