ኢሳይያስ 34:1-17

  • ይሖዋ በብሔራት ላይ የሚወስደው የበቀል እርምጃ (1-4)

  • ኤዶም ትወድማለች (5-17)

34  እናንተ ብሔራት፣ ለመስማት ወደዚህ ቅረቡ፤እናንተ ሕዝቦች፣ በትኩረት አዳምጡ። ምድርና በውስጧ ያለው ነገር ሁሉ፣ምድርና ከእሷ የሚገኘው ምርት ሁሉ ይስሙ።   ይሖዋ በሁሉም ብሔራት ላይ ተቆጥቷልና፤+በሠራዊታቸውም ሁሉ ላይ ተቆጥቷል።+ ፈጽሞ ያጠፋቸዋል፤ለእርድም አሳልፎ ይሰጣቸዋል።+   የተገደሉባቸው ሰዎች ይጣላሉ፤የአስከሬኖቻቸውም ግማት ወደ ላይ ይወጣል፤+ከደማቸውም የተነሳ ተራሮቹ ይሸረሸራሉ።*+   የሰማያት ሠራዊት ሁሉ ይበሰብሳሉ፤ሰማያትም እንደ መጽሐፍ ጥቅልል ይጠቀለላሉ። ደርቆ እንደረገፈ የወይን ቅጠልናደርቆ እንደወደቀ በለስሠራዊታቸውም ሁሉ ደርቀው ይረግፋሉ።   “ሰይፌ በሰማያት በደም ትርሳለችና።+ በኤዶም ይኸውም እንዲጠፋፍርድ ባስተላለፍኩበት ሕዝብ ላይ ትወርዳለች።+   ይሖዋ ሰይፍ አለው፤ ሰይፉም በደም ትሸፈናለች። በስብ፣+ በበግ ጠቦቶችና በፍየሎች ደምእንዲሁም በአውራ በጎች ኩላሊት ስብ ትለወሳለች።ይሖዋ በቦስራ መሥዋዕት፣ በኤዶምም ምድርታላቅ እርድ ያዘጋጃልና።+   የዱር በሬዎች ከእነሱ ጋር ይወድቃሉ፤ወይፈኖችም ከብርቱ ኮርማዎች ጋር ይወድቃሉ። ምድራቸውም በደም ይሸፈናል፤አፈራቸውም በስብ ይርሳል።”   ይሖዋ የሚበቀልበት ቀን፣+በጽዮን ላይ ለተፈጸመው በደል ቅጣት የሚያስፈጽምበት ዓመት አለውና።+   በእሷ* የሚገኙት ጅረቶች ወደ ዝፍት ይለወጣሉ፤አፈሯም ወደ ድኝ ይቀየራል፤ምድሪቱም እንደሚቃጠል ዝፍት ትሆናለች። 10  እሳቱ በሌሊትም ሆነ በቀን አይጠፋም፤ጭሷም ለዘላለም ይወጣል። ከትውልድ እስከ ትውልድም እንደወደመች ትቀራለች፤ለዘላለም ማንም በእሷ አያልፍም።+ 11  ሻላና* ጃርት ይወርሷታል፤ባለ ረጅም ጆሮ ጉጉቶችና ቁራዎችም በእሷ ውስጥ ይኖራሉ። አምላክ፣ ምድሪቱ ባዶ እንደምትሆንና እንደምትጠፋ ለማሳየትበመለኪያ ገመድና በቱንቢ* ይለካታል። 12  ከታላላቅ ሰዎቿ መካከል ለንግሥና የሚበቃ አንድም ሰው አይኖርም፤መኳንንቷም ሁሉ ይጠፋሉ። 13  በማይደፈሩ ማማዎቿ ላይ እሾህ፣በምሽጎቿም ላይ ሳማና ኩርንችት ይበቅላል። የቀበሮዎች ማደሪያ፣+የሰጎኖችም መኖሪያ ትሆናለች። 14  የበረሃ ፍጥረታት ከሚያላዝኑ እንስሶች ጋር ይገናኛሉ፤የዱር ፍየልም* ባልንጀራውን ይጠራል። የሌሊት ወፍ በዚያ ታርፋለች፤ ማረፊያ ስፍራም ታገኛለች። 15  ተወንጫፊ እባብ በዚያ ጎጆዋን ትሠራለች፤ እንቁላልም ትጥላለች፤ከዚያም ትቀፈቅፋለች፤ በጥላዋም ሥር ትሰበስባቸዋለች። ጭላቶችም ጥንድ ጥንድ ሆነው በዚያ ይሰበሰባሉ። 16  በይሖዋ መጽሐፍ ውስጥ ፈልጉ፤ ድምፃችሁንም ከፍ አድርጋችሁ አንብቡ፤ ከእነሱ መካከል አንዳቸውም አይጎድሉም፤ሁሉም ተጓዳኝ አያጡም፤ይህ ትእዛዝ የወጣው ከይሖዋ አፍ ነውና፤አንድ ላይ የሰበሰባቸውም የእሱ መንፈስ ነው። 17  ዕጣ የጣለላቸው እሱ ነው፤የተመደበላቸውን ቦታ የለካው የገዛ እጁ ነው።* እነሱም ለዘለቄታው ይወርሱታል፤ከትውልድ እስከ ትውልድም በዚያ ይኖራሉ።

የግርጌ ማስታወሻ

ወይም “ተራሮቹ በደም ይጥለቀለቃሉ።”
የኤዶም ዋና ከተማ የሆነችውን ቦስራን የሚያመለክት ሊሆን ይችላል።
ወይም “ገርጌሶና።” ጠፍጠፍ ያለ ረጅም መንቆር ያለው ትልቅ አሞራ።
ቃል በቃል “በድንጋዮች።”
“ፍየል የሚመስል ጋኔንም” ማለትም ሊሆን ይችላል።
ቃል በቃል “በመለኪያ ገመድ ለክቶ አከፋፍሏቸዋል።”