ኢዮብ 12:1-25
12 ከዚያም ኢዮብ እንዲህ ሲል መለሰ፦
2 “በእርግጥ አዋቂዎች እናንተ ናችኋ!*ጥበብም ከእናንተ ጋር ትሞታለቻ!
3 እኔም እኮ ማስተዋል* አለኝ።
ከእናንተ አላንስም።
እነዚህን ነገሮች የማያውቅ ማን ነው?
4 ወደ አምላክ ተጣርቼ መልስ የምጠብቅ፣+የባልንጀሮቼ መሳለቂያ ሆኛለሁ።+
ጻድቅና ነቀፋ የሌለበት ሰው፣ የሰዎች መሳለቂያ ነው።
5 የደላው ሰው ‘መከራ የሚደርሰውእግራቸው በሚብረከረክ* ሰዎች ላይ ብቻ ነው’ ብሎ በማሰብ መከራን ይንቃል።
6 የዘራፊዎች ድንኳን ሰላም አለው፤+አምላክን የሚያስቆጡ ሰዎችም፣አምላካቸውን* በእጃቸው እንደያዙ ሰዎች የደህንነት ስሜት ይሰማቸዋል።+
7 ይሁን እንጂ እስቲ እንስሳትን ጠይቅ፤ እነሱም ያስተምሩሃል፤በሰማያት የሚበርሩ ወፎችንም ጠይቅ፤ እነሱም ይነግሩሃል።
8 ወይም በምድር ላይ ትኩረትህን አድርግ፤* እሷም ታስተምርሃለች፤የባሕር ዓሣም ያሳውቅሃል።
9 የይሖዋ እጅ ይህን ማድረጉን፣ከእነዚህ ሁሉ መካከል የማያውቅ ማን ነው?
10 የሕያው ነገር ሁሉ ሕይወት፣*የሰውም ሁሉ መንፈስ* በእሱ እጅ ነው።+
11 ምላስ* የምግብን ጣዕም እንደሚለይ ሁሉ፣ጆሮስ ቃላትን አያመዛዝንም?+
12 በዕድሜ በገፉት መካከል ጥበብ፣ከረጅም ዕድሜስ ጋር ማስተዋል አይገኝም?+
13 በእሱ ዘንድ ጥበብና ኃይል አለ፤+ምክርና ማስተዋልም አለው።+
14 እሱ ያፈረሰውን ነገር መልሶ መገንባት አይቻልም፤+እሱ የዘጋውን ማንም ሰው ሊከፍት አይችልም።
15 ውኃዎችን ሲከለክል ሁሉም ነገር ይደርቃል፤+ሲልካቸውም ምድርን ያጥለቀልቃሉ።+
16 ብርታትና ጥበብ* በእሱ ዘንድ ናቸው፤+መንገድ የሚስተውም ሆነ የሚያስተው የእሱ ናቸው፤
17 አማካሪዎችን ባዶ እግራቸውን ያስኬዳቸዋል፤*ፈራጆችንም ያሞኛቸዋል።+
18 ነገሥታት ያሰሩትን ይፈታል፤+በወገባቸውም ዙሪያ መታጠቂያ ያስራል።
19 ካህናትን ባዶ እግራቸውን ያስኬዳቸዋል፤+በሥልጣን ላይ ተደላድለው የተቀመጡትንም ይገለብጣል፤+
20 የታመኑ አማካሪዎችን የሚሉትን ነገር ያሳጣቸዋል፤ሽማግሌዎችንም ማስተዋል ይነሳል፤
21 በታላላቅ ሰዎች ላይ የውርደት መዓት ያዘንባል፤+ብርቱዎችንም ደካማ ያደርጋል፤*
22 ጥልቅ የሆኑ ነገሮችን ከጨለማ ውስጥ ይገልጣል፤+በድቅድቅ ጨለማ ላይ ብርሃን ይፈነጥቃል፤
23 ያጠፋቸው ዘንድ ብሔራትን ታላቅ ያደርጋል፤ወደ ግዞት ይወስዳቸውም ዘንድ ብሔራትን እንዲስፋፉ ያደርጋቸዋል።
24 የሕዝቡን መሪዎች ማስተዋል* ይነሳል፤መንገድ በሌለበት ጠፍ መሬትም እንዲቅበዘበዙ ያደርጋል።+
25 ብርሃን በሌለበት ጨለማ፣ በዳበሳ ይሄዳሉ፤+እንደሰከሩ ሰዎች እንዲዳክሩ ያደርጋቸዋል።+