ኢሳይያስ 9:1-21

  • በገሊላ ምድር ላይ ታላቅ ብርሃን ወጣ (1-7)

    • “የሰላም መስፍን” ተወለደ (6,7)

  • በእስራኤል ላይ የተዘረጋው የአምላክ እጅ (8-21)

9  ይሁን እንጂ ፅልማሞቱ ምድሪቱ በተጨነቀችበት ጊዜ እንደነበረው ይኸውም የዛብሎን ምድርና የንፍታሌም ምድር በተዋረዱበት ወቅት እንደነበረው እንደቀድሞው ዘመን አይሆንም።+ በኋለኛው ዘመን ግን ምድሩ ማለትም በባሕሩ አጠገብ የሚያልፈው መንገድ፣ በዮርዳኖስ ክልል የሚገኘው የአሕዛብ ገሊላ እንዲከበር ያደርጋል።   በጨለማ ውስጥ ይሄዱ የነበሩ ሰዎችታላቅ ብርሃን አዩ። ድቅድቅ ጨለማ ባጠላበት ምድር የሚኖሩ ሰዎችምብርሃን ወጣላቸው።+   ሕዝቡን አብዝተሃል፤ታላቅ ደስታ እንዲያገኝ አድርገሃል። መከር በሚሰበሰብበት ጊዜ ሐሴት እንደሚያደርጉ፣ምርኮንም ሲከፋፈሉ እንደሚደሰቱ ሰዎችበፊትህ ደስ ይሰኛሉ።   ምድያም ድል በተደረገበት ጊዜ እንደሆነው ሁሉ+የሸክማቸውን ቀንበር፣ በትከሻቸው ላይ ያለውን በትር፣የተቆጣጣሪያቸውንም ዘንግ ሰባብረሃልና።   መሬቱ እስኪንቀጠቀጥ ድረስ በኃይል የሚረግጡ ሰልፈኞች ጫማ ሁሉእንዲሁም በደም የተጨማለቀ ልብስ በሙሉለእሳት ማገዶ ይሆናል።   ልጅ ተወልዶልናልና፤+ወንድ ልጅም ተሰጥቶናል፤ገዢነትም* በጫንቃው ላይ ይሆናል።+ ስሙ ድንቅ መካሪ፣+ ኃያል አምላክ፣+ የዘላለም አባትና የሰላም መስፍን ይባላል።   በዳዊት ዙፋንና+ በመንግሥቱ ላይ ይቀመጣል፤እየተጠናከረ የሚሄደው አገዛዙም* ሆነሰላሙ ፍጻሜ አይኖረውም።+ ከአሁን ጀምሮ ለዘላለምበማይናወጥ ሁኔታ ይመሠረታል፤+በፍትሕና+ በጽድቅም+ ጸንቶ ይኖራል። የሠራዊት ጌታ የይሖዋ ቅንዓት ይህን ያደርጋል።   ይሖዋ በያዕቆብ ላይ ቃል ላከ፤ቃሉም በእስራኤል ላይ ደረሰ።+   ሕዝቡም ሁሉ ይኸውም የኤፍሬምና የሰማርያ ነዋሪዎችይህን ያውቃሉ፤በትዕቢታቸውና በልባቸው እብሪት የተነሳ እንዲህ ይላሉ፦ 10  “ጡቦቹ ወድቀዋል፤እኛ ግን በጥርብ ድንጋይ እንገነባለን።+ የሾላ ዛፎቹ ተቆርጠዋል፤እኛ ግን በአርዘ ሊባኖስ እንተካቸዋለን።” 11  ይሖዋ የረጺንን ባላጋራዎች በእሱ ላይ ያስነሳል፤ጠላቶቹንም እርምጃ እንዲወስዱ ይቀሰቅሳቸዋል፤ 12  ሶርያን ከምሥራቅ፣ ፍልስጤማውያንን ደግሞ ከምዕራብ* ያመጣበታል፤+እነሱም አፋቸውን ከፍተው እስራኤልን ይውጡታል።+ ከዚህ ሁሉ የተነሳ ቁጣው አልተመለሰም፤ይልቁንም እጁ ለመምታት ገና እንደተዘረጋ ነው።+ 13  ሕዝቡ ወደመታቸው አልተመለሱምና፤የሠራዊት ጌታ ይሖዋን አልፈለጉም።+ 14  ይሖዋ ራስንና ጅራትን፣ ቀንበጥንና እንግጫን*ከእስራኤል በአንድ ቀን ይቆርጣል።+ 15  ሽማግሌውና የተከበረው ሰው ራስ ነው፤የሐሰት መመሪያ የሚሰጠው ነቢይ ደግሞ ጅራት ነው።+ 16  ይህን ሕዝብ የሚመሩት ሰዎች እንዲባዝን ያደርጉታል፤በእነሱ የሚመራውም ሕዝብ ግራ ይጋባል። 17  ይሖዋ በወጣቶቻቸው የማይደሰተው ለዚህ ነው፤በመካከላቸው ላሉት አባት የሌላቸው ልጆችና* መበለቶች ምሕረት አያሳይም፤ምክንያቱም ሁሉም ከሃዲዎችና ክፉ አድራጊዎች ናቸው፤+የሁሉም አፍ የማይረባ ነገር ይናገራል። ከዚህ ሁሉ የተነሳ ቁጣው አልተመለሰም፤ይልቁንም እጁ ለመምታት ገና እንደተዘረጋ ነው።+ 18  ክፋት እንደ እሳት ይቀጣጠላል፤ቁጥቋጦውንና አረሙንም ይበላል። በደን ውስጥ ያለውን ጥሻ ያነደዋል፤ጥሻው በሚቃጠልበት ጊዜም ጭሱ እየተትጎለጎለ ይወጣል። 19  ከሠራዊት ጌታ ከይሖዋ ቁጣ የተነሳምድሪቷ በእሳት ተያያዘች፤ሕዝቡም እሳት እንደሚበላው ማገዶ ይሆናል። ማንም ሰው ወንድሙን እንኳ አይምርም። 20  አንዱ በቀኝ በኩል ይቆርጣል፤ሆኖም ይራባል፤ሌላው ደግሞ በግራ በኩል ይበላል፤ሆኖም አይጠግብም። እያንዳንዳቸው የገዛ ክንዳቸውን ሥጋ ይበላሉ፤ 21  ምናሴ ኤፍሬምን፣ኤፍሬም ደግሞ ምናሴን ይበላል። በይሁዳም ላይ በአንድነት ይነሳሉ።+ ከዚህ ሁሉ የተነሳ ቁጣው አልተመለሰም፤ይልቁንም እጁ ለመምታት ገና እንደተዘረጋ ነው።+

የግርጌ ማስታወሻ

ወይም “መንግሥትም፤ መስፍናዊ አገዛዝም።”
ወይም “መንግሥቱም፤ መስፍናዊ አገዛዙም።”
ቃል በቃል “ከኋላ።”
“የዘንባባ ቅርንጫፍንና ሸምበቆን” ማለትም ሊሆን ይችላል።
ወይም “ወላጅ አልባ የሆኑ ልጆችና።”