ኢያሱ 21:1-45
21 የሌዋውያን አባቶች ቤቶች መሪዎች ወደ ካህኑ ወደ አልዓዛር፣+ ወደ ነዌ ልጅ ወደ ኢያሱና ወደ እስራኤል ነገዶች አባቶች ቤቶች መሪዎች ቀርበው
2 በከነአን ምድር በሴሎ+ እንዲህ አሏቸው፦ “ይሖዋ የምንኖርባቸው ከተሞች ለከብቶቻችን ከሚሆኑት የግጦሽ መሬቶቻቸው ጋር እንዲሰጡን በሙሴ በኩል አዝዞ ነበር።”+
3 በመሆኑም እስራኤላውያን ይሖዋ በሰጠው ትእዛዝ መሠረት ከራሳቸው ርስት ላይ እነዚህን ከተሞችና የግጦሽ መሬቶቻቸውን ለሌዋውያኑ ሰጡ።+
4 ከዚያም ዕጣው ለቀአታውያን ቤተሰቦች+ ወጣ፤ የካህኑ የአሮን ዘሮች የሆኑት ሌዋውያንም ከይሁዳ ነገድ፣+ ከስምዖን ነገድና+ ከቢንያም ነገድ+ ላይ 13 ከተሞች በዕጣ ተሰጧቸው።
5 ለቀሩት ቀአታውያንም ከኤፍሬም ነገድ፣+ ከዳን ነገድና ከምናሴ ነገድ+ እኩሌታ ቤተሰቦች ላይ አሥር ከተሞች በዕጣ ተሰጧቸው።
6 ለጌድሶናውያንም+ ከይሳኮር ነገድ፣ ከአሴር ነገድ፣ ከንፍታሌም ነገድና በባሳን+ ከሚገኘው ከምናሴ ነገድ እኩሌታ ቤተሰቦች ላይ 13 ከተሞች በዕጣ ተሰጧቸው።
7 ለሜራራውያንም+ በየቤተሰባቸው ከሮቤል ነገድ፣ ከጋድ ነገድና ከዛብሎን ነገድ+ ላይ 12 ከተሞች ተሰጧቸው።
8 በመሆኑም እስራኤላውያን ይሖዋ በሙሴ አማካኝነት በሰጠው ትእዛዝ መሠረት ለሌዋውያኑ እነዚህን ከተሞችና የግጦሽ መሬቶቻቸውን በዕጣ ሰጧቸው።+
9 ከይሁዳ ነገድና ከስምዖን ነገድ ላይ ደግሞ እዚህ ላይ በስም የተጠቀሱትን እነዚህን ከተሞች ሰጧቸው፤+
10 እነዚህም ከሌዋውያን መካከል የቀአታውያን ቤተሰብ ለሆኑት ለአሮን ልጆች ተሰጡ፤ ምክንያቱም የመጀመሪያው ዕጣ የወጣው ለእነሱ ነበር።
11 እነሱም በይሁዳ ተራራማ አካባቢ የምትገኘውን ቂርያትአርባን+ (አርባ የኤናቅ አባት ነበር) ይኸውም ኬብሮንን+ እና በዙሪያዋ ያለውን የግጦሽ መሬት ሰጧቸው።
12 ይሁንና የከተማዋን እርሻና መንደሮቿን ለየፎኒ ልጅ ለካሌብ ርስት አድርገው ሰጡት።+
13 ለካህኑ ለአሮን ልጆችም ነፍስ ላጠፋ ሰው የመማጸኛ ከተማ+ የሆነችውን ኬብሮንን+ ከነግጦሽ መሬቷ፣ ሊብናን+ ከነግጦሽ መሬቷ፣
14 ያቲርን+ ከነግጦሽ መሬቷ፣ ኤሽተሞዓን+ ከነግጦሽ መሬቷ፣
15 ሆሎንን+ ከነግጦሽ መሬቷ፣ ደቢርን+ ከነግጦሽ መሬቷ፣
16 አይንን+ ከነግጦሽ መሬቷ፣ ዩጣን+ ከነግጦሽ መሬቷ እንዲሁም ቤትሼሜሽን ከነግጦሽ መሬቷ ሰጡ፤ ከእነዚህ ሁለት ነገዶች ላይ ዘጠኝ ከተሞችን ሰጡ።
17 ከቢንያም ነገድ ገባኦንን+ ከነግጦሽ መሬቷ፣ ጌባን ከነግጦሽ መሬቷ፣+
18 አናቶትን+ ከነግጦሽ መሬቷ እንዲሁም አልሞንን ከነግጦሽ መሬቷ ይኸውም አራት ከተሞችን ሰጧቸው።
19 ለካህናቱ ለአሮን ዘሮች የተሰጡት ከተሞች በአጠቃላይ 13 ከተሞች ከነግጦሽ መሬቶቻቸው ነበሩ።+
20 ከሌዋውያን መካከል ለሆኑት ለቀሩት የቀአታውያን ቤተሰቦች ደግሞ ከኤፍሬም ነገድ ርስት ላይ ከተሞች በዕጣ ተሰጧቸው።
21 ነፍስ ላጠፋ ሰው የመማጸኛ ከተማ የሆነችውን+ በኤፍሬም ተራራማ አካባቢ የምትገኘውን ሴኬምን+ ከነግጦሽ መሬቷ፣ ጌዜርን+ ከነግጦሽ መሬቷ፣
22 ቂብጻይምን ከነግጦሽ መሬቷ እንዲሁም ቤትሆሮንን+ ከነግጦሽ መሬቷ ይኸውም አራት ከተሞችን ሰጧቸው።
23 ከዳን ነገድ ላይ ኤልተቄን ከነግጦሽ መሬቷ፣ ጊበቶንን ከነግጦሽ መሬቷ፣
24 አይሎንን+ ከነግጦሽ መሬቷ እንዲሁም ጋትሪሞንን ከነግጦሽ መሬቷ ይኸውም አራት ከተሞችን ሰጧቸው።
25 ከምናሴ ነገድ እኩሌታ ላይ ታአናክን+ ከነግጦሽ መሬቷ እንዲሁም ጋትሪሞንን ከነግጦሽ መሬቷ ይኸውም ሁለት ከተሞችን ሰጧቸው።
26 ለቀሩት የቀአታውያን ቤተሰቦች የተሰጧቸው ከተሞች ከነግጦሽ መሬቶቻቸው በአጠቃላይ አሥር ነበሩ።
27 የሌዋውያን ቤተሰቦች የሆኑት ጌድሶናውያንም+ ከምናሴ ነገድ እኩሌታ ላይ ነፍስ ላጠፋ ሰው የመማጸኛ ከተማ የሆነችውን በባሳን የምትገኘውን ጎላንን+ ከነግጦሽ መሬቷ እንዲሁም በኤሽተራን ከነግጦሽ መሬቷ ይኸውም ሁለት ከተሞችን ወሰዱ።
28 ከይሳኮር ነገድ+ ላይ ቂሾንን ከነግጦሽ መሬቷ፣ ዳብራትን+ ከነግጦሽ መሬቷ፣
29 ያርሙትን ከነግጦሽ መሬቷ እንዲሁም ኤንጋኒምን ከነግጦሽ መሬቷ ይኸውም አራት ከተሞችን ሰጡ።
30 ከአሴር ነገድ+ ላይ ሚሽአልን ከነግጦሽ መሬቷ፣ አብዶንን ከነግጦሽ መሬቷ፣
31 ሄልቃትን+ ከነግጦሽ መሬቷ እንዲሁም ሬሆብን+ ከነግጦሽ መሬቷ ይኸውም አራት ከተሞችን ሰጡ።
32 ከንፍታሌም ነገድ ላይ ነፍስ ላጠፋ ሰው የመማጸኛ ከተማ+ የሆነችውን በገሊላ የምትገኘውን ቃዴሽን+ ከነግጦሽ መሬቷ፣ ሃሞትዶርን ከነግጦሽ መሬቷ እንዲሁም ቃርታንን ከነግጦሽ መሬቷ ይኸውም ሦስት ከተሞችን ሰጡ።
33 የጌድሶናውያን ከተሞች በየቤተሰባቸው በአጠቃላይ 13 ከተሞች ከነግጦሽ መሬቶቻቸው ነበሩ።
34 የሜራራውያን ቤተሰቦች+ የሆኑት የቀሩት ሌዋውያን ደግሞ ከዛብሎን ነገድ+ ላይ ዮቅነአምን+ ከነግጦሽ መሬቷ፣ ቃርታን ከነግጦሽ መሬቷ፣
35 ዲምናን ከነግጦሽ መሬቷ እንዲሁም ናሃላልን+ ከነግጦሽ መሬቷ ይኸውም አራት ከተሞችን ወሰዱ።
36 ከሮቤል ነገድ ላይ ቤጼርን+ ከነግጦሽ መሬቷ፣ ያሃጽን ከነግጦሽ መሬቷ፣+
37 ቀደሞትን ከነግጦሽ መሬቷ እንዲሁም መፋአትን ከነግጦሽ መሬቷ ይኸውም አራት ከተሞችን ሰጡ።
38 ከጋድ ነገድ+ ላይ ደግሞ ነፍስ ላጠፋ ሰው የመማጸኛ ከተማ የሆነችውን በጊልያድ የምትገኘውን ራሞትን+ ከነግጦሽ መሬቷ፣ ማሃናይምን+ ከነግጦሽ መሬቷ፣
39 ሃሽቦንን+ ከነግጦሽ መሬቷ እንዲሁም ያዜርን+ ከነግጦሽ መሬቷ በአጠቃላይ አራት ከተሞችን ሰጡ።
40 ከሌዋውያን ቤተሰቦች ለቀሩት ሜራራውያን በየቤተሰባቸው በዕጣ የተሰጧቸው ከተሞች በአጠቃላይ 12 ከተሞች ነበሩ።
41 በእስራኤላውያን ርስት መካከል የነበሩት የሌዋውያን ከተሞች በአጠቃላይ 48 ከተሞች ከነግጦሽ መሬቶቻቸው ነበሩ።+
42 እነዚህ ከተሞች በሙሉ እያንዳንዳቸው በዙሪያቸው የግጦሽ መሬት ነበራቸው።
43 በመሆኑም ይሖዋ ለእስራኤላውያን፣ ለአባቶቻቸው ለመስጠት የማለላቸውን ምድር+ በሙሉ ሰጣቸው፤ እነሱም ምድሪቱን ወርሰው በዚያ መኖር ጀመሩ።+
44 በተጨማሪም ይሖዋ ለአባቶቻቸው በማለላቸው+ በእያንዳንዱ ነገር መሠረት በዙሪያቸው ካሉት ጠላቶቻቸው ሁሉ እረፍት ሰጣቸው፤ ከጠላቶቻቸው መካከል ሊቋቋማቸው የቻለ አንድም አልነበረም።+ ይሖዋ ጠላቶቻቸውን ሁሉ በእጃቸው አሳልፎ ሰጣቸው።+
45 ይሖዋ ለእስራኤል ቤት ከገባው መልካም ቃል ሁሉ ሳይፈጸም የቀረ አንድም ቃል የለም፤ ሁሉም ተፈጽሟል።+