ኢያሱ 12:1-24

  • ኢያሱ ድል ያደረጋቸው ከዮርዳኖስ በስተ ምሥራቅ ያሉ ነገሥታት (1-6)

  • ኢያሱ ድል ያደረጋቸው ከዮርዳኖስ በስተ ምዕራብ ያሉ ነገሥታት (7-24)

12  እንግዲህ እስራኤላውያን ድል ያደረጓቸውና ከዮርዳኖስ በስተ ምሥራቅ የሚገኘውን ምድራቸውን ይኸውም ከአርኖን ሸለቆ*+ አንስቶ እስከ ሄርሞን ተራራ+ ድረስ ያለውን እንዲሁም በስተ ምሥራቅ የሚገኘውን አረባን በሙሉ የወረሱባቸው ነገሥታት እነዚህ ናቸው፦+  በሃሽቦን የሚኖረውና በአርኖን ሸለቆ* ዳርቻ ላይ በምትገኘው በአሮዔር+ ሆኖ የሚገዛው የአሞራውያን ንጉሥ ሲሖን፤+ እሱም በአርኖን ሸለቆ+ መሃል ካለው ስፍራ አንስቶ የአሞናውያን ወሰን እስከሆነው እስከ ያቦቅ ሸለቆ* ድረስ ያለውን የጊልያድን እኩሌታ ይገዛ ነበር።  በተጨማሪም ምሥራቃዊ አረባን እስከ ኪኔሬት ባሕር*+ ድረስ፣ በስተ ምሥራቅ በቤትየሺሞት አቅጣጫ እስካለው የአረባ ባሕር ይኸውም እስከ ጨው ባሕር* ድረስና በስተ ደቡብ እስከ ጲስጋ+ ሸንተረር ድረስ ያለውን አካባቢ ይገዛ ነበር።  እንዲሁም በአስታሮትና በኤድራይ ይኖር የነበረውንና ከመጨረሻዎቹ የረፋይም+ ወገኖች አንዱ የሆነውን የባሳንን ንጉሥ የኦግን+ ግዛት፤  እሱም የሄርሞንን ተራራ፣ ሳልካን፣ ባሳንን+ በሙሉ እስከ ገሹራውያንና እስከ ማአካታውያን+ ወሰን ድረስ እንዲሁም እስከ ሃሽቦን+ ንጉሥ እስከ ሲሖን ግዛት ድረስ ያለውን የጊልያድን እኩሌታ ይገዛ ነበር።  የይሖዋ አገልጋይ ሙሴና እስራኤላውያን እነዚህን ነገሥታት ድል አደረጓቸው፤+ ከዚያም የይሖዋ አገልጋይ ሙሴ ምድራቸውን ለሮቤላውያን፣ ለጋዳውያንና ለምናሴ ነገድ እኩሌታ ርስት አድርጎ ሰጠ።+  ኢያሱና እስራኤላውያን ድል ያደረጓቸው ከዮርዳኖስ በስተ ምዕራብ ያሉት የምድሪቱ ነገሥታት እነዚህ ናቸው፤ ግዛታቸውም በሊባኖስ ሸለቆ+ ከሚገኘው ከበዓልጋድ+ አንስቶ ወደ ሴይር+ ሽቅብ እስከሚወጣው እስከ ሃላቅ ተራራ+ ድረስ ነው፤ ከዚያም ኢያሱ ምድራቸውን ለእስራኤል ነገዶች እንደየድርሻቸው ርስት አድርጎ ሰጠ፤+  ይህም በተራራማው አካባቢ፣ በሸፌላ፣ በአረባ፣ በሸንተረሮቹ ላይ፣ በምድረ በዳውና በኔጌብ+ የሚኖሩት የሂታውያን፣ የአሞራውያን፣+ የከነአናውያን፣ የፈሪዛውያን፣ የሂዋውያንና የኢያቡሳውያን+ ምድር ነው፤ ነገሥታቱም የሚከተሉት ናቸው፦   የኢያሪኮ ንጉሥ፣+ አንድ፤ በቤቴል አጠገብ የነበረችው የጋይ ንጉሥ፣+ አንድ፤ 10  የኢየሩሳሌም ንጉሥ፣ አንድ፤ የኬብሮን ንጉሥ፣+ አንድ፤ 11  የያርሙት ንጉሥ፣ አንድ፤ የለኪሶ ንጉሥ፣ አንድ፤ 12  የኤግሎን ንጉሥ፣ አንድ፤ የጌዜር ንጉሥ፣+ አንድ፤ 13  የደቢር ንጉሥ፣+ አንድ፤ የጌዴር ንጉሥ፣ አንድ፤ 14  የሆርማ ንጉሥ፣ አንድ፤ የአራድ ንጉሥ፣ አንድ፤ 15  የሊብና ንጉሥ፣+ አንድ፤ የአዱላም ንጉሥ፣ አንድ፤ 16  የመቄዳ ንጉሥ፣+ አንድ፤ የቤቴል ንጉሥ፣+ አንድ፤ 17  የታጱአ ንጉሥ፣ አንድ፤ የሄፌር ንጉሥ፣ አንድ፤ 18  የአፌቅ ንጉሥ፣ አንድ፤ የላሻሮን ንጉሥ፣ አንድ፤ 19  የማዶን ንጉሥ፣ አንድ፤ የሃጾር ንጉሥ፣+ አንድ፤ 20  የሺምሮንመሮን ንጉሥ፣ አንድ፤ የአክሻፍ ንጉሥ፣ አንድ፤ 21  የታአናክ ንጉሥ፣ አንድ፤ የመጊዶ ንጉሥ፣ አንድ፤ 22  የቃዴሽ ንጉሥ፣ አንድ፤ በቀርሜሎስ የምትገኘው የዮቅነአም ንጉሥ፣+ አንድ፤ 23  በዶር+ ሸንተረሮች የምትገኘው የዶር ንጉሥ፣ አንድ፤ በጊልጋል የምትገኘው የጎይም ንጉሥ፣ አንድ፤ 24  የቲርጻ ንጉሥ፣ አንድ፤ በአጠቃላይ 31 ነገሥታት ናቸው።

የግርጌ ማስታወሻ

ወይም “ደረቅ ወንዝ።”
ወይም “ደረቅ ወንዝ።”
ወይም “ደረቅ ወንዝ።”
ሙት ባሕርን ያመለክታል።
ጌንሴሬጥ ሐይቅን ወይም ገሊላ ባሕርን ያመለክታል።