ኢያሱ 16:1-10

  • የዮሴፍ ወንዶች ልጆች ርስት (1-4)

  • የኤፍሬም ርስት (5-10)

16  ለዮሴፍ ዘሮች+ በዕጣ የተሰጣቸው ምድር+ በኢያሪኮ አጠገብ ካለው ከዮርዳኖስ አንስቶ ከኢያሪኮ በስተ ምሥራቅ እስካሉት ውኃዎች ድረስ ሲሆን ከኢያሪኮ ሽቅብ የሚወጣውን ምድረ በዳ አቋርጦ እስከ ተራራማው የቤቴል አካባቢ ድረስ ይዘልቃል።+  እንዲሁም በሎዛ ከምትገኘው ከቤቴል አንስቶ በአጣሮት እስካለው የአርካውያን ወሰን ድረስ ይሄዳል፤  ከዚያም በስተ ምዕራብ ወደ ያፍለጣውያን ወሰን ቁልቁል በመውረድ እስከ ታችኛው ቤትሆሮን+ ወሰንና እስከ ጌዜር+ ይደርሳል፤ ባሕሩም ጋ ሲደርስ ያበቃል።  ስለሆነም የዮሴፍ ዘሮች+ ምናሴና ኤፍሬም ርስታቸው የሆነውን መሬት ወሰዱ።+  የኤፍሬም ዘሮች ወሰን በየቤተሰባቸው የሚከተለው ነው፦ በስተ ምሥራቅ በኩል የርስታቸው ወሰን አጣሮትዓዳር+ ሲሆን እስከ ላይኛው ቤትሆሮንም+ ይደርሳል፤  ከዚያም እስከ ባሕሩ ድረስ ይዘልቃል። ወሰኑ በስተ ሰሜን ሚክመታት+ ሲሆን በስተ ምሥራቅ በኩል ዞሮ ወደ ታአናትሺሎ ይሄድና በስተ ምሥራቅ አቅጣጫ ወደ ያኖአህ ይዘልቃል።  ከያኖአህ ተነስቶም ወደ አጣሮትና ወደ ናዕራ ቁልቁል በመውረድ ኢያሪኮ+ ይደርስና ወደ ዮርዳኖስ ይዘልቃል።  ከዚያም ከታጱአ+ ተነስቶ በስተ ምዕራብ በኩል እስከ ቃና ሸለቆ በመዝለቅ ባሕሩ ጋ ሲደርስ ያበቃል።+ የኤፍሬም ነገድ በየቤተሰቡ ያገኘው ርስት ይህ ነው፤  የኤፍሬም ዘሮች በምናሴ+ ርስት ውስጥም የተከለሉ ከተሞች ነበሯቸው፤ ከተሞቹ በሙሉ ከነመንደሮቻቸው የእነሱ ነበሩ። 10  ሆኖም በጌዜር+ ይኖሩ የነበሩትን ከነአናውያን አላባረሯቸውም፤ ከነአናውያንም እስከ ዛሬ ድረስ በኤፍሬም መካከል ይኖራሉ፤+ የግዳጅ ሥራ የመሥራት ግዴታም ተጥሎባቸዋል።+

የግርጌ ማስታወሻ