ኢዮብ 14:1-22

  • ኢዮብ መልስ መስጠቱን ቀጠለ (1-22)

    • የሰው ሕይወት አጭርና በመከራ የተሞላ ነው (1)

    • “ዛፍ እንኳ ተስፋ አለው” (7)

    • “ምነው በመቃብር ውስጥ በሰወርከኝ!” (13)

    • “ሰው ከሞተ በኋላ ዳግመኛ በሕይወት ሊኖር ይችላል?” (14)

    • አምላክ የእጁን ሥራ ይናፍቃል (15)

14  “ከሴት የተወለደ ሰው፣የሕይወት ዘመኑ አጭርና+ በመከራ የተሞላ* ነው።+   እንደ አበባ ይፈካል፤ ከዚያም ይጠወልጋል፤*+እንደ ጥላም ወዲያው ያልፋል፤ ደብዛውም ይጠፋል።+   አዎ፣ ዓይንህን በዚህ ሰው ላይ አሳርፈሃል፤እሱንም ከአንተ ጋር ፍርድ ፊት ታቀርበዋለህ።*+   ንጹሕ ካልሆነ ሰው፣ ንጹሕ የሆነ ሰው መውለድ የሚችል ማን ነው?+ ማንም የለም!   የሰው የሕይወት ዘመን አጭር እንዲሆን የተወሰነ ከሆነ፣የወራቱ ቁጥር በአንተ ቁጥጥር ሥር ነው፤ከዚያ እንዳያልፍ ገደብ አበጅተህለታል።+   እንደ ቅጥር ሠራተኛ ጊዜውን እስኪያጠናቅቅ ድረስ፣እረፍት ያገኝ ዘንድ ዓይንህን ከእሱ ላይ መልስ።+   ዛፍ እንኳ ተስፋ አለውና። ቢቆረጥ መልሶ ያቆጠቁጣል፤ቅርንጫፎቹም ማደጋቸውን ይቀጥላሉ።   ሥሩ መሬት ውስጥ ቢያረጅ፣ጉቶውም አፈር ውስጥ ቢበሰብስ፣   የውኃ ሽታ ሲያገኝ ያቆጠቁጣል፤እንደ አዲስ ተክልም ቅርንጫፎች ያወጣል። 10  ሰው ግን ይሞታል፤ አቅም አጥቶም ይጋደማል፤ሰው ሲሞት የት ይገኛል?+ 11  ውኃ ከባሕር ውስጥ ይጠፋል፤ወንዝም ፈስሶ ይደርቃል። 12  ሰውም ያንቀላፋል፤ ደግሞም አይነሳም።+ ሰማይ እስከሚያልፍ ድረስ አይነቁም፤ከእንቅልፋቸውም አይነሱም።+ 13  ምነው በመቃብር* ውስጥ በሰወርከኝ!+ቁጣህ እስኪያልፍ ድረስ በሸሸግከኝ!ቀጠሮም ሰጥተህ ባስታወስከኝ!+ 14  ሰው ከሞተ በኋላ ዳግመኛ በሕይወት ሊኖር ይችላል?+ እፎይታ የማገኝበት ጊዜ እስኪደርስ ድረስ፣የግዳጅ አገልግሎት በምፈጽምበት ዘመን ሁሉ በትዕግሥት እጠብቃለሁ።+ 15  አንተ ትጣራለህ፤ እኔም እመልስልሃለሁ።+ የእጅህን ሥራ ትናፍቃለህ።* 16  አሁን ግን እርምጃዬን ሁሉ ትቆጥራለህ፤ኃጢአቴን ብቻ ትመለከታለህ። 17  መተላለፌ በከረጢት ውስጥ ታሽጓል፤በደሌንም በሙጫ ታሽጋለህ። 18  ተራራ እንደሚወድቅና ተፈረካክሶ እንደሚጠፋ፣ቋጥኝም ከስፍራው እንደሚወገድ፣ 19  ውኃ ድንጋይን እንደሚቦረቡር፣ጎርፍም የምድርን አፈር አጥቦ እንደሚወስድ፣አንተም ሟች የሆነውን ሰው ተስፋ አጥፍተሃል። 20  እስኪጠፋ ድረስ በእሱ ላይ ታይልበታለህ፤+ገጽታውን ለውጠህ ታሰናብተዋለህ። 21  ልጆቹ ክብር ቢያገኙም እሱ ይህን አያውቅም፤ውርደት ሲደርስባቸውም ልብ አይልም።+ 22  ሕመም የሚሰማው በሥጋ ሳለ ብቻ ነው፤የሚያዝነው* በሕይወት ሳለ ብቻ ነው።”

የግርጌ ማስታወሻ

ወይም “በጭንቀት የተሞላ።”
“ይቆረጣል” ማለትም ሊሆን ይችላል።
ቃል በቃል “እኔንም . . . ታቀርበኛለህ።”
ወይም “በሲኦል።” የሰው ልጆችን ሁሉ መቃብር ያመለክታል። የቃላት መፍቻውን ተመልከት።
ወይም “ለማየት ትጓጓለህ።”
ወይም “ነፍሱ የምታዝነው።”