ኢሳይያስ 62:1-12

  • የጽዮን አዲስ ስም (1-12)

62  ጽድቋ እንደ ደማቅ ብርሃን እስኪፈነጥቅ፣+መዳኗም እንደ ችቦ እስኪቀጣጠል ድረስለጽዮን ስል ጸጥ አልልም፤+ለኢየሩሳሌምም ስል ዝም ብዬ አልቀመጥም።+   “አንቺ ሴት ሆይ፣+ ብሔራት ጽድቅሽን፣ነገሥታትም ሁሉ ክብርሽን ያያሉ።+ አንቺም የይሖዋ አፍ በሚያወጣልሽአዲስ ስም ትጠሪያለሽ።+   በይሖዋ እጅ የውበት ዘውድ፣በአምላክሽ መዳፍ የንጉሥ ጥምጥም ትሆኛለሽ።   ከእንግዲህ የተተወች ሴት አትባዪም፤+ምድርሽም ከእንግዲህ ባድማ ተብላ አትጠራም።+ ከዚህ ይልቅ “ደስታዬ በእሷ ነው” ተብለሽ ትጠሪያለሽ፤+ምድርሽም “ያገባች ሴት” ትባላለች። ይሖዋ በአንቺ ደስ ይለዋልና፤ምድርሽም እንዳገባች ሴት ትሆናለች።   አንድ ወጣት ድንግሊቱን እንደሚያገባ፣ወንዶች ልጆችሽ አንቺን ያገባሉ። አንድ ሙሽራ በሙሽራይቱ ሐሴት እንደሚያደርግ፣አምላክሽም በአንቺ ሐሴት ያደርጋል።+   ኢየሩሳሌም ሆይ፣ በቅጥሮችሽ ላይ ጠባቂዎች አቁሜአለሁ። ቀኑንም ሆነ ሌሊቱን በሙሉ፣ መቼም ቢሆን ዝም ሊሉ አይገባም። እናንተ ስለ ይሖዋ የምትናገሩ፣ፈጽሞ አትረፉ፤   ደግሞም ኢየሩሳሌምን አጽንቶ እስኪመሠርታት፣አዎ፣ የምድር ምስጋና እስኪያደርጋት ድረስ ምንም እረፍት አትስጡት።”+   ይሖዋ በቀኝ እጁ፣ ብርቱ በሆነውም ክንዱ እንዲህ ሲል ምሏል፦ “ከእንግዲህ እህልሽን ለጠላቶችሽ መብል እንዲሆን አልሰጥም፤የደከምሽበትንም አዲስ የወይን ጠጅ የባዕድ አገር ሰዎች አይጠጡትም።+   ሆኖም እህሉን፣ የሚሰበስቡት ሰዎች ይበሉታል፤ ይሖዋንም ያወድሳሉ፤ወይኑንም፣ የሚለቅሙት ሰዎች ቅዱስ በሆኑት ቅጥር ግቢዎቼ ውስጥ ይጠጡታል።”+ 10  በበሮቹ በኩል እለፉ፤ እለፉ። ለሕዝቡ መንገዱን ጥረጉ።+ ሥሩ፤ አውራ ጎዳናውን ሥሩ። ድንጋዮቹን አስወግዱ።+ ለሕዝቦችም ምልክት* አቁሙ።+ 11  እነሆ፣ ይሖዋ እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ አውጇል፦ “ለጽዮን ሴት ልጅ‘እነሆ፣ መዳንሽ ቀርቧል።+ እነሆ፣ የሚከፍለው ወሮታ ከእሱ ጋር ነው፤የሚመልሰውም ብድራት በፊቱ አለ’ በሏት።”+ 12  ቅዱስ ሕዝብ፣ ይሖዋ የተቤዣቸው+ ተብለው ይጠራሉ፤አንቺም “እጅግ የምትፈለግ፣” “ያልተተወች ከተማ” ተብለሽ ትጠሪያለሽ።+

የግርጌ ማስታወሻ

ወይም “ለምልክት የሚተከል ምሰሶ።”