ኢሳይያስ 63:1-19

  • ይሖዋ በብሔራት ላይ የሚወስደው የበቀል እርምጃ (1-6)

  • የይሖዋ ታማኝ ፍቅር (7-14)

  • የንስሐ ጸሎት (15-19)

63  ይህ ከኤዶም የሚመጣው፣+ደማቅ ቀለም ያለው* ልብስ ለብሶ ከቦስራ+ የሚገሰግሰው ማን ነው?ይህ እጅግ ያማረ ልብስ ለብሶናበታላቅ ኃይል ተሞልቶ የሚራመደው ማን ነው? “በጽድቅ የምናገር፣ለማዳን የሚያስችል ታላቅ ኃይል ያለኝ እኔ ነኝ።”   መጎናጸፊያህ የቀላውናልብሶችህ በመጭመቂያ ውስጥ ወይን እንደሚረግጥ ሰው ልብስ የሆኑት ለምንድን ነው?+   “በወይን መጭመቂያው ውስጥ ወይኑን ብቻዬን ረገጥኩ። ከሕዝቦች መካከል ከእኔ ጋር ማንም አልነበረም። በቁጣዬም ረጋገጥኳቸው፤በታላቅ ቁጣዬም ጨፈላለቅኳቸው።+ ደማቸውም ልብሶቼ ላይ ተረጨ፤ልብሴንም ሁሉ በከልኩ።   የምበቀልበት ቀን በልቤ ውስጥ ነውና፤+የምቤዥበትም ዓመት ደርሷል።   ተመለከትኩ፤ ሆኖም እርዳታ የሚሰጥ አልነበረም፤ማንም ድጋፍ ባለመስጠቱ ደነገጥኩ። ስለዚህ ክንዴ መዳን* አስገኘልኝ፤+የገዛ ቁጣዬም ድጋፍ ሆነልኝ።   ሕዝቦችን በቁጣዬ ረጋገጥኩ፤በታላቅ ቁጣዬም አሰከርኳቸው፤+ደማቸውንም በምድር ላይ አፈሰስኩ።”   ይሖዋ በምሕረቱና ታላቅ በሆነው ታማኝ ፍቅሩለእኛ ባደረገልን ነገሮች ሁሉ+ይኸውም ለእስራኤል ቤት ባደረጋቸው በርካታ መልካም ነገሮች የተነሳየይሖዋን የታማኝ ፍቅር መግለጫዎች፣ደግሞም ሊወደሱ የሚገባቸውን የይሖዋን ሥራዎች እናገራለሁ።   እሱ እንዲህ ብሏልና፦ “እነሱ በእርግጥ ሕዝቤ፣ የማይከዱ* ወንዶች ልጆች ናቸው።”+ ስለዚህ አዳኝ ሆነላቸው።+   በጭንቃቸው ሁሉ እሱ ተጨነቀ።+ የግል መልእክተኛውም* አዳናቸው።+ እሱ በፍቅሩና በርኅራኄው ተቤዣቸው፤+በቀድሞውም ዘመን ሁሉ አነሳቸው እንዲሁም ተሸከማቸው።+ 10  እነሱ ግን ዓመፁ፤+ ቅዱስ መንፈሱንም አሳዘኑ።+ በዚህ ጊዜ ጠላት ሆነባቸው፤+ደግሞም ተዋጋቸው።+ 11  እነሱም የጥንቱን ዘመን፣አገልጋዩ ሙሴ የኖረበትን ጊዜ አስታወሱ፦ “ከመንጋው እረኞች+ ጋር ከባሕሩ ያወጣቸው የት አለ?+ በእሱ ውስጥ ቅዱስ መንፈሱን ያኖረው፣+ 12  የከበረ ክንዱ ከሙሴ ቀኝ እጅ ጋር እንዲሄድ ያደረገው፣+ለራሱ ዘላለማዊ ስም ለማትረፍ+ውኃዎቹን በፊታቸው የከፈለው፣+ 13  አውላላ ሜዳ* ላይ እንዳለ ፈረስ፣በሚናወጡ ውኃዎች* መካከልሳይደናቀፉ እንዲሄዱ ያደረገው የት አለ? 14  የከብት መንጋ ወደ ሸለቋማ ሜዳ ሲወርድ እንደሚሆነው፣የይሖዋ መንፈስ አሳረፋቸው።”+ ለራስህ የከበረ* ስም ለማትረፍ ስትል+ሕዝብህን የመራኸው በዚህ መንገድ ነው። 15  ከሰማይ ተመልከት፤ከፍ ካለው የቅድስናና የክብር* መኖሪያህም ሆነህ እይ። ቅንዓትህና ታላቅ ኃይልህ፣የሚንሰፈሰፈው አንጀትህና+ ምሕረትህ የት አለ?+ እነዚህን ነገሮች ነፍገኸኛል። 16  አንተ አባታችን ነህና፤+አብርሃም ባያውቀን፣እስራኤልም ባያስታውሰን እንኳይሖዋ ሆይ፣ አንተ አባታችን ነህ። ስምህም ከጥንት ዘመን ጀምሮ “እኛን የተቤዠ” የሚል ነው።+ 17  ይሖዋ ሆይ፣ ከመንገዶችህ ወጥተን እንድንቅበዘበዝ የፈቀድከው* ለምንድን ነው? አንተን እንዳንፈራ ልባችን እንዲደነድን የፈቀድከው* ለምንድን ነው?+ ስለ አገልጋዮችህ፣ርስትህ ስለሆኑትም ነገዶች ስትል ተመለስ።+ 18  ቅዱስ ሕዝብህ ለጥቂት ጊዜ ወርሶት ነበር። ጠላቶቻችን መቅደስህን ረግጠዋል።+ 19  እኛ ለረጅም ጊዜ፣ ፈጽሞ እንዳልገዛኻቸው፣ጨርሶ በስምህ እንዳልተጠሩ ሰዎች ሆነናል።

የግርጌ ማስታወሻ

“ደማቅ ቀይ” ማለትም ሊሆን ይችላል።
ወይም “ድል።”
ወይም “የማይዋሹ።”
ወይም “በፊቱ ያለው መልአክም።”
ወይም “ምድረ በዳ።”
ወይም “በጥልቅ ውኃዎች።”
ወይም “ያማረ።”
ወይም “የውበት።”
ወይም “ያደረግከው።”
ቃል በቃል “ልባችንን ያደነደንከው።”