ኢሳይያስ 50:1-11

  • የእስራኤል ኃጢአት ያስከተለው ችግር (1-3)

  • የይሖዋ ታዛዥ አገልጋይ (4-11)

    • ከአምላክ የተማሩ ሰዎች አንደበትና ጆሮ (4)

50  ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “እናታችሁን በሰደድኳት ጊዜ የፍቺ የምሥክር ወረቀት+ ሰጥቻታለሁ? እናንተንስ የሸጥኳችሁ ለየትኛው አበዳሪዬ ነው? እነሆ፣ የተሸጣችሁት በገዛ ጥፋታችሁ+ ነው፤እናታችሁም እንድትሄድ የተደረገው በገዛ በደላችሁ ነው።+   ታዲያ በመጣሁ ጊዜ እዚህ ማንም ያልነበረው ለምንድን ነው? በተጣራሁስ ጊዜ የሚመልስ ሰው የጠፋው ለምንድን ነው?+ እጄ አጭር ሆና እናንተን መዋጀት ተስኗታል?ወይስ እናንተን ለመታደግ የሚያስችል ኃይል የለኝም?+ እነሆ፣ በተግሣጼ ባሕሩን አደርቃለሁ፤+ወንዞችን በረሃ አደርጋለሁ።+ ዓሣዎቻቸው ውኃ ባለማግኘታቸው ይበሰብሳሉ፤በውኃ ጥምም ይሞታሉ።   ሰማያትን ጨለማ አለብሳለሁ፤+ማቅንም መሸፈኛቸው አደርጋለሁ።”   ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ፣ ለደከመው ትክክለኛውን ቃል በመናገርእንዴት መልስ* መስጠት እንደምችል አውቅ ዘንድ+ የተማሩ ሰዎችን አንደበት* ሰጥቶኛል።+ በየማለዳው ያነቃኛል፤እንደ ተማሪ አዳምጥ ዘንድ ጆሮዬን ያነቃል።+   ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ጆሮዬን ከፍቷል፤እኔም ዓመፀኛ አልነበርኩም።+ ጀርባዬን አልሰጠሁም።+   ለሚገርፉኝ ጀርባዬን፣ጢም ለሚነጩም ጉንጮቼን ሰጠሁ። ፊቴን፣ ከሚያዋርዱ ነገሮችና ከትፋት አልሰወርኩም።+   ሆኖም ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ይረዳኛል።+ ስለዚህ አልዋረድም። ከዚህም የተነሳ ፊቴን እንደ ባልጩት አደረግኩ፤+ለኀፍረት እንደማልዳረግም አውቃለሁ።   ጻድቅ መሆኔን የሚመሠክርልኝ ቀርቧል። ታዲያ ማን ሊከሰኝ* ይችላል?+ በአንድነት እንቁም።* ከእኔ ጋር ሙግት ያለው ማን ነው? እስቲ ወደ እኔ ይቅረብ።   እነሆ፣ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ይረዳኛል። ታዲያ ጥፋተኛ ነህ ሊለኝ የሚችል ማን ነው? እነሆ፣ ሁሉም እንደ ልብስ ያረጃሉ። ብል ይበላቸዋል። 10  ከመካከላችሁ ይሖዋን የሚፈራ፣የአገልጋዩንም ድምፅ የሚሰማ ማን ነው?+ ብርሃን በሌለበት በድቅድቅ ጨለማ የሄደ ማን ነው? በይሖዋ ስም ይታመን፤ በአምላኩም ይደገፍ።* 11  “እነሆ፣ እናንተ እሳት የምታያይዙ፣የእሳት ፍንጣሪ የምታበሩ ሁሉ፣በእሳታችሁ ብርሃን፣ባያያዛችሁትም እሳት ብልጭታዎች መካከል ሂዱ። ከእጄ የምትቀበሉት ይህ ነው፦ በከባድ ሥቃይ ትጋደማላችሁ።

የግርጌ ማስታወሻ

“ማበረታቻ” ማለትም ሊሆን ይችላል።
ወይም “በሚገባ የሠለጠነ አንደበት።”
ወይም “ሊሟገተኝ።”
ወይም “ፊት ለፊት እንጋጠም።”
ወይም “ይመካ።”