ኢሳይያስ 56:1-12

  • የባዕድ አገር ሰውና ጃንደረባ የሚያገኙት በረከት (1-8)

    • ለሰው ሁሉ የሚሆን የጸሎት ቤት (7)

  • ዕውር ጠባቂዎች፤ መናገር የማይችሉ ውሾች (9-12)

56  ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ፍትሕን ጠብቁ፤+ ጽድቅ የሆነውንም አድርጉ፤ማዳኔ በቅርቡ ይመጣልና፤ጽድቄም ይገለጣል።+   ይህን የሚያደርግ ሰው፣ደግሞም ይህን አጥብቆ የሚይዝ፣ሰንበትን የሚጠብቅና የማያረክስ፣+እንዲሁም ከማንኛውም ዓይነት ክፋት እጁን የሚመልስ የሰው ልጅ ደስተኛ ነው።   ከይሖዋ ጋር የሚቆራኝ የባዕድ አገር ሰው+‘ይሖዋ ከሕዝቡ እንደሚለየኝ ጥርጥር የለውም’ አይበል። ጃንደረባም ‘እነሆ፣ እኔ ደረቅ ዛፍ ነኝ’ አይበል።”  ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦ “ሰንበቶቼን ለሚጠብቁ፣ ደስ የሚያሰኘኝን ነገር ለሚመርጡና ቃል ኪዳኔን አጥብቀው ለሚይዙ ጃንደረቦች፣   በቤቴና በቅጥሮቼ ውስጥከወንዶችና ከሴቶች ልጆች የሚሻል ነገር፣ ይኸውም የመታሰቢያ ሐውልትና ስም እሰጣቸዋለሁ።ለዘላለም የማይጠፋ ስም እሰጣቸዋለሁ።   እሱን ለማገልገል፣ የይሖዋን ስም ለመውደድናየእሱ አገልጋዮች ለመሆንከይሖዋ ጋር የሚቆራኙትን የባዕድ አገር ሰዎች፣+ሰንበትን የሚጠብቁትንና የማያረክሱትን፣ቃል ኪዳኔንም አጥብቀው የሚይዙትን ሁሉ፣   ቅዱስ ወደሆነው ተራራዬ አመጣቸዋለሁ፤+በጸሎት ቤቴም ውስጥ እጅግ እንዲደሰቱ አደርጋቸዋለሁ። የሚያቀርቧቸውም ሙሉ በሙሉ የሚቃጠሉ መባዎችና መሥዋዕቶች በመሠዊያዬ ላይ ተቀባይነት ያገኛሉ። ቤቴም ለሕዝቦች ሁሉ የጸሎት ቤት ተብሎ ይጠራልና።”+  የተበተኑትን የእስራኤል ሰዎች የሚሰበስበው ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ+ እንዲህ ይላል፦ “አስቀድሞ ከተሰበሰቡት በተጨማሪ ሌሎችን ወደ እሱ እሰበስባለሁ።”+   እናንተ በሜዳ ያላችሁ አራዊት ሁሉ፣እናንተ በጫካ የምትኖሩ አራዊት ሁሉ፣ ኑና ብሉ።+ 10  ጠባቂዎቹ ዕውሮች ናቸው፤+ አንዳቸውም አላስተዋሉም።+ ሁሉም መናገር የማይችሉ ውሾች ናቸው፤ መጮኽ አይችሉም።+ ተጋድመው ያለከልካሉ፤ እንቅልፍም ይወዳሉ። 11  በቀላሉ የማይጠግቡ* ውሾች ናቸው፤ጠገብኩ ማለትን አያውቁም። ማስተዋል የሌላቸው እረኞች ናቸው።+ ሁሉም በገዛ ራሳቸው መንገድ ሄደዋል፤እያንዳንዳቸው አግባብ ያልሆነ ጥቅም ለማግኘት ይሻሉ፤ እንዲህም ይላሉ፦ 12  “ኑ! የወይን ጠጅ ላምጣናእስኪወጣልን ድረስ እንጠጣ።+ ነገም እንደ ዛሬ ይሆናል፤ እንዲያውም በጣም የተሻለ ይሆናል።”

የግርጌ ማስታወሻ

ወይም “ብርቱ ነፍስ ያላቸው።”