ኢሳይያስ 30:1-33
30 “ግትር ለሆኑ ልጆች ወዮላቸው”+ ይላል ይሖዋ፤“በኃጢአት ላይ ኃጢአት ለመጨመርየእኔን ሳይሆን የራሳቸውን ዕቅድ ይፈጽማሉ፤+ደግሞም ኅብረት ይፈጥራሉ፤* ይህን የሚያደርጉት ግን በመንፈሴ አይደለም።
2 በፈርዖን ጥበቃ ሥር* ለመሸሸግናበግብፅ ጥላ ሥር ለመጠለልእኔን ሳያማክሩ*+ ወደ ግብፅ ይወርዳሉ!+
3 ይሁንና ፈርዖን የሚያደርግላችሁ ጥበቃ ለኀፍረት፣በግብፅ ጥላ ሥር መጠለልም ለውርደት ይዳርጋችኋል።+
4 መኳንንቱ በጾዓን+ ናቸውና፤መልእክተኞቹም ሃኔስ ደርሰዋል።
5 ምንም ሊጠቅማቸው በማይችል፣እርዳታ በማይሰጥና ጥቅም በማያስገኝ፣ይልቁንም ለውርደትና ለነቀፋ በሚዳርግ ሕዝብሁሉም ኀፍረት ይከናነባሉ።”+
6 በደቡብ እንስሳት ላይ የተላለፈ ፍርድ፦
አንበሳ፣ አዎ የሚያገሳ አንበሳ ባለበት፣እፉኝት እንዲሁም የሚበርና የሚያቃጥል እባብ* በሚገኙበት፣አስጨናቂና አስቸጋሪ ሁኔታዎች በሞሉበት ምድርሀብታቸውን በአህያ ላይ፣ቁሳቁሳቸውንም በግመል ሻኛ ላይ ጭነው ይሄዳሉ።
ሆኖም እነዚህ ነገሮች ለሕዝቡ ምንም ጥቅም አያስገኙለትም።
7 ግብፅ የምትሰጠው እርዳታ ምንም እርባና የለውምና።+
ስለዚህ እሷን “ረዓብ፣+ ሥራ ፈታ የምትጎለት” ብዬ ጠርቻታለሁ።
8 “በል ሂድ፤ ለመጪዎቹ ዘመናት፣ቋሚ ምሥክር እንዲሆንእነሱ ባሉበት በጽላት ላይ ጻፈው፤በመጽሐፍም ላይ ክተበው።+
9 እነሱ ዓመፀኛ ሕዝብ፣+ አታላይ ልጆችና+የይሖዋን ሕግ* ለመስማት እንቢተኛ የሆኑ ልጆች ናቸውና።+
10 ባለ ራእዮችን ‘ከእንግዲህ ራእይ አትዩ’ ይላሉ፤
ነቢያትንም እንዲህ ይላሉ፦ ‘እውነተኛ ራእይ አትንገሩን።+
የሚጥም* ነገር ንገሩን፤ አሳሳች የሆነ ሕልም አልሙልን።+
11 ከመንገዱ ዞር በሉ፤ ጎዳናውንም ልቀቁ።
የእስራኤልን ቅዱስ በፊታችን አታድርጉ።’”+
12 ስለዚህ የእስራኤል ቅዱስ እንዲህ ይላል፦
“ይህን ቃል ስለናቃችሁ፣+በማጭበርበርና በማታለል ስለታመናችሁ፣በዚያም ላይ ስለተደገፋችሁ፣+
13 ይህ በደል እንደተሰነጠቀ ቅጥር፣ሊወድቅ እንደተቃረበ ያዘመመ ረጅም ቅጥር ይሆንባችኋል።
ሳይታሰብ በድንገት ይፈርሳል።
14 ሸክላ ሠሪ እንደሠራው ትልቅ እንስራ ይሰባበራል፤እንክትክቱ ከመውጣቱ የተነሳ ከምድጃ ፍም ለመውሰድወይም ከረግረጋማ ቦታ* ውኃ ለመጨለፍ የሚያስችልአንድም ገል አይገኝም።”
15 የእስራኤል ቅዱስ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦
“ወደ እኔ በመመለስና በማረፍ ትድናላችሁ፤ሳትረበሹ፣ ተማምናችሁ በመኖር ብርቱ መሆናችሁን ታሳያላችሁ።”+
እናንተ ግን ፈቃደኞች አልሆናችሁም።+
16 ይልቁንም “አይሆንም፣ በፈረሶች እንሸሻለን!” አላችሁ።
ደግሞም ትሸሻላችሁ።
“በፈጣን ፈረሶችም እንጋልባለን!” አላችሁ።+
ስለሆነም የሚያሳድዷችሁ ሰዎች ፈጣኖች ይሆናሉ።+
17 አንድ ሰው ከሚሰነዝረው ዛቻ የተነሳ ሺዎች ይሸበራሉ፤+በተራራ አናት ላይ እንደተተከለ ምሰሶናበኮረብታ ላይ እንደቆመ ለምልክት የሚያገለግል ግንድ ሆናችሁ እስክትቀሩ ድረስ፣አምስት ሰዎች ከሚሰነዝሩት ዛቻ የተነሳ ትሸሻላችሁ።+
18 ይሁንና ይሖዋ ሞገስ ሊያሳያችሁ በትዕግሥት* ይጠባበቃል፤+ምሕረት ሊያሳያችሁም ይነሳል።+
ይሖዋ የፍትሕ አምላክ ነውና።+
እሱን በተስፋ* የሚጠባበቁ ሁሉ ደስተኞች ናቸው።+
19 ሕዝቡ በጽዮን ይኸውም በኢየሩሳሌም በሚኖርበት ጊዜ+ ፈጽሞ አታለቅሱም።+ እርዳታ ለማግኘት በምትጮኹበት ጊዜ በእርግጥ ሞገስ ያሳያችኋል፤ ጩኸታችሁን እንደሰማም ይመልስላችኋል።+
20 ይሖዋ የጭንቀትን ምግብና የጭቆናን ውኃ ቢሰጥህም+ እንኳ ታላቁ አስተማሪህ ከእንግዲህ ራሱን አይሰውርም፤ በገዛ ዓይኖችህም ታላቁን አስተማሪህን+ ታያለህ።
21 ወደ ቀኝ ወይም ወደ ግራ ዞር ብትል ጆሮህ ከኋላህ “መንገዱ ይህ ነው።+ በእሱ ሂድ” የሚል ድምፅ ይሰማል።+
22 የተቀረጹ ምስሎችህ የተለበጡበትን ብርና ከብረት የተሠሩ ሐውልቶችህ*+ የተለበጡበትን ወርቅ ታረክሳለህ። እንደ ወር አበባ ጨርቅ “ከዚህ ጥፉ!”* በማለት አሽቀንጥረህ ትጥላቸዋለህ።+
23 እሱም መሬት ላይ ለምትዘራው ዘር ዝናብ ይሰጥሃል፤+ ምድሪቱም የምታፈራው እህል የተትረፈረፈና ምርጥ* ይሆናል።+ በዚያም ቀን ከብቶችህ ሰፊ በሆነ የግጦሽ መስክ ይሰማራሉ።+
24 መሬቱንም የሚያርሱ ከብቶችና አህዮች በእንቧጮ* የተቀመመ እንዲሁም በላይዳና በመንሽ የተለየ ገፈራ ይበላሉ።
25 ብዙ እልቂት በሚደርስበትና ግንቦች በሚፈርሱበት ቀን፣ በረጅም ተራራና ከፍ ባለ ኮረብታ ሁሉ ላይ ጅረቶች ይፈስሳሉ፤+ የውኃ መውረጃ ቦዮችም ይኖራሉ።
26 የሙሉ ጨረቃ ብርሃንም እንደ ፀሐይ ብርሃን ይሆናል፤ ይሖዋ የሕዝቡን ስብራት* በሚጠግንበትና+ በእሱ ምት የተነሳ የደረሰባቸውን ከባድ ቁስል በሚፈውስበት ቀን+ የፀሐይ ብርሃን፣ እንደ ሰባት ቀን ብርሃን ሰባት እጥፍ ይደምቃል።+
27 እነሆ፣ የይሖዋ ስም በቁጣው እየነደደጥቅጥቅ ካለ ደመና ጋር ከሩቅ ይመጣል።
ከንፈሮቹ በቁጣ ተሞልተዋል፤ምላሱም እንደሚባላ እሳት ነው።+
28 መንፈሱ* እስከ አንገት ድረስ እንደሚደርስ የሚያጥለቀልቅ ወንዝ ነው፤ብሔራትን በጥፋት ወንፊት* ይነፋቸዋል፤በሕዝቦች መንጋጋም መንገድ እንዲስቱ የሚያደርግ ልጓም ይገባል።+
29 እናንተ ግን፣ ለበዓል በምትዘጋጁበት* ጊዜ+በሌሊት እንደሚዘመረው ያለ መዝሙር ትዘምራላችሁ፤ደግሞም ወደ እስራኤል ዓለት፣+ ወደ ይሖዋ ተራራ ሲጓዝዋሽንት ይዞ* እንደሚሄድ ሰውልባችሁ ሐሴት ያደርጋል።
30 ይሖዋ ግርማ የተላበሰ ድምፁ+ እንዲሰማ ያደርጋል፤የክንዱንም ብርታት ይገልጣል፤+ይህን የሚያደርገው በሚነድ ቁጣ፣+ በሚባላ የእሳት ነበልባል፣+ሳይታሰብ በሚወርድ ዶፍ፣+ ነጎድጓድ በቀላቀለ ውሽንፍርና በበረዶ ድንጋይ+ ታጅቦ ክንዱ ጥቃት ለመሰንዘር ወደ ታች በሚወርድበት ጊዜ ነው።
31 ከይሖዋ ድምፅ የተነሳ አሦር በሽብር ይናጣልና፤+በበትርም ይመታዋል።+
32 ይሖዋ በጦርነት ክንዱን በእነሱ ላይ በሚያነሳበት ጊዜ+በአሦር ላይ የሚያወርደውየቅጣት በትር ሁሉበአታሞና በበገና የታጀበ ይሆናል።+
33 ቶፌቱ*+ ከወዲሁ ተዘጋጅቷልና፤ለንጉሡም ተዘጋጅቶለታል።+
የእንጨት ክምሩ ጥልቀትና ስፋት ያለው እንዲሆን አድርጓል፤ብዙ እሳትና እንጨትም አለ።
የይሖዋ እስትንፋስ ልክ እንደ ድኝ ጅረትበእሳት ያያይዘዋል።
የግርጌ ማስታወሻ
^ ቃል በቃል “የመጠጥ መባ ያፈሳሉ።” ስምምነት ማድረጋቸውን የሚያሳይ ሊሆን ይችላል።
^ ወይም “ከአፌ መመሪያ ሳይጠይቁ።”
^ ቃል በቃል “በፈርዖን ምሽግ።”
^ ወይም “ተወርዋሪ መርዘኛ እባብ።”
^ ወይም “መመሪያ፤ ትምህርት።”
^ ቃል በቃል “ለስላሳ።”
^ “ከውኃ ጉድጓድ” ማለትም ሊሆን ይችላል።
^ ወይም “በእርግጠኝነት።”
^ ወይም “በጉጉት።”
^ ወይም “ቀልጠው የተሠሩ ሐውልቶችህ።”
^ “ቆሻሻ” ማለትም ሊሆን ይችላል።
^ ቃል በቃል “የሰባና ቅባት የሞላበት።”
^ ጨው ጨው የሚል ጣዕም ያለው የዕፀዋት ዓይነት።
^ ወይም “ስንጥቅ።”
^ ወይም “እስትንፋሱ።”
^ ቃል በቃል “በከንቱነት ወንፊት።”
^ ወይም “ለበዓል ራሳችሁን በምትቀድሱበት።”
^ ወይም “የዋሽንት ድምፅ እየሰማ።”
^ እዚህ ላይ “ቶፌት” የሚለው ቃል እሳት የሚነድበትን ቦታ የሚያሳይ ምሳሌያዊ አገላለጽ ሲሆን ጥፋትን ያመለክታል።