ኢሳይያስ 52:1-15

  • “ጽዮን ሆይ፣ ተነሺ!” (1-12)

    • ምሥራች ይዘው የሚመጡ ያማሩ እግሮች (7)

    • የጽዮን ጠባቂዎች በአንድነት እልል ይላሉ (8)

    • የይሖዋን ዕቃ የሚሸከሙ ንጹሕ መሆን ይጠበቅባቸዋል (11)

  • የይሖዋ አገልጋይ ከፍ ከፍ ይላል (13-15)

    • ከሰው ልጆች ሁሉ ይልቅ ተጎሳቆለ (14)

52  ጽዮን ሆይ፣+ ተነሺ! ተነሺ! ብርታትን ልበሺ!+ ቅድስቲቱ ከተማ ኢየሩሳሌም ሆይ፣ የሚያምሩ ልብሶችሽን ልበሺ!+ ከእንግዲህ ወዲህ ያልተገረዘና ርኩስ የሆነ ወደ አንቺ አይገባምና።+   ኢየሩሳሌም ሆይ፣ አቧራሽን አራግፊ፤ ተነስተሽ ቦታሽን ያዢ። ምርኮኛ የሆንሽው የጽዮን ሴት ልጅ ሆይ፣ አንገትሽ ላይ ያለውን ማሰሪያ ፍቺ።+   ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦ “ያለዋጋ ተሸጣችሁ ነበር፤+ያለገንዘብም ትቤዣላችሁ።”+   ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦ “በመጀመሪያ ሕዝቤ ባዕድ ሆኖ ለመኖር ወደ ግብፅ ወረደ፤+ከዚያም አሦር ያላንዳች ምክንያት በጭቆና ገዛው።”   “ታዲያ እዚህ ምን ማድረግ ይኖርብኛል?” ይላል ይሖዋ። “ሕዝቤ የተወሰደው ያለዋጋ ነውና። የሚገዟቸው በድል አድራጊነት ጉራ ይነዛሉ”+ ይላል ይሖዋ፤“ስሜንም ቀኑን ሙሉ ያለማቋረጥ ያቃልላሉ።+   በዚህ ምክንያት ሕዝቤ ስሜን ያውቃል፤+በዚህም የተነሳ የተናገርኩት እኔ እንደሆንኩ በዚያ ቀን ያውቃሉ። እነሆ፣ እኔ ነኝ!”   ምሥራች ይዞ የሚመጣ፣+ሰላምን የሚያውጅ፣+የተሻለ ነገር እንደሚመጣ ምሥራች የሚያበስር፣መዳንን የሚያውጅ፣ጽዮንንም “አምላክሽ ነግሦአል!”+ የሚል በተራሮች ላይ እግሮቹ እንዴት ያማሩ ናቸው!   ስሚ! ጠባቂዎችሽ ድምፃቸውን ከፍ ያደርጋሉ። በአንድነት ሆነው እልል ይላሉ፤ይሖዋ ጽዮንን መልሶ ሲሰበስብ በግልጽ* ያያሉና።   እናንተ የኢየሩሳሌም ፍርስራሾች፣ ደስ ይበላችሁ፤ በአንድነትም እልል በሉ፤+ይሖዋ ሕዝቡን አጽናንቷልና፤+ ኢየሩሳሌምንም ተቤዥቷል።+ 10  ይሖዋ በብሔራት ሁሉ ፊት ቅዱስ ክንዱን ገልጧል፤+የምድር ዳርቻዎችም ሁሉ የአምላካችንን የማዳን ሥራዎች* ያያሉ።+ 11  እናንተ የይሖዋን ዕቃ የምትሸከሙ፣+ ገለል በሉ፣ ገለል በሉ፤ ከዚያ ውጡ፤+ ማንኛውንም ርኩስ ነገር አትንኩ!+ከመካከሏ ውጡ፤+ ንጽሕናችሁን ጠብቁ። 12  ተደናግጣችሁ አትወጡም፤ሸሽታችሁም አትሄዱም፤ይሖዋ በፊታችሁ ይሄዳልና፤+የእስራኤል አምላክም ደጀን ይሆናችኋል።+ 13  እነሆ፣ አገልጋዬ+ ማንኛውንም ነገር የሚያከናውነው በጥልቅ ማስተዋል ነው። ላቅ ያለ ቦታ ይሰጠዋል፤ከፍ ከፍ ይላል፤ እጅግም ይከበራል።+ 14  ብዙዎች በመገረም ትኩር ብለው እንዳዩት ሁሉ፣(መልኩ ከማንኛውም ሰው የባሰ፣ግርማ የተላበሰ ቁመናውም ከሰው ልጆች ሁሉ ይልቅ ተጎሳቁሎ ነበር) 15  እሱም ብዙ ብሔራትን+ ያስደንቃል። ነገሥታት በእሱ ፊት አፋቸውን ይዘጋሉ፤*+ምክንያቱም ያልተነገራቸውን ያያሉ፤ወዳልሰሙትም ነገር ትኩረታቸውን ያዞራሉ።+

የግርጌ ማስታወሻ

ወይም “ዓይን በዓይን።”
ወይም “ድል።”
ወይም “በእሱ ፊት ዱዳ ይሆናሉ።”