ኢያሱ 19:1-51

  • የስምዖን ርስት (1-9)

  • የዛብሎን ርስት (10-16)

  • የይሳኮር ርስት (17-23)

  • የአሴር ርስት (24-31)

  • የንፍታሌም ርስት (32-39)

  • የዳን ርስት (40-48)

  • የኢያሱ ርስት (49-51)

19  ከዚያም ሁለተኛው ዕጣ+ ለስምዖን ይኸውም ለስምዖን+ ነገድ በየቤተሰቡ ወጣ። ርስታቸውም በይሁዳ ርስት መካከል ነበር።+  ርስታቸውም የሚከተለው ነበር፦ ቤርሳቤህ+ ከሳባ ጋር፣ ሞላዳ፣+  ሃጻርሹአል፣+ ባላህ፣ ኤጼም፣+  ኤልቶላድ፣+ በቱል፣ ሆርማ፣  ጺቅላግ፣+ ቤትማርካቦት፣ ሃጻርሱሳ፣  ቤትለባኦት+ እና ሻሩሄን፤ በአጠቃላይ 13 ከተሞች ከነመንደሮቻቸው፤  አይን፣ ሪሞን፣ ኤቴር እና አሻን፤+ በአጠቃላይ አራት ከተሞች ከነመንደሮቻቸው፤  እንዲሁም በእነዚህ ከተሞች ዙሪያ የነበሩትን መንደሮች በሙሉ እስከ ባዓላትበኤር ይኸውም በስተ ደቡብ እስከምትገኘው እስከ ራማ ድረስ ያሉትን አካባቢዎች ይጨምራል። የስምዖን ነገድ ርስት በየቤተሰቡ ይህ ነበር።  ለስምዖን ዘሮች ርስት የተሰጠው ከይሁዳ ልጆች ድርሻ ላይ ተወስዶ ነበር፤ ምክንያቱም የይሁዳ ዘሮች ድርሻቸው በጣም በዝቶባቸው ነበር። በመሆኑም የስምዖን ልጆች ርስት ያገኙት በእነሱ ርስት መካከል ነው።+ 10  በመቀጠል ሦስተኛው ዕጣ+ ለዛብሎን+ ዘሮች በየቤተሰባቸው ወጣ፤ የርስታቸውም ወሰን እስከ ሳሪድ ድረስ ይዘልቃል። 11  በስተ ምዕራብም ወደ ማረአል ይወጣና እስከ ዳባሼት ይደርሳል፤ ከዚያም በዮቅነአም ፊት ለፊት እስካለው ሸለቆ* ድረስ ይሄዳል። 12  ከሳሪድ ተነስቶ በስተ ምሥራቅ ወደ ፀሐይ መውጫ አቅጣጫ እስከ ኪስሎትታቦር ድንበር ድረስ ይሄድና ወደ ዳብራት+ ከዚያም ወደ ያፊአ ይወጣል። 13  ከዚያም ተነስቶ በስተ ምሥራቅ በፀሐይ መውጫ አቅጣጫ ወደ ጋትሔፌር፣+ ወደ ኢትቃጺን ከሄደ በኋላ ወደ ሪሞን ወጥቶ እስከ ኒአ ይዘልቃል። 14  በመቀጠልም በስተ ሰሜን ዞሮት ወደ ሃናቶን ያመራል፤ ወሰኑ የሚያበቃው ይፍታህኤል ሸለቆ፣ 15  ቃጣት፣ ናሃላል፣ ሺምሮን፣+ ይዳላ እና ቤተልሔም + ጋ ሲደርስ ነው፤ በአጠቃላይ 12 ከተሞች ከነመንደሮቻቸው ነበሩ። 16  የዛብሎን ዘሮች ርስት በየቤተሰባቸው ይህ ነበር።+ ከተሞቹና መንደሮቻቸው እነዚህ ነበሩ። 17  አራተኛው ዕጣ+ የወጣው ለይሳኮር+ ይኸውም ለይሳኮር ዘሮች በየቤተሰባቸው ነበር። 18  ወሰናቸውም እስከ ኢይዝራኤል፣+ ከሱሎት፣ ሹነም፣+ 19  ሃፋራይም፣ ሺኦን፣ አናሃራት፣ 20  ራቢት፣ ቂሾን፣ ኤቤጽ፣ 21  ረመት፣ ኤንጋኒም፣+ ኤንሃዳ እና ቤትጳጼጽ ድረስ ነበር። 22  ከዚያም እስከ ታቦር፣+ ሻሃጺማ እና ቤትሼሜሽ ይዘልቅ ነበር፤ ወሰናቸውም ዮርዳኖስ ጋ ሲደርስ ያበቃል፤ በአጠቃላይ 16 ከተሞች ከነመንደሮቻቸው ነበሩ። 23  የይሳኮር ነገድ ርስት በየቤተሰቡ ይህ ነበር፤+ ከተሞቹና መንደሮቻቸው እነዚህ ነበሩ። 24  ከዚያም አምስተኛው ዕጣ+ ለአሴር+ ነገድ በየቤተሰቡ ወጣ። 25  ወሰናቸውም ሄልቃት፣+ ሃሊ፣ ቤጤን፣ አክሻፍ፣ 26  አላሜሌክ፣ አምዓድ እና ሚሽአል ነበር። በስተ ምዕራብም እስከ ቀርሜሎስና+ እስከ ሺሆርሊብናት ይደርስ ነበር፤ 27  ወደ ምሥራቅ አቅጣጫ ወደ ቤትዳጎን ተመልሶ እስከ ዛብሎን እንዲሁም በስተ ሰሜን እስከ ይፍታህኤል ሸለቆ ይደርስና እስከ ቤትኤሜቅ እንዲሁም እስከ ነኢኤል ይዘልቃል፤ በመቀጠልም በስተ ግራ በኩል ወደ ካቡል ይሄዳል፤ 28  ከዚያም ወደ ኤብሮን፣ ሬሆብ፣ ሃሞን እና ቃና ሄዶ እስከ ታላቋ ሲዶና+ ድረስ ይደርሳል። 29  ወሰኑ ወደ ራማ ተመልሶ እስከተመሸገችው ከተማ እስከ ጢሮስ+ ይዘልቃል። ከዚያም ወደ ሆሳ ይመለስና በአክዚብ ክልል የሚገኘው ባሕር፣ 30  ዑማ፣ አፌቅ+ እና ሬሆብ+ ጋ ሲደርስ ያበቃል፤ በአጠቃላይ 22 ከተሞች ከነመንደሮቻቸው ነበሩ። 31  የአሴር ነገድ ርስት በየቤተሰቡ ይህ ነው።+ ከተሞቹና መንደሮቻቸው እነዚህ ነበሩ። 32  ስድስተኛው ዕጣ+ የወጣው ለንፍታሌም ዘሮች ይኸውም ለንፍታሌም ዘሮች በየቤተሰባቸው ነበር። 33  ወሰናቸውም ከሄሌፍ፣ በጻናኒም ከሚገኘው ትልቅ ዛፍ፣+ ከአዳሚኔቄብ እና ከያብነኤል አንስቶ እስከ ላቁም ይደርሳል፤ ዮርዳኖስ ጋ ሲደርስም ያበቃል። 34  ወሰኑ በስተ ምዕራብ ወደ አዝኖትታቦር ይመለሳል፤ ከዚያም በመነሳት ወደ ሁቆቃ ይሄድና በስተ ደቡብ እስከ ዛብሎን፣ በስተ ምዕራብ እስከ አሴር፣ በስተ ምሥራቅ ደግሞ በዮርዳኖስ እስከሚገኘው እስከ ይሁዳ ይደርሳል። 35  የተመሸጉት ከተሞች እነዚህ ነበሩ፦ ጺዲም፣ ጸር፣ ሃማት፣+ ራቃት፣ ኪኔሬት፣ 36  አዳማ፣ ራማ፣ ሃጾር፣+ 37  ቃዴሽ፣+ ኤድራይ፣ ኤንሃጾር፣ 38  ይርኦን፣ ሚግዳልኤል፣ ሆሬም፣ ቤትአናት እና ቤትሼሜሽ፤+ በአጠቃላይ 19 ከተሞች ከነመንደሮቻቸው ነበሩ። 39  የንፍታሌም ነገድ ርስት በየቤተሰቡ ይህ ነበር፤+ ከተሞቹና መንደሮቻቸው እነዚህ ነበሩ። 40  ሰባተኛው ዕጣ+ ለዳን+ ነገድ በየቤተሰቡ ወጣ። 41  የርስታቸውም ወሰን ጾራ፣+ ኤሽታዖል፣ ኢርሻሜሽ፣ 42  ሻአላቢን፣+ አይሎን፣+ ይትላ፣ 43  ኤሎን፣ ቲምና፣+ ኤቅሮን፣+ 44  ኤልተቄ፣ ጊበቶን፣+ ባዓላት፣ 45  የሁድ፣ ብኔበራቅ፣ ጋትሪሞን፣+ 46  መሃይያርቆን፣ ራቆን እና ከኢዮጴ+ ትይዩ ያለው ድንበር ነበር። 47  የዳን ዘሮች ርስታቸው በጣም ጠቧቸው ነበር።+ በመሆኑም ወጥተው ለሸምን+ ወጉ፤ ከተማዋንም በመቆጣጠር በሰይፍ መቷት። ከዚያም ከተማዋን ርስት አድርገው በመያዝ በዚያ መኖር ጀመሩ፤ ለሸምንም በአባታቸው በዳን ስም ዳን ብለው ጠሯት።+ 48  የዳን ነገድ ርስት በየቤተሰቡ ይህ ነበር። ከተሞቹና መንደሮቻቸው እነዚህ ነበሩ። 49  በዚህ መንገድ ምድሪቱን በየክልሉ በርስትነት አከፋፍለው ጨረሱ። ከዚያም እስራኤላውያን ለነዌ ልጅ ለኢያሱ በመካከላቸው ርስት ሰጡት። 50  እነሱም የጠየቀውን ከተማ ማለትም በኤፍሬም ተራራማ አካባቢ የምትገኘውን ቲምናትሰራን+ በይሖዋ ትእዛዝ መሠረት ሰጡት፤ እሱም ከተማዋን ገንብቶ በዚያ ተቀመጠ። 51  ካህኑ አልዓዛር፣ የነዌ ልጅ ኢያሱና የእስራኤል ነገዶች የአባቶች ቤት መሪዎች በሴሎ+ በይሖዋ ፊት በመገናኛ ድንኳኑ መግቢያ ላይ+ ርስት አድርገው በዕጣ ያከፋፈሉት ድርሻ ይህ ነበር።+ በዚህ ሁኔታ ምድሪቱን አከፋፍለው ጨረሱ።

የግርጌ ማስታወሻ

ወይም “ደረቅ ወንዝ።”