ኢሳይያስ 60:1-22
60 “አንቺ ሴት ሆይ፣ ተነሺ፣+ ብርሃን አብሪ፤ ብርሃንሽ መጥቷልና።
የይሖዋ ክብር በአንቺ ላይ ያበራል።+
2 እነሆ፣ ጨለማ ምድርን፣ድቅድቅ ጨለማም ብሔራትን ይሸፍናል፤በአንቺ ላይ ግን ይሖዋ ያበራል፤ክብሩም በአንቺ ላይ ይታያል።
3 ብሔራት ወደ ብርሃንሽ፣+ነገሥታትም+ አንጸባራቂ ወደሆነው ውበትሽ* ይመጣሉ።+
4 ዓይንሽን አንስተሽ ዙሪያሽን ተመልከቺ!
ሁሉም አንድ ላይ ተሰብስበዋል፤ ወደ አንቺም እየመጡ ነው።
ከሩቅ ቦታ ወንዶች ልጆችሽ በመምጣት ላይ ናቸው፤+ሴቶች ልጆችሽም ታዝለው እየመጡ ነው።+
5 በዚያን ጊዜ ታያለሽ፤ ፊትሽም ይፈካል፤+ልብሽ በኃይል ይመታል፤ በደስታም ይሞላል፤ምክንያቱም የባሕር ብልጽግና ወደ አንቺ ይጎርፋል፤የብሔራትም ሀብት ወደ አንቺ ይመጣል።+
6 የግመል መንጋ ምድርሽን ይሸፍናል፤*የምድያምና የኤፋ+ ግልገል ግመሎች ያጥለቀልቁሻል።
ሁሉም ወርቅና ነጭ ዕጣን ይዘውከሳባ ይመጣሉ።
የይሖዋንም ውዳሴ ያውጃሉ።+
7 የቄዳር+ መንጎች ሁሉ ወደ አንቺ ይሰበሰባሉ።
የነባዮት+ አውራ በጎች ያገለግሉሻል።
እነሱም በመሠዊያዬ ላይ ተቀባይነት ያለው መሥዋዕት ይሆናሉ፤+ክብራማ የሆነውንም ቤቴን* አሳምረዋለሁ።+
8 እንደ ደመና፣ ወደ ቤታቸውም* እንደሚተሙ ርግቦችእየበረሩ የሚመጡት እነዚህ እነማን ናቸው?
9 ደሴቶች እኔን ተስፋ ያደርጋሉና፤+የተርሴስ መርከቦችም ከሩቅ ወንዶች ልጆችሽንከነብራቸውና ከነወርቃቸውለአምላክሽ ለይሖዋ ስምና ለእስራኤል ቅዱስ ለማምጣት+ቀዳሚ ሆነው* ይወጣሉ፤እሱ ክብር* ያጎናጽፍሻልና።+
10 የባዕድ አገር ሰዎች ቅጥሮችሽን ይገነባሉ፤ነገሥታታቸውም ያገለግሉሻል፤+በቁጣዬ መትቼሻለሁና፤በሞገሴ* ግን ምሕረት አሳይሻለሁ።+
11 በሮችሽ ሁልጊዜ ክፍት ይሆናሉ፤+የብሔራትን ሀብት ወደ አንቺ ያመጡ ዘንድበሮችሽ ቀንም ሆነ ሌሊት አይዘጉም፤ነገሥታታቸውም ቀዳሚ ይሆናሉ።+
12 አንቺን የማያገለግል ማንኛውም ብሔርም ሆነ ማንኛውም መንግሥት ይጠፋልና፤ብሔራትም ፈጽመው ይደመሰሳሉ።+
13 የመቅደሴን ስፍራ አስውብ ዘንድየሊባኖስ ክብር፣+ ጥዱ፣ የአሽ ዛፉና* የፈረንጅ ጥዱበአንድነት ወደ አንቺ ይመጣሉ፤+እግሬ የሚያርፍበትንም ስፍራ አከብራለሁ።+
14 የጨቋኞችሽ ወንዶች ልጆች መጥተው በፊትሽ ይሰግዳሉ፤የሚያዋርዱሽ ሁሉ እግርሽ ሥር ይደፋሉ፤ደግሞም የይሖዋ ከተማ፣የእስራኤልም ቅዱስ አምላክ ንብረት የሆንሽ ጽዮን ብለው ይጠሩሻል።+
15 የተተውሽና የተጠላሽ፣ ማንም ሰው የማያልፍብሽ መሆንሽ ቀርቶ+የዘላለም መኩሪያ፣ከትውልድ እስከ ትውልድም የደስታ ምንጭ እንድትሆኚ አደርግሻለሁ።+
16 አንቺም የብሔራትን ወተት ትጠጫለሽ፤+የነገሥታትን ጡት ትጠቢያለሽ፤+እኔ ይሖዋ አዳኝሽ እንደሆንኩ፣ደግሞም የያዕቆብ ኃያል አምላክ የሆንኩት እኔ እንደምቤዥሽ በእርግጥ ታውቂያለሽ።+
17 በመዳብ ፋንታ ወርቅ፣በብረት ፋንታ ብር፣በእንጨት ፋንታ መዳብ፣በድንጋዮችም ፋንታ ብረት አመጣለሁ፤ሰላምንም የበላይ ተመልካቾችሽ፣ጽድቅንም አሠሪዎችሽ አድርጌ እሾማለሁ።+
18 ከዚህ በኋላ በምድርሽ ውስጥ ዓመፅ፣ወይም በክልልሽ ውስጥ ጥፋትና ውድመት አይሰማም።+
ቅጥሮችሽን መዳን፣+ በሮችሽንም ውዳሴ ብለሽ ትጠሪያቸዋለሽ።
19 ከእንግዲህ ፀሐይ በቀን ብርሃን አትሆንልሽም፤የጨረቃም ብርሃን ከእንግዲህ አያበራልሽም፤ይሖዋ የዘላለም ብርሃን፣+አምላክሽም ውበት ይሆንልሻልና።+
20 ፀሐይሽ ከእንግዲህ አትጠልቅም፤ጨረቃሽም አትደበዝዝም፤ይሖዋ የዘላለም ብርሃን ይሆንልሻልና፤+የሐዘንሽም ጊዜ ያበቃል።+
21 ሕዝቦችሽም ሁሉ ጻድቃን ይሆናሉ፤ምድሪቱን ለዘላለም ይወርሳሉ።
እነሱ፣ ውበት እጎናጸፍ ዘንድ የተከልኳቸው ችግኞች፣የእጆቼም ሥራ ናቸው።+
22 ጥቂት የሆነው ሺህ፣ትንሽ የሆነውም ኃያል ብሔር ይሆናል።
እኔ ይሖዋ፣ ይህን በራሱ ጊዜ አፋጥነዋለሁ።”