ኢሳይያስ 57:1-21
57 ጻድቁ ሞቷል፤ይህን ግን ማንም ልብ አይልም።
ታማኝ ሰዎች ተወስደዋል፤*+ሆኖም ጻድቁ የተወሰደውከመከራ የተነሳ እንደሆነ* የሚያስተውል የለም።
2 እሱ ሰላም ያገኛል።
በቅንነት የሚሄዱ ሁሉ አልጋቸው* ላይ ያርፋሉ።
3 “ይሁንና እናንተ የአስማተኛዋ ወንዶች ልጆች፣የአመንዝራና የዝሙት አዳሪ ልጆች፣ኑ ወደዚህ ቅረቡ፦
4 የምታሾፉት በማን ላይ ነው?
አፋችሁን የምትከፍቱትና ምላሳችሁን የምታወጡትስ በማን ላይ ነው?
እናንተ የዓመፅ ልጆች፣የሐሰትም* ልጆች አይደላችሁም?+
5 በትላልቅ ዛፎች መካከል፣ቅጠሉ በተንዠረገገም ዛፍ ሥር ሁሉ በስሜት የተቃጠላችሁ፣+በሸለቆዎች* ውስጥ፣ በቋጥኞች መካከልልጆችን የምታርዱ አይደላችሁም?+
6 በሸለቆው* ውስጥ ያሉት ለስላሳ ድንጋዮች ድርሻዎችሽ ናቸው።+
አዎ፣ እነዚህ ዕጣ ፋንታዎችሽ ናቸው።
ለእነሱም ጭምር የመጠጥ መባ አፍስሰሻል፤ ስጦታም አቅርበሻል።+
ታዲያ እኔ በእነዚህ ነገሮች ደስ ልሰኝ ይገባል?*
7 በረጅሙና ከፍ ባለው ተራራ ላይ አልጋሽን አነጠፍሽ፤+መሥዋዕት ለማቅረብም ወደዚያ ወጣሽ።+
8 ከበሩና ከመቃኑ ጀርባ የመታሰቢያ ምልክትሽን አደረግሽ።
እኔን ተውሽኝ፤ እርቃንሽንም ገለጥሽ፤ወደ ላይ ወጣሽ፤ መኝታሽንም አሰፋሽ።
ከእነሱም ጋር ቃል ኪዳን ገባሽ።
በአልጋቸው ላይ አብረሽ መተኛት ወደድሽ፤+የወንድ ብልትም* አፍጥጠሽ አየሽ።
9 ዘይትና ብዛት ያለው ሽቶ ይዘሽወደ ሜሌክ* ወረድሽ።
መልእክተኞችሽን ወደ ሩቅ ቦታ ላክሽ፤በመሆኑም ወደ መቃብር* ወረድሽ።
10 ብዛት ያላቸውን መንገዶችሽን በመከተል ደከምሽ፤ሆኖም ‘ተስፋ የለውም!’ አላልሽም።
ጉልበትሽ ታደሰ።
ተስፋ ያልቆረጥሽው* ለዚህ ነው።
11 መዋሸት የጀመርሽው+ ማን አስፈርቶሽ፣ማንስ ስጋት አሳድሮብሽ ነው?
እኔን አላስታወስሽም።+
ልብ ያልሽውም ነገር የለም።+
እኔ ዝም አላልኩም? ደግሞስ ከመናገር አልተቆጠብኩም?*+
በመሆኑም እኔን አልፈራሽም።
12 ‘ጽድቅሽን’+ እና ሥራሽን+ እናገራለሁ፤እነሱም አይጠቅሙሽም።+
13 እርዳታ ለማግኘት በምትጮኺበት ጊዜየሰበሰብሻቸው ጣዖቶች አይታደጉሽም።+
ነፋስ ሁሉንም ጠራርጎ ይወስዳቸዋል፤እስትንፋስ ይዟቸው ይሄዳል፤እኔን መጠጊያ የሚያደርግ ግን ምድሪቱን ይወርሳል፤ቅዱስ ተራራዬም ርስቱ ይሆናል።+
14 እንዲህ ይባላል፦ ‘መንገድ ሥሩ! መንገድ ሥሩ! መንገዱን አዘጋጁ!+
ሕዝቤ ከሚሄድበት መንገድ ላይ ማንኛውንም እንቅፋት አስወግዱ።’”
15 ለዘላለም የሚኖረውና+ ስሙ ቅዱስ የሆነው፣+ከፍ ከፍ ያለውና እጅግ የከበረው እንዲህ ይላልና፦
“ከፍ ባለውና ቅዱስ በሆነው ስፍራ እኖራለሁ፤+ደግሞም የተሰበረ ልብ ካለውና መንፈሱ ከተደቆሰው ጋር እሆናለሁ፤ይህም የችግረኞችን መንፈስ አነሳሳ ዘንድ፣የተሰበረ ልብ ያላቸውንም አነቃቃ ዘንድ ነው።+
16 ለዘላለም አልቃወማቸውም፤ወይም ለዘለቄታው አልቆጣም፤+በእኔ የተነሳ የሰው መንፈስ፣እኔ የሠራኋቸው እስትንፋስ ያላቸው ፍጥረታትም እንኳ ይዝላሉና።+
17 በማጭበርበር ጥቅም ለማግኘት ሲል በፈጸመው ኃጢአት እጅግ ተቆጣሁ፤+በመሆኑም መታሁት፤ ፊቴን ሰወርኩ፤ ተቆጣሁም።
እሱ ግን እንደ ከዳተኛ የልቡን መንገድ ተከትሎ መሄዱን ገፋበት።+
18 መንገዶቹን አይቻለሁ፤ሆኖም እፈውሰዋለሁ፤+ እንዲሁም እመራዋለሁ፤+ለእሱም ሆነ ላዘኑ ወገኖቹ መጽናኛን እመልሳለሁ።”*+
19 “የከንፈሮችን ፍሬ እፈጥራለሁ።
በሩቅም ሆነ በቅርብ ያለው ዘላቂ ሰላም ያገኛል፤+እኔም እፈውሰዋለሁ” ይላል ይሖዋ።
20 “ክፉዎች ግን ጸጥ ማለት እንደማይችል የሚናወጥ ባሕር ናቸው፤ውኃውም የባሕር ውስጥ ዕፀዋትንና ጭቃን ያወጣል።
21 ክፉዎች ሰላም የላቸውም” ይላል አምላኬ።+
የግርጌ ማስታወሻ
^ “ከመከራ እንዲተርፍ መሆኑን” ማለትም ሊሆን ይችላል።
^ መሞትን ያመለክታል።
^ መቃብርን ያመለክታል።
^ ወይም “የማታለልም።”
^ ወይም “በደረቅ ወንዞች።”
^ ወይም “ራሴን ላጽናና ይገባል?”
^ ወይም “በደረቁ ወንዝ።”
^ የጣዖት አምልኮን የሚያመለክት ሊሆን ይችላል።
^ “ወደ ንጉሡ” ማለትም ሊሆን ይችላል።
^ ወይም “ሲኦል።” የሰው ልጆችን ሁሉ መቃብር ያመለክታል። የቃላት መፍቻውን ተመልከት።
^ ቃል በቃል “ያልዛልሽው።”
^ ወይም “ነገሮችን አልደበቅኩም?”
^ ወይም “እሱንም ሆነ ያዘኑ ወገኖቹን በማጽናናት እክሳቸዋለሁ።”