ኢሳይያስ 61:1-11

  • “ምሥራች እንድናገር ቀብቶኛል” (1-11)

    • ‘ይሖዋ በጎ ፈቃድ የሚያሳይበት ዓመት’ (2)

    • “ትላልቅ የጽድቅ ዛፎች” (3)

    • የባዕድ አገር ሰዎች እርዳታ ያበረክታሉ (5)

    • “የይሖዋ ካህናት” (6)

61  የሉዓላዊው ጌታ የይሖዋ መንፈስ በእኔ ላይ ነው፤+ምክንያቱም ይሖዋ የዋህ ለሆኑ ሰዎች ምሥራች እንድናገር ቀብቶኛል።+ ልባቸው የተሰበረውን እንድጠግን፣ለተማረኩት ነፃነትን እንዳውጅእንዲሁም ‘የእስረኞች ዓይን ይከፈታል’ ብዬ እንድናገር ልኮኛል፤+   ይሖዋ በጎ ፈቃድ* የሚያሳይበትን ዓመት፣አምላካችን የሚበቀልበትንም ቀን እንዳውጅ፣+የሚያለቅሱትንም ሁሉ እንዳጽናና ልኮኛል፤+   በጽዮን የተነሳ ላዘኑትበአመድ ፋንታ የራስ መሸፈኛ፣በሐዘን ፋንታ የደስታ ዘይት፣በተደቆሰም መንፈስ ፋንታ የውዳሴ ልብስ እንድሰጥ ልኮኛል። እነሱም ይሖዋ ራሱን ክብር ለማጎናጸፍ*የተከላቸው ትላልቅ የጽድቅ ዛፎች ተብለው ይጠራሉ።+   የጥንቶቹን ፍርስራሾች መልሰው ይገነባሉ፤በቀድሞዎቹ ጊዜያት ባድማ የሆኑትን ቦታዎች ይሠራሉ፤+የወደሙትን ከተሞች፣ከትውልድ እስከ ትውልድም ፈራርሰው የቆዩትን ቦታዎች መልሰው ይገነባሉ።+   “እንግዳ ሰዎች መጥተው መንጎቻችሁን ይጠብቃሉ፤የባዕድ አገር ሰዎችም+ ገበሬዎቻችሁና የወይን አትክልት ሠራተኞቻችሁ ይሆናሉ።+   እናንተም የይሖዋ ካህናት ተብላችሁ ትጠራላችሁ፤+የአምላካችን አገልጋዮች ብለው ይጠሯችኋል። የብሔራትን ሀብት ትበላላችሁ፤+በእነሱም ክብር* ትኮራላችሁ።   በኀፍረት ፋንታ እጥፍ ድርሻ ይኖራችኋል፤በውርደትም ፋንታ በሚያገኙት ድርሻ በደስታ እልል ይላሉ። አዎ፣ በምድራቸው እጥፍ ድርሻ ይወርሳሉ።+ የዘላለም ሐሴት የእነሱ ይሆናል።+   እኔ ይሖዋ ፍትሕን እወዳለሁና፤+ዝርፊያንና ክፋትን እጠላለሁ።+ ደሞዛቸውን በታማኝነት እሰጣቸዋለሁ፤ከእነሱም ጋር ዘላለማዊ ቃል ኪዳን አደርጋለሁ።+   ዘሮቻቸው በብሔራት፣ልጆቻቸውም በሕዝቦች መካከል የታወቁ ይሆናሉ።+ የሚያዩአቸው ሁሉይሖዋ የባረካቸው ዘሮች እንደሆኑ ይገነዘባሉ።”+ 10  እኔ በይሖዋ እጅግ ደስ ይለኛል። ሁለንተናዬ በአምላኬ ሐሴት ያደርጋል።*+ የመዳንን መጎናጸፊያ አልብሶኛልና፤+የካህን ዓይነት ጥምጥም+ እንደሚያደርግ ሙሽራ፣በጌጣጌጧም ራሷን እንዳስዋበች ሙሽሪትየጽድቅ ቀሚስ አልብሶኛል። 11  ምድር ቡቃያዋን እንደምታበቅል፣የአትክልት ቦታም በላዩ ላይ የተዘሩትን ዘሮች እንደሚያበቅልሉዓላዊው ጌታ ይሖዋምበብሔራት ሁሉ ፊት ጽድቅንና+ ውዳሴን ያበቅላል።+

የግርጌ ማስታወሻ

ወይም “ሞገስ።”
ወይም “ራሱን ውበት ለማጎናጸፍ።”
ወይም “ሀብት።”
ወይም “ነፍሴ በአምላኬ ሐሴት ታደርጋለች።”